TIKVAH-MAGAZINE
197K subscribers
20.3K photos
352 videos
70 files
2.56K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ለግብፅ የ4.7 ቢሊየን ዶላር የመሳሪያ ሽያጭን አፅድቋል።

በመሳሪያ ሽያጩ መሰረት ግብፅ ራዳር፣ ሚሳኤሎች እና የሎጅስቲክስ እንደዚሁም የኢንጂነሪንግ ድጋፎችን ከአሜሪካ ታገኛለች።

አሜሪካ ለግብፅ የምትሰጠው የአየር ስርዓት መሳሪያ ሂሊኮፕተሮችን፣ ድሮኖችን እንደዚሁም ክሩዝ ሚሳኤሎችን ለመመከት ያስችላል።

አሜሪካ ይህንን ሽያጭ የኔቶ አባል ሃገር ካልሆኑት ዋነኛ አጋሮቿ ውስጥ የሆነችው የግብፅን ደህንነት ለማሻሻል መሆኑን ገልፃ ይህም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም እና የኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር ያስችላል ብሏል።

በተጨማሪ ለግብፅ ጦር ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ 26 የአሜሪካ መንግስት ሰራተኞች እና 34 ኮንትራክተሮች ወደ ግብፅ ያመራሉ ተብሏል።

የመሳሪያ ሽያጩን የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ያፀደቀው ሲሆን በቀጣይ የኮንግረሱ ውሳኔ ይቀረዋል።

ከ1979 ጀምሮ ግብፅ ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት በመፈራረሟ ከአሜሪካ የመሳሪያ ሽያጭ እና ድጋፍ በገፍ እያገኘች እንደሆነች ይታወቃል።

ግብፅ በተመሳሳይ በ2024 የ5 ቢሊየን ዶላር የመሳሪያ ግዢን ከአሜሪካ ፈፅማለች።

ሃገረ ግብፅ ከእስራኤል በመቀጠል ከአሜሪካ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የወታደራዊ ድጋፍ የሚደረግላት ሃገር ስትሆን ከ1979 ጀምሮ በየአመቱ የ1.3 ቢሊየን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ ከአሜሪካ ታገኛለች።

Source: Al Jazeera, Madamasr, Defensepost

@TikvahethMagazine
🤔10895👎29🤣20👍8🤬5😢5🤯2🕊2
ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ጎን አፓርትመንት ሽያጭ
በ10%ቅድመ ክፍያ  የቤት ባለቤት ይሁን!!
👉1መኝታ 63 ካሬ
     2መኝታ 86ካሬ
     3መኝታ 114ካሬ -146 ካሬ
👉ቀሪውን 90% በ16ዙር ብር ያለምንም ጭማሪ በብር ከፍለው የሚጨርሱት
  👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ አዘጋጅተናል

ተጨማሪ መሰረታዊ ነገሮችን ያሟላ
👉 ስቶር እና የላውንደሪ ማስቀመጫ
👉 የመኪና ማቆሚያ
👉 የተፈጥሮ ብርሀን የሚጠቀም
👉 የከርሰ ምድር ውሀ
👉 የቆሻሻ ማስወገጃ
👉 ዘመናዊ የደህንነት ካሜራ
ቀድመው በመምጣት የሚፈልጉትን ቤት የእርሰዎ ያድርጉ፡፡
  ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
     +251-930-82-56-05
     +251-911-83-22-90
https://t.iss.one/Temersalesconsultant
WhatsApp. https://wa.me/qr/CCTF4GFMC2EEA1
9👎1
አጠቃላይ የጤና ቼካፕ (Medical Checkup)

ከ 3000 ብር ጀምሮ! ከነፃ የዶክተር ማማከር ጋር።

አጋር ክሊኒክ ፣ የጤናዎ አጋር።

ቀጠሮ ለማስያዝ
📞 011 644 8048

አድራሻ: https://maps.app.goo.gl/voKGteAKWGV3grif8?g_st=ipc

Telegram group: https://t.iss.one/agarclinic

TikTok: https://www.tiktok.com/@agar.clinic?_t=ZM-8xoGU8aTUiD&_r=1

Facebook: https://www.facebook.com/share/1CLD724fbR/?mibextid=wwXIfr
10
የፈረንሳዩ ተቋም ካናል+  የደቡብ አፍሪካውን መልቲቾይዝ ግሩፕ በ3 ቢሊየን ዶላር ገዝቶታል።

ካናል+ መጀመሪያውንም ቢሆን የመልቲቾይዝ 45 በመቶ ባለድርሻ የነበረ ሲሆን አሁን ሙሉ ለሙሉ ድርሻውን ገዝቶታል።

መልቲቾይዝ ለ40 አመታት የቆየ ስም የገነባ መሆኑ ሲገለፅ በአፍሪካ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉት ይገለፃል።

መልቲቾይዝ በክፍያ ከሚሰሩ የቴሌቪዥን ገበያዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ እና ጎቲቪ በኩል የተለያዩ የስፖርት እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በክፍያ ሲያስተላልፍ ቆይቷል።

ግዢው ሙሉ ለሙሉ በመጪው ጥቅምት ይጠናቀቃል ተብሎ ሲጠበቅ ካናል+ የደቡብ አፍሪካን ፕሮዳክሽን በአዲስ ገበያዎች የማስተዋወቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

ደቡብ አፍሪካ በህጓ የደቡብ አፍሪካን የስርጭት መብት የያዘ ድርጅት ባለቤትነቱ ከ20 በመቶ በላይ በውጪ ዜጋ መያዝን ስለምትከለክል መልቲቾይዝ የስርጭት መብቱን ላይሰንስኮ በተሰኘ ድርጅት ማድረጉ ተሰምቷል።

መልቲቾይዝ ሃገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን በዲ ኤስ ቲቪ በኩል የእግር ኳስ እና የመዝናኛ ፕሮግራሞችንም ሲያሰራጭ ቆይቷል።

ካናል+ በበኩሉ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ከገባ በኋላ የክፍያ ቴሌቪዥኑን በመዝጋት ወደ ሌላ አማራጮች ማዞሩን ከወራት በፊት መግለፁ ይታወሳል።

Source: The Punch

@TikvahethMagazine
30👍5👏1
የቀድሞው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ካቢላ በሃገር ክህደት ወንጀል ተከሰሱ።

የቀድሞ ፕሬዚዳንት የሃገር ክህደት ወንጀል ክስ ትናንት በኪንሻሳ ባለው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ሲጀመር ካቢላ ከሃገር ክህደት በተጨማሪ በግድያ፣ በአስገድዶ መድፈር እና የM23 ታጣቂዎችን ደግፏል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የወቅቱ የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፍሌክስ ሽሴኬዲ በተደጋጋሚ ካቢላ ከአመፁ ጀርባ ያለ ሰው ነው ብለው ሲከሱ የቆዩ ሲሆን ጆሴፍ ካቢላ በፍርድ ቤቱ የተቀረቡባቸውን ክሶች አላደረኩም ብለዋል።

ጆሴፍ ካቢላ ላለፉት ሁለት አመታት ከሃገራቸው ወጥተው በደቡብ አፍሪካ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ባለፈው ግንቦት ወር ነበር ወደ ሃገራቸው የተመለሱት።

ካቢላ የዕድሜ ልክ ያለመከሰስ መብት የነበራቸው ቢሆንም የኮንጎ ሴናተሮች ከተለያዩ ወንጀሎች ጋር በተያያዘ ያለመከሰስ መብታቸውን በማንሳታቸው ሊከሰሱ ችለዋል።

ኮንጎ ካቢላን ከሩዋንዳው ፖል ካጋሜ ጋር በመሆን የወቅቱን ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሴሽኬዲን ከስልጣን ለማውረድ ሸርበዋል ብላ ስትከስ ለተጨማሪ ምርመራ ፍርድ ቤቱ ለወሩ መጨረሻ ቀጠሮ ይዟል።

ጆሴፍ ካቢላ በ29 አመታቸው የአባታቸውን መገደል ተከትሎ በ2001 ሃገሪቱን መምራት ሲጀምሩ በ2019 ነበር ከኃላፊነታቸው የወረዱት።

Source: BBC

@TikvahethMagazine
42👎1😢1
ቢሊየነሩ አሊኮ ዳንጎቴ ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ሊቀመንበርነት ለቀቁ።

ናይጄሪያዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ ከዳንጎቴ ሲሚንቶ ሊቀመንበርነት መልቀቃቸው ሲሰማ በእሳቸው ምትክ ድርጅቱን በሊቀመንበርነት ኢማኑኤል ኢካዞቦህ ይመሩታል።

በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፈው ሰኔ ዳንጎቴ ከ20 ዓመታት በኋላ ከሌላኛው ድርጅታቸው ዳንጎቴ ስኳር ማጣሪያ መልቀቃቸው ይታወሳል።

ድርጅቱ የዳንጎቴ ከኃላፊነት መልቀቅ ከድርጅቱ የተተኪ መርህ እና አስተዳደር ጋር አብሮ የሚሄድ ነው ብሏል።

ዳንጎቴ ሲሚንቶ በአህጉሪቱ ያለ ትልቁ የሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሆን በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙ ሲሚንቶ ወደ ሃገር ውስጥ በማስገባት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ናይጄሪያ በአህጉሪቱ ብዙ ሲሚንቶ ለውጪ ገበያ በማቅረብ መሪ እንድትሆን አድርጓታል።

ዳንጎቴ ሲሚንቶ በአመት 48.6 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ሲሚንቶ የሚያመርት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 32 ሚሊየን ያህሉ በናይጄሪያ ይመረታል።

ቀሪው 16 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ኢትዮጵያን ጨምሮ በሌሎች 9 የአፍሪካ ሃገራት ይመረታል።

የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ በኢትዮጵያ በ2007 ዓ.ም ስራውን የጀመረ ሲሆን ለበርካታ ሰዎችም የስራ ዕድልን የፈጠረ ነው።

በቅርቡ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ ያለው የሲሚንቶ ፋብሪካ ላይ የ400 ሚሊየን ዶላር ማስፋፊያ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል።

በማስፋፊያው መሰረትም በአመት የኢትዮጵያው ፋብሪካ ብቻ 5 ሚሊየን ቶን በላይ ሲሚንቶ በአመት ማምረት ሲያስችለው ለተጨማሪ 25,000 ሰዎችም የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ እንደሚጠበቅ መነገሩ ይታወሳል።

Source: Business Insider Africa, Semafor

@TikvahethMagazine
95👏10👍5
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://t.iss.one/samcomptech
12🤣2
በጥራት እና በፍጥነት 7 ሳይቶች ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁን ላይ ደሞ ለእርስዎ ለመኖሪያነት ምቹ በሆኑ አካባቢዎች

በሳርቤትበፒያሳበአያትበሶማሌተራበጋርመንት የመኖሪያ አፓርትመንት ቤቶችን ከባለ 1 እስከ ባለ3 መኝታ ከ63 ካሬ -146ካሬ በ10% ቅድመ ክፍያ ማለትም ከ693 ሺብር ጀምሮ በሽያጭ ላይ እንገኛለን።

👉የ25% ልዩ ቅናሽም ለእርስዎ አዘጋጅተናል።
👉ለንግድ የሚሆኑ ሱቆች ከፈለጉ ደሞ በፒያሳ ከ20 ካሬ ጀምሮ በ900ሺ ቅድመ ክፍያ ያገኛሉ።

ይደውሉ ህልምዎን እውን ያድርጉ!
0938262649/0964741264
6👍2
በናይጄሪያ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸውን እህሎች በተመለከተ ልዩነት መኖሩ ተዘገበ።

ናይጄሪያ ከ2019 ጀምሮ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው እህሎችን መፍቀዷ የሚታወስ ሲሆን ከሰሞኑ አንድ የህክምና ባለሙያ በጉዳዩ ላይ ሃሳቡን ከሰጠ በኋላ ዳግም የህዝብ መከራከሪያ ሆኗል።

X በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገፅ ከ6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ባዩት ቪዲዮ ቢሊየነሩ ቢልጌትስ በዘረመል የተለወጡ እህሎች ላይ እንደሚሰራ እና በናይጄሪያ የጤና እና ምግብ ዘርፍ ላይ 2.8 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ማድረጉን ይገልፃል።

ከቪዲዮው በኋላ አንዳንዶች የውጪ ባለሃብቶች በአፍሪካ የምግብ ዘርፍ ላይ መሰማራታቸው እንደሚያሳስባቸው እና የአፍሪካን ህዝብ በሚበላው እና በሚያርሰው ነገር ዳግም ቅኝ መግዛት እና ባሪያ ማድረግ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ጉዳዩ ያሳሰበው የናይጄሪያ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው እህሎች ተቆጣጣሪ አካል እህሎቹ ለህዝብ ደህንነት እና ለአካባቢው ተስማሚ መሆናቸው በደንብ ይፈተሻል፤ የሚያሳስብ ነገር የለም ብሏል።

በናይጄሪያ ከ31 ሚሊየን ሰዎች በላይ የምግብ እርዳታ ሲሹ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው እህሎች ድርቅን በመቋቋማቸው ረገድ ለምግብ ዋስትና ጥሩ መፍትሄ ይሆናሉ የሚሉ ወገኖችም አሉ።

በሌላ በኩል የዘረመ ለውጥ የተደረገባቸውን እህሎች የሚያመርቱት በዋነኝነት በምዕራባውያን ድርጅቶች በመያዛቸው የምግብ አቅርቦትን በውጪ ኃይሎች ላይ እንዲመሰረት ያደርጋል የሚሉም አሉ።

በአፍሪካ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸውን ብዙ እህሎች በመፍቀድ ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን አልጄሪያ፣ ማዳጋስካር እና ዚምባቡዌ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው እህሎች እንዳይዘሩ ብሎም ወደ ሃገር እንዳይገቡ አግደዋል።

በኢትዮጵያም ጉዳዩ መከራከሪያ ሲሆን በቅርቡ በጉዳዩ ላይ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ምሁራዊ ክርክር ማድረጉ ይታወሳል።

በክርክሩ ወቅትም የዘረመል ለውጥ የተደረገበት 56 በመቶ የምርት ጭማሪ ያለው የበቆሎ ምርት ወደ ገበያ እንዲገባ መፈቀዱ መነገሩ ይታወሳል።

ለተጨማሪ መረጃ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ ሰርቶት የነበረው ዘገባ ከዚህ ያንብቡ።

Source: Africa News

@TikvahethMagazine
64😢11🤬5🤣3🔥2👏2
ቻይና የዓለም የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ትብብር ድርጅት እንዲመሰረት ሀሳብ አቀረበች።

በሻንጋይ መካሄድ በጀመረው ዓለም አቀፉ የሰው ሰራሽ አስተውህሎት ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ቺያንግ ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ለዕድገት ጉልህ ሚና ቢጫወትም የአለም ሃገራት በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ አክለውም እያደገ ባለው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ የችሎታ መለዋወጥ ላይ ማዕቀቦች መኖራቸው እና የቺፕስ እጥረት ያሉ ችግሮች መኖራቸውን አንስተው የአለም ሃገራት ሁሉ በትብብር መስራት አለባቸው ብለዋል።

ቻይና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ግኝቶች ሁሉም ሀገራት እና ኩባንያዎች እኩል የመጠቀም መብት እንዲኖራቸው ትፈልጋለች ሲሉ በዘርፉ የብቻ ውድድር መሆን የለበትም ሲሉ አሳስበዋል።

ቤጂንግ ልምዷን እና ምርቷን ለሌሎች ሀገራት በተለይም ለታዳጊ ወይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሀገሮች (Global South) ለማጋራት ፈቃደኛ መሆኗንም ገልጸዋል።

ቻይና በአለማችን ላይ ካሉ ሃገራት በቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ በጥልቀት እየሰራች እንዳለች ይታወቃል።

ቻይና በ2030 በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ዘርፍ ግንባር ቀደም ሃገር ለመሆን አቅዳ እየሰራች ስትገኝ በ2030 ሰው ሰራሽ አስተውህሎት የቻይና ኢኮኖሚ ላይ 600 ቢሊየን ዶላር በየአመቱ እንደሚጨምር ይጠበቃል።

በ2024 ቻይና 4500 ሰው ሰራሽ አስተውህሎት ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች የነበሯት ሲሆን ይህም የአለም 15 በመቶ ያህሉን እንደማለት ነው።

ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውህሎት ዘርፉ በእጅጉ እያደገ ሲመጣ የግል ዘርፉ ኢንቨስትመንትም በእጅጉ እየጨመረ መጥቷል።

በቻይና የግል ድርጅቶች ብቻ በጄኔሬቲቭ ኤ አይ ዘርፍ በ2025 ያደረጉት ኢንቨስትመንት 3.15 ቢሊየን ዶላር ሲደርስ በዘርፉ ያሰበችውን ዕቅድ ለማሳካት ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ታምኗል።

Source: Reuters , Al-Arabia, FORBES

@TikvahethMagazine
75👍12👎3🙏1🤣1
"የ50 እና 25 ሚሊየን ብር ሎተሪ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ተረክበዋል" - የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት

በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት "የ50 ሚሊዮን ብር የሎተሪ" እንዲሁም "በቶምቦላ ሎተሪ" ባለ ዕድለኞችን በዛሬው ዕለት ሽልማታቸውን አበርክቷል።

አገልግሎቱ ሥራውን ከጀመረበት ከ1954 ዓ,ም ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የሽልማት ጣራውን  ወደ 50 ሚሊዮን ብር በማድረግ ሽልማቶችን አበርክቷል።

ግንቦት 30/2017 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የሎተሪ ዕጣ ከ50 ሚሊዮን ብር ጀምሮ የ25 ሚሊዮን ፤ የ10 ሚሊዮን ፤ የ9 ሚሊዮን ፤  የ8 ሚሊዮን እና የተለያዩ የሚሊዮን ብር ዕጣዎችን የያዘ ነው።

የ50 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ የሆነችው እድለኛ ትውልድና ዕድገቷ ጎንደር ከተማ የሆነው ወጣቷ የሽቱ ምስጋናው ነች።

ወጣቷ፥ ከደብረ-ብርሀን 10ኪሎ ሜትር በምትርቀው ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስትያን ለንግስ ሄዳ በቆረጠችው የሚሊየን ትኬት የ50 ሚሊዮን ብር ዕድለኛ መሆን ችላለች።

አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ውስጥ በወር የ1500 ብር ተቀጥሮ የሚሰራው ካሳ አለሙ ደግሞ የ25 ሚለዮን ብር ዕጣ ባለእድለኛ ሆኗል።

በተለምዶ 24 በሚባለው አከባቢ ከአንድ ሎተሪ አድራሽ በ200 ብር የቆረጠው ሎተሪ ያሸልው ወጣት ባሸነፈው ብር ቤትና መኪና ለመግዛት ማቀዱን ገልጿል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሎተሪ አገልግሎት በቶምቦላ ሎተሪ ባለዕድለኛ የሆኑ የቤትና መኪና አሸናፊዎችንም ሽልማት ማስረከቡን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

አገልግሎቱ በቀጣይ በእንቁጠጣሽ ሎተሪ ከ66 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት በተለያዩ ዕጣዎች አጠቃሎ ለዕድለኞች እንደሚያቀርብ ገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@TikvahethMagazine
112👏17👎7🤔6🤣5👍1🔥1🕊1
#Somalia 🇸🇴

የሶማሊያው ፕረዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር አዛዥን ከሰልጣን ሊያነሱ እያሰቡ ስለመሆናቸው ተዘገበ።

ፕረዚደንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ ጦራቸው ከአልሸባብ ጋር ባለበት ውጊያ ሽንፈቶች እየገጠመው መሆኑን ተከትሎ የጦሩን አዛዥ ጀነራል ኦዶዋ ዩሱፍን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ማሰባቸው ነው የተሰማው።

በምትካቸው የወቅቱን የወደቦች ሚኒስትር አብዱልቃድር መሃመድ ኑር ጃማን ለመሾም ማሰባቸው አስበዋል ነው የተባለው።

መሐመድ ጃማ የፕሬዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድ እንደዚሁም የፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ጥብቅ ወዳጅ ነው ሲባል የእርሱ መሾም ቱርኪዬ በሶማሊያ ያላትን ተፅዕኖ እንደሚያሳድገው ተጠብቋል።

አብዱልቃድር መሐመድ ጃማ ከዚህ በፊት የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሰራ ሲሆን ከፕረዚዳንት ሃሰን ሼህ መሐሙድም በወቅቱ ይፋ ሳይሆን የሜጀር ጀነራልነት ማዕረግ ተሰጥቶታል።

አብዱልቃድር ጃማ የጦር አዛዥ ከሆነ ወትሮውንም ግለሰቡ ከመከላከያ ሚኒስትርነት እንዲነሳ ስትጠይቅ የነበረችውን አሜሪካ ከሶማሊያ ጉዳይ የሚገፋ ውሳኔ ሲሆን እንደ አዲስ የሶማሊያ ወዳጅ ሆና ብቅ ላለችው ቱርኪዬ ደግሞ ትልቅ ስኬት ይሆናል ተብሏል።

Source: Somali Guardian

@TikvahethMagazine
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
64🤣3🙏1
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://t.iss.one/samcomptech
8
በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሚመራው ጥምረት መንግስት መመስረቱን አስታወቀ።

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት 27ኛ ወሩን በያዘበት ወቅት በጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው ጥምረት መንግስት መስርቼያለሁ ብሏል።

እራሱን TASIS ሲል የጠራው ጥምረት 15 አባላት ያሉት የፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት ያለው ሲሆን ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ በፕሬዚዳንትነት ይመሩታል።

በተጨማሪ ጥምረቱ መሐመድ ሃሰንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሾሙን ገልጿል።

ጥምረቱ አላማው በፍትህ እና ነፃነት ላይ የተመሰረተችን ሱዳን መገንባት መሆኑን ገልጿል።

በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ይታወሳል።

በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተመሰረተው ጥምረት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሾሙ በተጨማሪ ለክልሎችም አስተዳዳሪዎችን መድቧል።

አሁን ባለው ተመድን ጨምሮ ሃገራት በሱዳን ጦር ለተመደቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል እድሪስ መንግስት እውቅና የሰጡ ከወራት በፊት ተመድ ሌላ መንግስት መመስረት ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ሲያስጠነቅቅ ነበር።

ሃገሪቷ በሁለት ኃይሎች ተከፋፍላ በምትመራው ሱዳን የሱዳን ጦር ለተመሰረተው መንግስት የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።

ሱዳን በ2023 ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ከገባች በኋላ በጦርነቱ ከ13 ሚሊየን ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ ከ15,000 በላይ ሰዎችም መምታቸው ይታወሳል።

Source: Al Jazeera, DW

@Tikvahethmagazine
41🕊11👎1🤔1
አልሸባብ ለሚፈፅማቸው ጥቃቶች የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለመጠቀም እያሰበ መሆኑ ተዘገበ።

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጣናው የደኅንነት ስጋት ሆኖ የቆየው አልሸባብ ለሚፈፅማቸው ጥቃቶች ድሮኖችን ለመጠቀም እያሰበ መሆኑ ሲሰማ ወታደራዊ ክንፉንም በአዲስ ማደራጀት መጀመሩ ተገልጿል።

"ጀባህ" በመባል የሚታወቀውን የአልሸባብ የወታደራዊ ክንፍ ለረጅም ዓመታት የመራው ያሲር ጂስ ከአመራርነቱ ተነስቶ ወደ ቡድኑ የደኅንነት ክፍል መወሰዱ ተሰምቷል።

ጀባህ የአልሸባብ ቁልፍ የወታደራዊ ክንፍ ሲሆን በተደጋሚ በሞቃዲሾ እና ኬንያ ጥቃት የሚፈፅም አልፎ አልፎ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያም ገብቶ ጥቃት ለመፈፀም የሚሞክር ክንፍ ስለመሆኑ ተገልጿል።

ከክንፉ መሪነት የተነሳው ያሲር ጂስ ቀጣይ ሥራውም አልሸባብ የጦር መሳሪያዎችን የሚያስገባባትን ወሳኝ መስመሮች ማጠናከር ነው ተብሏል።

ያሲር ጂስ በአልሸባብ ውስጥ ቁልፍ ከሚባሉት ሰዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የወቅቱ የሶማሊያ የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የአጎት ልጅም ነው።

አሜሪካ በ2022 ያሲንን በአለም አቀፍ አሸባሪነት ስትፈርጀው ያለበትን ለጠቆመም የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጅታ ነበር።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አልሸባብ ከየመኑ ሁቲ ጋር ጥምረት እየፈጠረ መሆኑ እና የድሮን ስልጠናዎችን እንደዚሁም የቴክኖሎጂ ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተሰምቷል።

እንደ ተመድ ዘገባ ከሆነ የመን ሄደው ስልጠና የወሰዱ የመጀመሪያ ዙር የአልሸባብ ሰልጣኞች በመስከረም 2024 ወደ ሶማሊያ ተመልሰዋል።

በተጨማሪም ከባህር ሽፍታዎች ጋር በመሆን መርከቦችን በማገት ለማስለቀቅ ከሚከፈለው ብር በኢኮኖሚ ራሱን እያጠናከረ መጥቷል።

ቡድኑ ከየመን ሁቲ ባገኘው ሥልጠናም ድሮንን ለጥቃት ለመጠቀም እያሰበ መሆኑ ሲሰማ የተደረገው የአመራር ለውጥም ይህንን የሎጅስቲክስ ስራ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

በተጨማሪ ከዚህ በፊት የሶማሊያ የደኅንነት ቢሮ ውስጥ ይሰራ የነበረው አብዲሳታር ኢሴ ከቱርኪዬ እና አሜሪካ የድሮን ስልጠናዎችን ከወሰደ በኋላ ወደ ቡድኑ የገባ ሲሆን አሁን የአልሸባብን የድሮን ፕሮግራም እየመራ ነው።

አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን እያጠናከረ ከዚህ በፊት ያጣቸውን ቦታዎች ዳግም እየተቆጣጠረ መሆኑ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን አሁን ድሮን መታጠቅ ከጀመረ የደኅንነት ችግር ባለበት ቀጣና ሌላ ስጋት እንደሚጨምር አያጠያይቅም ተብሎ ተሰግቷል።

Source: Horn Observer, Horseed Media

@TikvahethMagazine
59🤔14🤯7🤬7
ጋና ክሪፕቶከረንሲ ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት ልትጀምር ነው።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና እያደገ ከመጣው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ ፍላጎት ጋር በተያያዘ እና ከመገበያያው ለመጠቀም እንድትችል ክሪፕቶከረንሲ ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት ትጀምራለች ተብሏል።

የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የህግ ማዕቀፉን አዘጋጅቶ መጨረሱን እና ለፓርላማው በመስከረም ወር ቀርቦ እንደሚፀድቅ የባንኩ ገዢ ገልፀዋል።

የባንኩ ገዢ ጆንሰን አሲያማ "በጨዋታው ወደኋላ ቀርተናል፤ የብዙ ሃገራት የኢኮኖሚ ተዋናዮች ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ መፈፀም ጀምረዋል" በማለት የህግ ማዕቀፍ መኖሩ ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።

በጋና ከሐምሌ 2023- ሰኔ 2024 ብቻ አጠቃላይ የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሩ 3 ቢሊየን ዶላር የነበረ ሲሆን 3 ሚሊየን ወጣቶቿ ወይም 17 በመቶ ያህል ህዝቧ ይህንን መገበያያ ይጠቀማል ተብሏል።

ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ከ2023-2024 አጠቃላይ የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሩ 125 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከዚህ ውስጥ 59 ቢሊየን ዶላሩ የናይጄሪያ ነው።

በአህጉሪቱ በርካታ ሀገራት የክሪፕቶከረንሲን የተመለከተ ፈቃድ እና ቁጥጥር የሌላቸው ሲሆን አሁን አሁን በርካታ ማዕከላዊ ባንኮች በራቸውን እየከፈቱ ይገኛሉ።

ፈቃድ የሰጡ ሃገራት መገበያያ ገንዘቡን ዜጎች በኃላፊነት እንዲጠቀሙ ከማድረግ በተጨማሪ ታክስ በመጣል ገቢ እየሰበሰቡ ይገኛሉ።

ናይጀሪያ በ2023 ክሪፕቶከረንሲ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በማንሳት ፈቃድ መስጠት ስትጀምር፤ ሌላኛዋ ሃገር ደቡብ አፍሪካ ከ59 ለሚበልጡ የክሪፕቶከረንሲ ድርጅቶች ፈቃድ ሰጥታለች።

ኬንያም በአህጉሪቱ ክሪፕቶከረንሲን ለመጠቀም እየሰሩ ካሉ ሃገራት መካከል ስትገኝ ህግ አርቅቃ እስኪፀድቅ እየጠበቀች ነው።

በአፍሪካ በተለይ ወጣቱ ህይወቱን በክሪፕቶከረንሲዎች ላይ እየመሰረተ የመጣ ሲሆን በ2025 መጨረሻ አህጉሪቱ ከዚሁ መገበያያ ገንዘብም 2.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።

Source: Bloomberg, CryptoNews

@TikvahEthMagazine
52👍17🕊3🔥2👏2🤔2