ስፑትኒክ ኢትዮጵያ
6.06K subscribers
3.9K photos
1.66K videos
2.21K links
ያልተነገረውን እንነግርዎታለን

ስለ አፍሪካ በእንግሊዘኛ ቋንቋ፤ @sputnik_africa
Download Telegram
⚡️በኢራን ቴህራን በከፍተኛ ፍርድ ቤት ሶስት ዳኞች ላይ ያነጣጠረ የመሳሪያ ጥቃት ተፈጸመ

ከዳኞች ሁለቱ ሲገደሉ፤ ሶስተኛው ዳኛ ቆስለው በህክምና ላይ እንደሚገኙ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇪🇹🇮🇷 ኢትዮጵያ እና ኢራን ብሪክስን ተጠቅመው ግኑኝነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው የኢራን አፈ-ጉባኤ ተናገሩ

የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ መሐመድ ጋሊባፍ፤ አርብ እለት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በአዲስ አበባ ባደረጉት ውይይት፤ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት በኢኮኖሚ፣ ባህል እና ፖለቲካ ትስስር ሊሰፋ እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ኢራን እና ኢትዮጵያ በእስያ እና አፍሪካ የሚገኙ፤ በአንዳንድ ኃያላን የቅኝ አገዛዝ ፖሊሲዎች ሳቢያ የሚፈተኑ ወሳኝ ሀገራት መሆናቸውንም አንስተዋል።

የሁለቱ ሀገራት ደማቅ ባህል እና ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ያላት ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ በኢኮኖሚ፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስኮች ትብብርን ለማስፋት ልዩ እድል ይፈጥራል ሲሉ የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤው ተናግረዋል።

🗣 "የብሪክስ ቡድንን አቅም የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማሳደግ እና ትብብራችንን ለማጠናከር ልንጠቀምበት ይገባል" ብለዋል።

ኢትዮጵያ እና ኢራን በፈረንጆቹ 2024 ጥር ወር ብሪክስን በይፋ ተቀላቅለዋል።

🤝 ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢራን ከሌላኛዋ የብሪክስ አባል ሀገር ሩሲያ ጋር ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ስምምነት አርብ እለት ተፈራርማለች።

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇷🇺📹 የሩሲያ ጦር በካርኮቭ ክልል ከግሉቦኮ መንደር ዳርቻ የሚገኘውን የዩክሬን የጥቃት ቡድን አወደመ

ተንቀሳቃሽ ምስሉ በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር የተለቀቀ ነው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇸🇩🇸🇸 ሱዳን ውስጥ ዜጎች ተገድለዋል መባሉን ተከትሎ በደቡብ ሱዳን በተነሳው ሕዝባዊ አመጽ ምክንያት በመላ ሀገሪቱ የሰዓት እላፊ ታወጀ

🗣 ከምሽት 12 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጠዋቱ 12 ሰዓት የሚቆየውን የሰዓት እላፊ አዋጅ በቴሌቭዥን ቀርበው ባደረጉት ንግግር ያስታወቁት የፖሊስ አዛዥ አብርሀም ፒተር ማንዩአት "ፖሊስ የትኛውንም አይነት ጥሰት አይታገስም" ብለዋል።

ሁከቱ በዋነኛነት በዋና ከተማዋ ጁባ በሚገኙ የሱዳናውያን የንግድ ተቋማት ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ቢያንስ የሶስት ሰዎች ህይወት መጥፋቱን እና ሰባት መቁሰላቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አስታውቀዋል። ብጥብጡ በሱዳን ድንበር አቅራቢያ ወደምትገኘው አዊል ተዛምቶ ሶስት ቤቶች ተቃጥለዋል። የጸጥታ ኃይሎች የሱዳን ነዋሪዎችን ደኅንነታቸው ወደሚጠበቅበት ቦታ ለማዛወር እየሰሩ ነው።

አመፁ የሱዳን ጦር እና ጥምር ቡድኖች በቅርቡ ዋድ ማዳኒ ከተማን ከአማፅያኑ ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ባስለቀቁበት ወቅት፤ የደቡብ ሱዳን ዜጎችን ገድለዋል የሚል ክስ ከቀረበባቸው በኋላ የመጣ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የሱዳን ጦር ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ይደግፋሉ ተብለው በተጠረጠሩ ንፁሀን ዜጎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን ጨምሮ "የተነጠሉ ጥቃቶችን" አውግዟል።

🗣 የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር የሱዳን አምባሳደርን ጠርተው ካነጋገሩ በኋላ "በቁጣ ምክንያት ልቦናችን ሊጋረድ ወይም በሀገራችን የሚገኙ የሱዳን ነጋዴዎችና ስደተኞችን በጠላትነት ልንመለከት አይገባም" ሲሉ አሳስበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇲🇿 የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት የሀገሪቱን የኢነርጂ እና ፋይናንስ ሴክተር የሚመሩ ሁለት ባለስልጣናትን ሾሙ

የሞዛምቢክ ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖ፤ ካርላ ሉቬራ የገንዘብ ሚኒስቴርን እና ኢስቴቫኦ ፓሌ ደግሞ የማዕድን ሀብትና ኢነርጂ ሚኒስቴርን እንዲመሩ አርብ ዕለት ሹመዋል።

ሉቬራ ከ2020 ጀምሮ የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ምክትል ሚኒስትር በመሆን እንዲሁም በሞዛምቢክ ባንክ በዳይሬክተር ቦታዎች አገልግለዋል። ፕሬዝዳንቱ የኢኮኖሚ እና ፋይናንስ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መለያየተቻውን አስታውቀዋል።

በ2020 የሞዛምቢክ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ ኢኤንኤች ሊቀመንበር እና የብሔራዊ ማዕድን ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉት ፓሌ፤ እንደ ቶታል ኢነርጂ እና ኤክሶን ሞቢል ካሉ ኩባንያዎች ጋር የጋዝ ፕሮጀክቶችን እንደገና ለመጀመር ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇲🇺 የሞሪሸስ ጠቅላይ ሚኒስትር የቻጎስ ደሴት የኪራይ ስምምነት ላይ ጥያቄ አነሱ

የሞሪሸሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቪን ራምጎላም የቻጎስ ደሴቶች ርክክብን በተመለከተ፤ የድርድሩ ቁልፍ ጉዳይ በሆነው የአሜሪካ እና ብሪታንያ የጦር ሰፈር የኪራይ ውል ጊዜ ላይ ተቃውሞ አንስተዋል።

በጥቅምት ወር ብሪታንያ የቻጎስ ደሴቶችን ለሞሪሸስ ለማስረከብ ተስማምታ የነበረ ሲሆን፤ እስካሁን ባልፀደቀው ስምምነት መሰረት የዲዬጎ ጋርሺያን የጦር ሰፈር በ99 ዓመት የኪራይ ውል ለመቆጣጠር ያስችላታል። የህዳሩን ምርጫ አሸንፈው ስልጣን የያዙት ጠቅላይ ሚኒስትር ራምጎላም ስምምነቱን ተችተዋል።

የብሪታንያን ስምምነት “የክህደት” ነው ሲሉ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ራምጎላም፤ የኪራይ ውሉ የዋጋ ንረት እና የምንዛሪ ተመንን ሊያካተት፣ እንግሊዝ ውሉን በራሷ እንዳታድስ ሊገድብና ለሞሪሸስ ሉዓላዊነት እውቅና ሊሰጥ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ሉዓላዊነት አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዩናይትድ ስቴትስ ስምምነቱ ከትራምፕ ሥልጣን በፊት እንዲጠናቀቅ ትፈልጋለች ብለዋል።

የትራምፕ እጩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማርኮ ሩቢዮ፤ የቻጎስ ደሴቶች ስምምነት የጦር ሰፈሩን ከቻይና ጋር ወዳጅ ለሆነ ሀገር አሳልፎ የሚሰጥና የአሜሪካን ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🗣ሁቲዎች በእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ላይ ጥቃት ሰነዘሩ

አንሳር አላህ በሚል ስያሜው የሚታወቀው የሁቲ ንቅናቄ ቴል አቪቭ በሚገኘው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ላይ ጥቃት መፈፀሙን አስታውቋል። ጥቃቱ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ የመጣ ነው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇧🇫🇨🇮 የቡርኪናፋሶ የፀጥታ ሚኒስትር ሀገሪቱን ከኮትዲቯር በሚያዋስነው ድንበር ጎብኝት አደረጉ

እንደ ሚኒስቴሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ማሃማዱ ሳና የዪንደሬ የፍቸሻ ጣቢያን አርብ እለት ጎብኝተዋል። ሚኒስትሩ የጸጥታ ሁኔታውን ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎችን ገምግመዋል።

🗣 "የእናንተ ጥረት፣ ፅናት እና ቁርጠኝነት የሀገራችንን ደህንነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ምሰሶዎች ናቸው። በቀጣይም ይዞታችንን በተጠንቀቅ መያዙን እንቀጥል" ሲሉ ለመከላከያና የፀጥታ አካላት እንዲሁም ለመከላከያ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተናግረዋል።

የሳህል ሀገራት ህብረት አባል ዜጎችን የድንበር እንቅስቃሴ ምቹ ማድረግም ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫው አክሎ ገልጿል። "ትብብር እና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ለማጠናከር የተጓዦች መቀበያ እና ፈጣን አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንደተዘጋጁ" በመግለጫው ተመላክቷል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇷🇺 የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በቅርቡ በዩክሬን እና እንግሊዝ መካከል የተፈረመውን የ '100 ዓመት አጋርነት' ስምምነት ተቹ

ቃል አቀባይዋ ያነሷቸው ቁልፍ ነጥቦች፦

➡️ ስምምነቱ ተቀባይነት የለውም ያሉት ዛካሮቫ ትርጉም የለሽ እና ውጤት አልባ ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል።

➡️ የብሪታንያ ተሳትፎ በአዞቭ-ጥቁር ባህር አካባቢ ያለውን ቦታ ለመያዝ ያላትን የረጅም ጊዜ ምኞት የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

➡️ ዩክሬን እና ብሪታንያ በአዞቭ ባህር ላይ ለመተባበር ምንም አይነት ህጋዊ መሰረት እንደሌላቸው ገልጸዋል።

➡️ ዛካሮቫ ስምምነቱ የዩክሬን መንግሥት የህዝብ ግኑኝነት ስልት እና ጠንካራ ጥምረት እንደፈጠረ ለማስመሰል የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል።

ስምምነቱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰር ኪር ስታርመር ሐሙስ እለት ዩክሬንን በጎበኙበት ወቅት ነበር የተፈረመው። ይፋ የሆነው ሰነድ በዩክሬን የጦር ሰፈሮችን በማቋቋም እና በረጅም እርቀት የጦር መሳሪያዎች ዙርያ ትብብር ለማድረግ የተቀመጡ እቅዶችን ይዘረዝራል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
🇳🇬 በሰሜን ናይጄሪያ ነዳጅ ጫኝ ተሸከርካሪ ፈንድቶ ከ60 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

በናይጄሪያ ኒጀር ግዛት የነዳጅ ጫኝ ታንከር ሹፌር ተሽከርካሪውን መቆጣጠር ባለመቻሉ መስቀለኛ መንገድ ላይ እንደተገለበጠ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ነዳጁ መንገዱ ላይ መፍሰሱን ተከትሎ በአካባቢው የነበሩ በርካታ ነዋሪዎች ነዳጁን ለመሰብሰብ ሲሞክሩ በድንገት ፍንዳታው ተከስቷል።

እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ፤ እሳቱ በአቅራቢያ የነበሩ መኪኖች፣ ሞተር ሳይክሎች እና ሱቆችን በእሳት ነበልባል ገርፏል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መሐመድ ኡማሩ ባጎ በክስተቱ ማዘናቸውን ገልፀው ለተጎጂ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ምስሎቹ ከማህበራዊ ትስስር ገጾች የተገኙ ናቸው

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
❗️ የሩሲያ ጦር በዶንዬትስክ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ ፔትሮፓቭሎቫካ እና ቭሬሜቭካ መንደሮችን ነፃ እንዳወጣ የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🇷🇺📹 የሩሲያ ጦር ነጻ ከወጣው ቭሬሜቭካ መንደር 600 ከሚደርሱ ህንጻዎች የዩክሬን ጦር ኃይሎችን በማስወጣት የጠላትን ምሽጎችን አወደመ

በአንደኛው ሕንፃ ላይ የሩሲያ ባንዲራ ሲውለበለብ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ተለቋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#sputnikviral | 🇪🇸 በስፔን አስቱን ሪዞርት የበረዶ መንሸራተቻ ሊፍት ወደቆ ​​በትንሹ 30 ሰዎች መጎዳታቸውን መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

📲 መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦

👉 APK ፋይል ሊንክ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ 👉@sputnik_ethiopia