ተራኪ | Teraki App
7.07K subscribers
542 photos
30 videos
1 file
540 links
https://linktr.ee/terakiapp
⬇️Google Play | ጉግል ፕሌስቶር - bit.ly/3CTALq3
⬇️App Store | አፕ ስቶር - https://apple.co/3AVp0i3
Telegram - https://t.iss.one/terakiapp
☎️ አብረውን መስራት ለሚፈለጉ ደራሲያን፣ ተራኪዎች እና ፖድካስተሮች በ +251904641111 | +251904649999 ይደውሉልን።
Download Telegram
ከማህበራዊ ሚዲያ ለ20 ደቂቃ እረፍት እንውሰድ እና በአዲስ ቅልብጭ እንጠመድ!

🤏🏽📚 | ትኩረት ለማይገባው ትኩረት ያለመስጠት ረቂቅ ጥበብ

በዓይነ ሕሊናህ ይህን ሣል፦ አንተ በአንድ ትልቅና ታዋቂ ኩባንያ ውስጥ ዋና ሥራ አስኪያጅ ነህ።
ሥራህን እና ሥራህ የሚያስገኝህን ጥቅማ ጥቅሞች ትወዳቸዋለህ።  ጥሩ መኪና ፣ የሚያማምሩ
አልባሳት እና የስራ ባልደረቦችህ  አክብሮት ሁሉ አለህ። ከሁሉም በላይ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሆን
ትወዳለህ። ከፍተኛ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሆን ማንነትህ ነው።
አሁን ከፍ ወዳለ ደረጃ  የመሸጋገር እድል እንደ ገጠመህ አስብ። ሆኖም ዕድሉ የመጣው ከከባድ
ሥጋቶች ጋር ነው። ፍፁም በሆነ መልኩ ማሳካት ካልቻልክ ሁሉንም ነገር ታጣለህ - ስራህን ፣
መኪናህን፣ ክብርህን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ማንነትህን።
ዕድሉን ትቀበለዋለህ?

▶️ትኩረት ለማይገባው ትኩረት ያለመስጠት ረቂቅ ጥበብ - https://terakiapp.page.link/4ccc

#ትኩረት_ለማይገባው_ትኩረት_ያለመስጠት_ረቂቅ_ጥበብ #ትረካ #ቅልብጭ
👍61
ቡናው እስኪፈላ ፤ ለምን አንድ ቅልብጭ መጽሃፍ አናዳምጥም?

🤏🏽📚 | አልኬሚስት

ህልሞችቻችንን ስለመከተል የሚያስተምር መፅሀፍ።

ዘአልኬሚስት (1988) የተባለው መፅሀፍ ስለ አንድ አንዳሉሺያዊ ወጣት እረኛ ታሪክ የጸፃፈ ሲሆን፣ ልጁ ወደ ግብፅ ፒራሚዶች ተጉዞ በተደጋጋሚ በህልሙ ሲያቸው የነበሩትን ውድ ሀብቶች ለማግኘት ሲሞክር ያስቃኘናል። በጉዞው ላይ፤ በጣም ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ነበረበት ፤ በፈተናዎቹ አማካኝነት ጠቃሚ የህይወት ትምህርቶችን ይማራል፡፡ በአስራ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን በነበረ አፈ ታሪክ ላይ በመመስረት፣ ህልምህን መከተል፣ እጣ ፈንታህን መፈለግ እና በተፈጥሮ ፍቅር መውደቅን የመሳሰሉ ርዕሶችን ይዳስሳል።

ደራሲው ፓውሎ ኮሎሆ ብራዚላዊው ሲሆን። በብዛት የሚታወቀው ዘአልኬሚስት የሚለውን መፅሃፍ በመፃፉ ነው፣ ነገር ግን ሌሎቹም መጽሃፎቹ በዓለም ላይ ከፍተኛ ሽያጭ ያገኙ ናቸው። ሥራው ወደ 83ቋንቋዎች ተተርጉመዋል።

▶️አልኬሚስት - https://terakiapp.page.link/4y5H

#አልኬሚስት #ትረካ
የሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ - ፖለቲካዊ ምጸቶች እና ማህበራዊ ሒሶች
ሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ
📖🎧 | አዲስ የመጽሐፍ ትረካ - የሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ - ፖለቲካዊ ምጸቶች እና ማህበራዊ ሒሶች

ክፍል ፩

✍🏽ድርሰት: አቤል የኪዳን ልጅ

━━━━♬♫♪(●。●)◗♪♫♬━━━━
ሮበርት ሙጋቤ በተጋበዘባቸው መድረኮች ንግግር ሲያደርግ፣ ወይም ለመገናኛ ብዙሐን ቃለ ምልልስ በሰጠ ቁጥር የሚያደርጋቸው አስገራሚ፣ አከራካሪና አወዛጋቢ ንግግሮቹ ቀልቤን ሲስቡት ኖረዋል፡፡ ሙጋቤ የሚሰጣቸው አስተያየቶች የአርዕስተ ዜናዎች መሪ አንቀጽ በመሆን ትኩረት ሲስቡ ኖረዋል፡፡
━━━━♬♫♪(●。●)◗♪♫♬━━━━

▶️ የሮበርት ጋብርኤል ሙጋቤ - ፖለቲካዊ ምጸቶች እና ማህበራዊ ሒሶች: https://terakiapp.page.link/2ShC

#ክፍል  #ትረካ

Instagram | TikTok | Twitter | Facebook | Telegram
👍6
📖🤏🏽 | አዲስ ቅልብጭ - አንድ ሰው ሲያስብ

✍🏽ድርሰት: ጄምስ አለን

ለምን እንደዚህ ታስባለህ? ለምን እንደዚህ ታሰቢያለሽ?

አብዛኛውን ጊዜ እንደነዚህ አይነት ከአስተሳሰባችን ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች የሚነሱት በማንነታችን እንዲሁም በምናሳየው ሁኔታ ላይ የምናስበው ነገር ተጸዕኖ ሲፈጥር ነው። ታዲያ አስተሳሰባችንን ለማሰልጠን ምን እናድርግ፣ ሰናስብስ በምን መልኩ መሆን አለበት? መልሱን “አንድ ሰው ሲያስብ” በተሰኘው መጽሃፍ ዉስጥ ታገኙታላችሁ!

▶️አንድ ሰው ሲያስብ - https://terakiapp.page.link/MycU

#አንድ_ሰው_ሲያስብ #ትረካ #ቅልብጭ
📖🤏🏽 | አዲስ ቅልብጭ - መኪናቸውን ሸጠው የመነኮሱት አባት

✍🏽ድርሰት: ሮቢን ሻርማ

መኪናን ሽጦ መመንኮስ ድረስ የሚያደርስ በህይወት ላይ የሚፈጠር ለውጥ!

ንብረታችሁን ሽጣችሁ መኖክሴ ሁኑ እያልን ሳይሆን፤ በህይወታችሁ ውስጥ የበለጠ ደስተኛ፣ ውጤታማ እንድትሆኑ አንድ አንድ ጊዜ ያልተጠበቁ ውሳኔዎችን መወሰን ሊኖርባችሁ ይችላል። ታዲያ ይህን አይነት ውሳኔ ስትወስኑ እንደ ምከር ምንጭ ሊሆናችሁ የሚችለዉን ”The Monk Who Sold His Ferrari” የተሰኘውን መጽሃፍ አጥሮ የተዘጋጀ ትረካ “መኪናቸውን ሽጠው የመነኮሱት አባት” በሚል ርዕስ ተራኪ ላይ በቅልብጭ መደብ ስር ታገኙታላችሁ!

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/xrCt

#መኪናቸውን_ሸጠው_የመነኮሱት_አባት #ትረካ #ቅልብጭ
📖🤏🏽 | አዲስ ቅልብጭ - ሰዎችን የማማለል ጥበብ

✍🏽ድርሰት: ሮበርት ግሪን

መቼስ የምትፈልጉትን ሰው በምን መልኩ ማማለል እንደምትችሉ የሚገልጹ ምክሮችን የተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ ተመልክታችኋል

እኛ ደግሞ አንድ የመጽሐፍ ትረካ እንጠቁማችሁ "የማማለል ጥበብ" ይሰኛል። ሰዎችን ለማማለል ከአእምሮ ጨዋታ የሚጀምሩ ስልቶችን በመጠቀም እንዴት ማሳካት እንደሚቻል በግልፅ የሚያስረዳ ነው። ዛሬውኑ አድምጡት!

▶️PLAY - https://terakiapp.page.link/QRH4

#ሰዎችን_የማማለል_ጥበብ #ትረካ #ቅልብጭ
👍2
📖🤏🏽 | አዲስ ቅልብጭ - አልጋችሁን አንጥፉ

✍🏽ድርሰት: ዊልያም ማክራቨን

ጠዋት ስትነሱ አልጋችሁን እንደማጠፍ ያለ ቀላል ነገር ህይወታችሁ ላይ ለውጥ ቢፈጥርስ?

አብዛኛውን ጊዜ እንደዚህ አይነት ጥቃቅን ለውጦች ህይወታችን ላይ ለውጥ የሚፈጥሩ ባይመስለንም፤ ምናልባትም ታላቅ የሆኑ የህይወት ግቦችን የምናሳካባቸው መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ። "አልጋችሁን አንጥፉ" የተሰኘው አጥሮ የተዘጋጀው የመጽሐፍ ትረካ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ አስር ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል!

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/KZbd

#አልጋችሁን_አንጥፉ #ትረካ #ቅልብጭ
👍21
🚗 ፒኢኢኢኢኢፕ - የቶዮታ መንገድ

ዛሬ ደግሞ ቶዮታን እንደ ድርጅርት ይዘን መጣን፤ “የቶዮታ መንገድ” የተባለው የመጽሃፍ ትረካ የድርጀቱን ባለቤት ስኬታማ ያደረጉትን ነገሮች ጨምሮ ስለ ድርጀቱ ባህል እና አሰራር ያስቃኛል።

የተለያዩ መኪናዎችን መንገድ ላይ ስንመለከት ወይ አድናቆት ወይ ደግሞ ነቀፋ እንሰነዝራለን
ሁሉም አይነት መኪኖች ለመነዳት የበቁት ከጀርባቸው ሆኖ ባመረታቸው ድርጀት እና አመራሮቹ አማካኝነት ነው። ለዚህ ማሳያ የሆነው ታዋቂው ቶዮታ እና አምራች ድርጅቱ ሲሆን፤ ላለፉት በርካታ አመታት የመኪና ምርቶቹን በማሻሻል አሁን ላለበት ደረጃ በቅቷል። ስለ ድርጀቱ ባለቤት የስኬታማነት ሚስጥሮች እንዲሁም ስለ ድርጀቱ ባህል እና አሰራር የሚያስቃኘዉን “የቶዮታ መንገድ” የተሰኘውን የመጽሃፍ ትረካ እንድታደምጡት ጋበዝን!

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/ChcU

#የቶዮታ_መንገድ #ትረካ #ቅልብጭ
ስላለፈው የፍቅር ግንኙነታችሁ ስትጠየቁ "ውይይይይይ አታንሱብኝ" ነው የምትሉት? 😔

አንዳንዴ ከተለያየንበት ምክንያት አንጻር በቀላሉ መርሳት ሊከብድ ይችላል ሆኖም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም በህይወታችሁ ስኬታማ መሆን እንዲሁም ራሳችሁን መንከባከብ እና ማሳደግ እንደምትችሉ "ያለፈውን የፍቅር ግንኙነታችሁን የምትረሱበት መንገድ" የተሰኘው የመጽሃፍ ትረካ ያሳያል። እንድታደምጡት ጋበዝን!

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/MYWU

#ያለፈውን_የፍቅር_ግንኙነታችሁን_የምትረሱበት_መንገድ #ትረካ #ቅልብጭ
👍4
በብዙ ታዋቂ ፊልሞች ላይ በታዋቂዎቹ ሞርጋን ፍሪማን እና ዴንዘል ዋሺንግተን የተመሰለውን ማልኮም ኤክስን ታውቁታላችሁ?

ካላወቃችሁት እኛ እናስተዋውቃችሁ፣ ማልኮም ኤክስ በአፍሪካ አሜሪካውያን የመብት ታሪክ ውስጥ ሲታገል የነበረ ጠንካራ ሰው ነበር። አጥሮ በተዘጋጀው “የማልኮም ኤክስ ግለ ታሪክ” በተሰኘው የመጽሃፍ ትረካ ውስጥ በህይወቱ ዉስጥ የከፈለውን መስዋትነት በጥልቀት ያስቃኛል፣ አሁኑኑ እንድታደምጡት ጋበዝን!

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/eRWY

#የማልኮም_ኤክስ_የሕይወት_ታሪክ_ለአሌክስ_ሄሌይ_እንደተነገረው #ትረካ #ቅልብጭ
6👍3
የሀምሳ አራቱ የአፍሪካ ሃገራት ታሪክ ቅጽ ፩ 🌍🎧

መፅሐፉ በደራሲ ሰላሙ ጫኔ ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን የእያንዳንዱን የአፍሪካ ሀገራት ታሪክ ከምስረታ እስክ ቅርብ ጊዜ ታሪኮቻቸው ድረስ በአጭሩ የሚያስቀኘን ይሆናል። የወደድነውንና ይበጀኛል የምንለውን አፍሪካ ሀገር መርጠን ለመመርመር ይህ መፅሀፍ እንደ መነሻ ወይ ፍላጎት መቀስቀሻ ሊሆን ይችላል፡፡

ለምን ከፊደል "ሰ" እስከ "ቀ" እንድተባለም ጠለቅ ብለን ስንገባ እንረዳዋለን።

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/wzHe

#ሀምሳ_አራቱ_የአፍሪካ_ሃገራት_ታሪክ #ትረካ
👍83
ሰባራ ጥላ - እውነተኛ ታሪክ ☂️🎧

የሕይወት ጋሪ የት እንደሚያደርስህ አይታወቅም፤ ደራሲው እንደገለጠው የአፍሬምን የሕይወት ወለል ያሻከረችው የጮሌዋ ራከብ ዓይነት ሰው በምድር ላይ ስለመኖሩ እጠራጠራለሁ። የግርማ እና የኤፍሬም ትከሻ መደንደን ያስደንቃል፤ በልጇ ምክንያት በመከራ ጦር ተደጋግማ የተወጋችው የገበያነሽ ታሪክ በራሱ ከመደነቅ በላይ ነው። የሰላሌውን ሐኪም ድንቅ ታሪክ እና የሽፍታውን ዘመላህ አውለውን ታሪክ ከኤፍሬም ታሪክ ጋር ያሰናሰለበት መንገድ ደራሲውን "አንትፍትፍ! ቢስ አይይህ!" እንድንለው እንገደዳለን። "ሰባራ ጥላ"ን አስገራሚ የሚያደርገው እውነተኛ ታሪክ መሆኑ ብቻ አይደለም፤ ከታሪኩ ቅልጥፍና አስከ አወቃቀሩ ጥበብ፣ የአንባቢያንን ስሜት በውብ ቋንቋ ሰቅዞ እንዲይዝ ተደርጎ መጻፉ ጭምር እንጂ። "ሰባራ ጥላ"ን አንብቦ የጨረሰ አንባቢ "እውነት እንዲህም አይነት ሰው አለ!?" ብሎ መጠየቁ አይቀርምና ለደራሲው አዝንለታለሁ።

አበረ አዳሙ(ደራሲ እና ገጣሚ )


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/3CAe

#ሰባራ_ጥላ #እውነተኛ_ታሪክ #ትረካ
3👍1
ምንሽሮ - አጫጭር ተረኮች 🎧

ምንሽሮ ስለ ካድሬዎች ምን ትላለች? 🧐
..ከሙያ አንጻር ጎበዝ የሚባል ካድሬ አለቃ ማግኘት አስቸጋሪ ነው፡፡ እንዳየሁትከሆነ ካድሬዎች በብዛት ገምጫጫ ናቸው፡፡ እንኳን ቀልድ ነገርም በቅጡ አይገባቸውም፡፡ ብዙ ጊዜ ለተመደቡበት ተቋም የሙያ መስክ ባዳ ናቸው። ስለዚህም በሥራ ዙሪያ ከእነሱ ጋር ተነጋግሮ ለመግባባት ይከብዳል፡፡ ሰው አያቀርቡም፤ የሚናቁ ይመስላቸዋል፡፡ ጨዋታ እና ቀልድ አይወዱም፤ ክብራቸው እና ተፈሪነታቸው የሚቀንስ ይመስላቸዋል፡፡ የሰው ችግር አይረዱም፤ የሚፈልጉት ነገር መፈጸሙ ብቻ ነው የሚያረካቸው፡፡ ሕዝብ የሚጠቀምበት ጥቂት ሥራ ሳይሆን ሹመት የሚያገኙበት የውሸት ሪፖርት ይወዳሉ፡፡ እራሳቸውን ችለው ውሳኔ አይሰጡም፤ ጉዳዩን ሁሉም ገብቶ እንዲያቦካው ይፈልጋሉ፡፡ ለሥራው ኃላፊነት አይወስዱም፤ የጭንቅ ቀን ሲመጣ ባለሙያዎቻቸውን አጋፍጠው ዞር ከማለት አይመለሱም፡፡

✒️ በ እመቤት ተሾመ ከበደ


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/6omc

#ምንሽሮ #አጫጭር_ተረኮች #ትረካ
👍95
ወደ 'ራስ - አጫጭር ተረኮች 🎧

ይህ ወደ 'ራስ የተሰኘ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ መጽሐፍ በቴክኒክና ይዘት አጠቃቀሙ ለሥነ- ጽሑፋችን እንግዳ ከሚባሉት ሥራዎች የሚመደብ ነው። መጽሐፉ አጫጭር የሚባሉ ተረኮችን ቢይዝም በገጸ ባህርያቱ ተያያዥነት ወጥ ልቦለድም ነው ማለት ይቻላል።

ተረኮቹ በዋናነት ስለ ሕይወት የሚበሰለሰሉ፣ ራሳቸውን በመፈለግ የተጠመዱ፣ አብዝተው የሚጠይቁና በመፈለግ የተጠመዱ በርካታ ገጸ ባህርያትን ይዘዋል። መጽሐፉን ያነበብ ሰውም በመጨረሻ የሚደርሰው ራሱ ላይ ሲሆን ራሱን ወደ መፈተሽና ወደ መጠየቅም ይመለሳል።

✒️ በ ናትናኤል ዳኛው


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/keTh

#ወደራስ #አጫጭር_ተረኮች #ትረካ
👍85
📣 🎧 መቆያ
የወጎች እና አጭር ልቦለዶች ስብስብ 🎧

ከመጽሃፉ ትረካ የተወሰደ

🗣️ከዕለታት አንድ ቀን እንደማንኛውም ሰነፍ ክርስትያን ከመጽሃፍ ቅዱስ አንዲት መስመር ላነብ፣ ቅዱሱን መጽሃፍ ከመኝታ ክፍሌ መጽሃፍ
መደርደርያ ላይ አነሳሁ።

አቧራውን አራግፌ ወደ መኝታዬ ተጠጋሁ፤ የአባታችን ሆይ ፀሎቴን የማስከትልባት ጥቅስ ፍለጋ፡፡ ከመተኛቴ በፊት ጥቁር እና አዲስ የሆነችውን የፈጣሪ ድርሳን ከፈትኳት። ምን እንደመራኝ እንጃ(በመንፈስ ታግዤ ይሆን?) የወንዳወንዱ ዔሳው እና የያዕቆብ ታሪክ ላይ አረፍኩ(ኦሪት ዘፍጥረት)፡፡ ልብወለድ እንደሚያነብ ሰው በዔሳው ጉዳይ ላይ ብዙ ተጠመድኩ፤ ቁመናው ሳበኝ። አኗኗሩንወደድኩ፤ እሱ አደን ሲወጣ ቤት የምጠብቀው ሚስቱ ብሆን ስል ተመኘሁ።🗣️

✒️ እናኑ ግርማ መልካ (አርክቴክት)


▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/kNkY

#መቆያ #ወጎች #አጫጭር_ተረኮች #ትረካ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍43😁1
💰💼 ድለላ እኮ የተከበረ ሙያ ነው!!

ድለላ ወይም የኮሚሽን ስራ በብዙዎች ዘንድ አሉታዊ ስም ሲሰጠው ይስተዋላል። ይህ 'የድለላ ሞያ ጥበብ' የተሰኘው መጽሃፍ 'ደላላ ማለት ምን ማለት ነው?' ከሚለው ጀምሮ ፤ የድለላ አይነቶች፣ ባህሪያት እና መርሆች ፤ እስከ ስለኮሚሽን አጠያየቅ (የድካም ዋጋ አከፋፈል) ዘዴዎች ሰፋ አርጎ ያወጋናል።

ይህ መጽሐፍ "ሥራ የለም” ለሚሉ ለበርካቶች ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ይታመንበታል። ስለሆነም ተረካውን በማድመጥ ዘርፈ ብዙ በሆነው የድለላ ሞያ ይሳተፉ፡፡ ለህብረተሰቡም የሰመረ አገልግሎት ይስጡ፡፡ ሀገርንም ይጥቀሙ፡፡

✒️ ወንድሙ ማናዬ

▶️PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/P3zm

#የድለላ_ሞያ_ጥበብ #ቢዝነስ #ትረካ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍62
⭐️ሶባሐል ኸይር! - እስላማዊ የመጽሃፍ ትረካ 🕋

የዚህ መጽሐፍ መግቢያ እንዲህ የሚል ሊሆን ቻለ ...
“የምትናገሩትም ሆነ የምትጽፉት ነገር ታሪካችሁ ነው፤ ከዕድሜያችሁ በላይ ምድር ላይ ሊቆይ ይችላልና በጥንቃቄ ፃፉ፣ ተናገሩም፡፡'' ተብሏል፡፡
መጽሐፉ በዋናነት ሰዎች ከፈጣሪያቸው አላህ ሱ.ወ. አንፃር መልካም ጥርጣሬ እንዲያሳድሩ (ተፋኡል እንዲኖራቸው)፣ በዱንያ ሕይወታቸው እንዲበረቱና ተስፋ እንዳይቆርጡ፣ ዱንያንም በብልሃትና በጥንካሬ እንዲሻገሩ ሀሳብ ይሠጣል፣ መንገድ ይጠቁማል፡፡ በየትኛዉም ከባድ የዱንያ ማዕበል ዉስጥ ብትሆኑ ፊትለፊታችሁ ብሩህ ነው አብሽሩ አትፍሩ ይላል፡፡ ወዳጆቼ ... ምክሩና ምልከታው ከናንተም በላይ ለኔ ያስፈልጋል፡፡ እኔን ፀሐፊዉን፤ እናንተን አንባቢዎችንም ተጠቃሚዎች ያድርገን፡፡

📝 በ ሙሐመድ ሰዒድ


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/nseZ

#ሶባሐልኸይር #እስላማዊ #ትረካ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5👍3
🏠✝️በእኔ ቤት

ይህ ድርሰት በኢትዮጵያ አርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ዉስጥ ያለውን እምቅ የእዉቀት ሀብት ሲያሳይ እግረ መንገዱን በጥቂቶች የሚከናወኑ አስተዳደራዊ እና ስነ ምግባራዊ ብልሽቶች የፈተና ምንጭ መሆናቸውን ፍንትው አድርጎ የሚያስረዳ ሥራ ነው፡፡ ትረካውን ካደመጡ በኋላ በልቦለዱ ውስጥ የታመቁት ሀሳቦች አደባባይ ወጥተው ለውይይት መነሻ መሆናቸው አይቀሬ ነው፡፡

📝 በ በረከት ዘላለም
🎤ተራኪ - እስጢፋኖስ ግርማ


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/R5dL

#በእኔቤት #ልብወለድ #ትረካ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍9
🛸ዳሎጵያ - ሳይንሳዊ ልብወለድ

"ይህ መፅሀፍ ሳይንስን ከመንፈሳዊነት ጋር ያጣመረ ስራ ነው… ዳኝነቱ ለአንባቢ ይሁን!... ነገር ግን አንድ ነገር ልበል… በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1990 ዓ.ም ላይ
አንድ ሰው "ወደፊት ምን መሆን ትፈልጋለህ?" የሚል ጥያቄ አቀረበልኝ… እኔም "ጠፈርተኛ" ብዬ መለስኩለት… ያው ጠያቂ መልሶ "ፊዚክስና ሂሳብ ላይ እንዴት ነህ?" ሲል ጠየቀኝ… "ጎበዝ አይደለሁም" አልኩት… እንደገና "ጥሩ የሆንክበት የትምህርት አይነት ምንድነው?" አለኝ… "ባዮሎጂ" በማለት ስመልስ… "በቃ ጠፈርተኛነቱን ተወውና ሀኪም ለመሆን በርትተህ ተማር" ብሎ የግል ሀሳቡን ሰነዘረልኝ… እኔ ግን ቅር ቅር አለኝ… በህይወት ዘመኔ አራት ነገር ለመሆን ፈልጌ አንዱም አልተሳካልኝም… ቄስ
(ሰባኪ)፣ ፓይለት፣ ጠፈርተኛና አስተዳዳሪ (ባለስልጣን) የመሆን ምኞት ነበረኝ… የትኛውም ምርጫ አልሆነልኝም… ነገር ግን ከሃያ ሁለት አመት በኋላ ሳላስበው በዚህ
መፅሀፍ ውስጥ እነዚህን አራቱንም የሙያ ዘርፎች ለራሴ ተወንኩባቸው… ደራሲ መሆን ለካ እንዲህ የልብ ያደርሳል!… እንዴት እንደረካሁ!!!... ተመስገን አምላኬ!!!"

- የደራሲው መልዕክት

📝 ሲሳይ መኳንንት
🎤ተራኪ - ናኦድ ባዬ


▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/SZDg

#ዳሎጵያ #ልብወለድ #ትረካ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍51😁1
💌ያልተላከው ደብዳቤ
እና ሌሎች አጫጭር ልብወለዶች

ይህ ድርሰት በ2017 ዓ.ም. ተጽፎ ለአንባበያን የበቃ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ ሲሆን 'ሳይመረጥ የቀረው ለእናቶቸ የተላከው ደብዳቤ' ፣ 'የቱ ናት ኢትዮጵያ የቱን እንበላት' ፣ 'ይጣራል አድዋ' ፣ 'የጋራ ጡት አባይ' እና 'የመከነው ህልም' የተሰኙ የተለያዩ አጫጭር ልብወለዶች እና የጉዞ ማስታወሻዎችን የየዘ፣ ለማድመጥ የሚማርክ ትረካ ነው።

📝 በ ትክክል ገና

▶️🎧PLAY(ለማጫወት) - https://terakiapp.page.link/T3vU

#በእኔቤት #ልብወለድ #ትረካ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍31