TIKVAH-MAGAZINE
197K subscribers
20.3K photos
353 videos
70 files
2.56K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
#SamiTech

አዳዲስ ላፕቶፕች ከአንድ ዓመት ዋስትና ጋር!!
@samcomptech

በጥራት፣ በብራንድና በባትሪ ቆይታ አስተማማኝ የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ላፕቶፖች በፈለጉት ስክሪን መጠን፣ ኮር አይ እና ጀነሬሽን አሉን።

ላፕቶፕ ከመገዛትዎ በፊት ማወቅ ያለባችሁን ወሳኝ ነገሮች እናስረዳለን። በላፕቶፖቻችን ጥራት ላይ አንደራደርም!

ለቢሮዎች፣ ለተማሪዎች፣ ለዲዛይን ባለሙያዎች፣ ለጌመሮች ወ.ዘ.ተ. ሁሉም አሉን።

የዕቃዎች ዋጋ፣ ዓይነት እና አድራሻ ለማግኘት 👉 @samcomptech

@sww2844

0928442662 / 0940141114

Telgram

      👇
https://t.iss.one/samcomptech
19👎1
በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሚመራው ጥምረት መንግስት መመስረቱን አስታወቀ።

የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት 27ኛ ወሩን በያዘበት ወቅት በጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ የሚመራው ጥምረት መንግስት መስርቼያለሁ ብሏል።

እራሱን TASIS ሲል የጠራው ጥምረት 15 አባላት ያሉት የፕሬዚዳንታዊ ምክር ቤት ያለው ሲሆን ጀነራል ሃምዳን ዳጋሎ በፕሬዚዳንትነት ይመሩታል።

በተጨማሪ ጥምረቱ መሐመድ ሃሰንን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሾሙን ገልጿል።

ጥምረቱ አላማው በፍትህ እና ነፃነት ላይ የተመሰረተችን ሱዳን መገንባት መሆኑን ገልጿል።

በጀነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የሚመራው የሱዳን ጦር ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር መሾሙ ይታወሳል።

በሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል የተመሰረተው ጥምረት ጠቅላይ ሚኒስትር ከመሾሙ በተጨማሪ ለክልሎችም አስተዳዳሪዎችን መድቧል።

አሁን ባለው ተመድን ጨምሮ ሃገራት በሱዳን ጦር ለተመደቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል እድሪስ መንግስት እውቅና የሰጡ ከወራት በፊት ተመድ ሌላ መንግስት መመስረት ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ሲያስጠነቅቅ ነበር።

ሃገሪቷ በሁለት ኃይሎች ተከፋፍላ በምትመራው ሱዳን የሱዳን ጦር ለተመሰረተው መንግስት የሰጠው ይፋዊ ምላሽ የለም።

ሱዳን በ2023 ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ከገባች በኋላ በጦርነቱ ከ13 ሚሊየን ሰዎች በላይ ሲፈናቀሉ ከ15,000 በላይ ሰዎችም መምታቸው ይታወሳል።

Source: Al Jazeera, DW

@Tikvahethmagazine
54🕊12🤔2👎1
አልሸባብ ለሚፈፅማቸው ጥቃቶች የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለመጠቀም እያሰበ መሆኑ ተዘገበ።

ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት የቀጣናው የደኅንነት ስጋት ሆኖ የቆየው አልሸባብ ለሚፈፅማቸው ጥቃቶች ድሮኖችን ለመጠቀም እያሰበ መሆኑ ሲሰማ ወታደራዊ ክንፉንም በአዲስ ማደራጀት መጀመሩ ተገልጿል።

"ጀባህ" በመባል የሚታወቀውን የአልሸባብ የወታደራዊ ክንፍ ለረጅም ዓመታት የመራው ያሲር ጂስ ከአመራርነቱ ተነስቶ ወደ ቡድኑ የደኅንነት ክፍል መወሰዱ ተሰምቷል።

ጀባህ የአልሸባብ ቁልፍ የወታደራዊ ክንፍ ሲሆን በተደጋሚ በሞቃዲሾ እና ኬንያ ጥቃት የሚፈፅም አልፎ አልፎ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያም ገብቶ ጥቃት ለመፈፀም የሚሞክር ክንፍ ስለመሆኑ ተገልጿል።

ከክንፉ መሪነት የተነሳው ያሲር ጂስ ቀጣይ ሥራውም አልሸባብ የጦር መሳሪያዎችን የሚያስገባባትን ወሳኝ መስመሮች ማጠናከር ነው ተብሏል።

ያሲር ጂስ በአልሸባብ ውስጥ ቁልፍ ከሚባሉት ሰዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የወቅቱ የሶማሊያ የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የአጎት ልጅም ነው።

አሜሪካ በ2022 ያሲንን በአለም አቀፍ አሸባሪነት ስትፈርጀው ያለበትን ለጠቆመም የ5 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጅታ ነበር።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ አልሸባብ ከየመኑ ሁቲ ጋር ጥምረት እየፈጠረ መሆኑ እና የድሮን ስልጠናዎችን እንደዚሁም የቴክኖሎጂ ድጋፍ እያገኘ መሆኑ ተሰምቷል።

እንደ ተመድ ዘገባ ከሆነ የመን ሄደው ስልጠና የወሰዱ የመጀመሪያ ዙር የአልሸባብ ሰልጣኞች በመስከረም 2024 ወደ ሶማሊያ ተመልሰዋል።

በተጨማሪም ከባህር ሽፍታዎች ጋር በመሆን መርከቦችን በማገት ለማስለቀቅ ከሚከፈለው ብር በኢኮኖሚ ራሱን እያጠናከረ መጥቷል።

ቡድኑ ከየመን ሁቲ ባገኘው ሥልጠናም ድሮንን ለጥቃት ለመጠቀም እያሰበ መሆኑ ሲሰማ የተደረገው የአመራር ለውጥም ይህንን የሎጅስቲክስ ስራ የሚያግዝ ነው ተብሏል።

በተጨማሪ ከዚህ በፊት የሶማሊያ የደኅንነት ቢሮ ውስጥ ይሰራ የነበረው አብዲሳታር ኢሴ ከቱርኪዬ እና አሜሪካ የድሮን ስልጠናዎችን ከወሰደ በኋላ ወደ ቡድኑ የገባ ሲሆን አሁን የአልሸባብን የድሮን ፕሮግራም እየመራ ነው።

አልሸባብ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሱን እያጠናከረ ከዚህ በፊት ያጣቸውን ቦታዎች ዳግም እየተቆጣጠረ መሆኑ ሲዘገብ የቆየ ሲሆን አሁን ድሮን መታጠቅ ከጀመረ የደኅንነት ችግር ባለበት ቀጣና ሌላ ስጋት እንደሚጨምር አያጠያይቅም ተብሎ ተሰግቷል።

Source: Horn Observer, Horseed Media

@TikvahethMagazine
85🤔17🤯9🤬7👍2🕊1
ጋና ክሪፕቶከረንሲ ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት ልትጀምር ነው።

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና እያደገ ከመጣው የዲጂታል መገበያያ ገንዘብ ፍላጎት ጋር በተያያዘ እና ከመገበያያው ለመጠቀም እንድትችል ክሪፕቶከረንሲ ላይ ለሚሰሩ ድርጅቶች ፈቃድ መስጠት ትጀምራለች ተብሏል።

የሀገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ የህግ ማዕቀፉን አዘጋጅቶ መጨረሱን እና ለፓርላማው በመስከረም ወር ቀርቦ እንደሚፀድቅ የባንኩ ገዢ ገልፀዋል።

የባንኩ ገዢ ጆንሰን አሲያማ "በጨዋታው ወደኋላ ቀርተናል፤ የብዙ ሃገራት የኢኮኖሚ ተዋናዮች ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ መፈፀም ጀምረዋል" በማለት የህግ ማዕቀፍ መኖሩ ለውጥ እንደሚያመጣ ተናግረዋል።

በጋና ከሐምሌ 2023- ሰኔ 2024 ብቻ አጠቃላይ የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሩ 3 ቢሊየን ዶላር የነበረ ሲሆን 3 ሚሊየን ወጣቶቿ ወይም 17 በመቶ ያህል ህዝቧ ይህንን መገበያያ ይጠቀማል ተብሏል።

ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት ከ2023-2024 አጠቃላይ የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሩ 125 ቢሊየን ዶላር ነበር። ከዚህ ውስጥ 59 ቢሊየን ዶላሩ የናይጄሪያ ነው።

በአህጉሪቱ በርካታ ሀገራት የክሪፕቶከረንሲን የተመለከተ ፈቃድ እና ቁጥጥር የሌላቸው ሲሆን አሁን አሁን በርካታ ማዕከላዊ ባንኮች በራቸውን እየከፈቱ ይገኛሉ።

ፈቃድ የሰጡ ሃገራት መገበያያ ገንዘቡን ዜጎች በኃላፊነት እንዲጠቀሙ ከማድረግ በተጨማሪ ታክስ በመጣል ገቢ እየሰበሰቡ ይገኛሉ።

ናይጀሪያ በ2023 ክሪፕቶከረንሲ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በማንሳት ፈቃድ መስጠት ስትጀምር፤ ሌላኛዋ ሃገር ደቡብ አፍሪካ ከ59 ለሚበልጡ የክሪፕቶከረንሲ ድርጅቶች ፈቃድ ሰጥታለች።

ኬንያም በአህጉሪቱ ክሪፕቶከረንሲን ለመጠቀም እየሰሩ ካሉ ሃገራት መካከል ስትገኝ ህግ አርቅቃ እስኪፀድቅ እየጠበቀች ነው።

በአፍሪካ በተለይ ወጣቱ ህይወቱን በክሪፕቶከረንሲዎች ላይ እየመሰረተ የመጣ ሲሆን በ2025 መጨረሻ አህጉሪቱ ከዚሁ መገበያያ ገንዘብም 2.9 ቢሊየን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተብሎ ይጠበቃል።

Source: Bloomberg, CryptoNews

@TikvahEthMagazine
85👍18👏6🤔4🔥3🕊3
በምስራቃዊ ኮንጎ በሚገኝ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ላይ በተፈፀመ ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ተገደሉ።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ ኮማንዳ ከተማ በሚገኝ ቤተክርስቲያን በተፈፀመ የሽብር ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ሲገደሉ ሃላፊነቱንም እስላሚክ ስቴት (ISIS) ወስዷል።

ጥቃቱን የፈፀመው እራሱን ADF ብሎ የሚጠራው እና በአይ ኤስ አይ ኤስ የሚደገፈው ቡድን መሆኑ ሲሆን ከቤተክርስቲያኒቱ በተጨማሪ በዙሪያው ባሉ ቤቶች እና ሱቆች ላይም ጥቃት አድርሷል

ADF በ1990ዎቹ በኡጋንዳው ፕረዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የተበሳጩ ሰዎች የመሰረቱት ድርጅት የነበረ ቢሆንም በኡጋንዳ የፀጥታ ኃይሎች ጥቃት ሲበዛበት እራሱን በ2002 ወደ ኮንጎ ያስገባ ቡድን ነበር።

የኮንጎ የፀጥታ ኃይሎች ታጣቂውን ለማጥፋት ቢሞክሩም ከ2019 ጀምሮ ከISIS ጋር አጋርነት በመፍጠር የሺዎችን ህይወት ነጥቋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው አማኞቹ ለፀሎት በተሰበሰቡበት ሰዓት ሲሆን ከተገደሉት ሰዎች መካከል ዘጠኙ ህፃናት ናቸው ተብሏል።

ከ130 በላይ ታጣቂ ቡድኖች ይገኙባታል በምትባለዋ ኮንጎ የሽብር ጥቃቶች በተደጋጋሚ የሚፈፀሙ ሲሆን ባለፈው የካቲት በተፈፀመ ጥቃትም 23 ሰዎች ተገድለዋል።

በአሁኑ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ከመቃጠላቸው የተነሳ ከጥቂቶቹ በስተቀር ማንነታቸው እንዳልተለየና ሥርዓተ ቀብራቸውን በጋራ ተፈጽሟል።

በውድ ማዕድናት ኃብት የበለፀገችው ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኦፍ ኮንጎ በቅርቡ በሩዋንዳ ከሚደገፉት የM23 ታጣቂዎች ጋር ውጊያ ውስጥ እንደነበረች ይታወሳል።

በተደጋጋሚ በሚገጥማትም የእርስ በእርስ ግጭተ የተነሳ ውድ ኃብቷን ሳትጠቀም ዜጎቿ በሰላም እጦት እና በችግር መኖራቸውን ቀጥለዋል።

Source: DW, ALARABIYA

@TikvahethMagazine
110😢96💔19🕊8🤬7👍2🤯1
በጥራት እና በፍጥነት 7 ሳይቶች ያስረከበው ቴምር ፕሮፐርቲ አሁን ላይ ደሞ ለእርስዎ ለመኖሪያነት ምቹ በሆኑ አካባቢዎች

በሳርቤትበፒያሳበአያትበሶማሌተራበጋርመንት የመኖሪያ አፓርትመንት ቤቶችን ከባለ 1 እስከ ባለ3 መኝታ ከ63 ካሬ -146ካሬ በ10% ቅድመ ክፍያ ማለትም ከ693 ሺብር ጀምሮ በሽያጭ ላይ እንገኛለን።

👉የ25% ልዩ ቅናሽም ለእርስዎ አዘጋጅተናል።
👉ለንግድ የሚሆኑ ሱቆች ከፈለጉ ደሞ በፒያሳ ከ20 ካሬ ጀምሮ በ900ሺ ቅድመ ክፍያ ያገኛሉ።

ይደውሉ ህልምዎን እውን ያድርጉ!
0938262649/0964741264
13👍2
ታንዛኒያ የውጪ ሃገር ዜጎች በ15 የቢዝነስ ዘርፎች መሰማራት እንዳይችሉ የሚያስችል ህግ አውጥታለች።

የታንዛኒያ መንግስት የሃገሩን ዜጎች ለመጠበቅ ሲል የውጪ ሃገራት ዜጎች በትንሽ እና መካከለኛ የቢዝነስ ዘርፎች እንዳይሳተፉ ከልክሏል።

በሃገሪቱ የንግድ ሚኒስትር የተፈረመው ደብዳቤ በተለምዶ የታንዛኒያ ዜጎች በብዛት የሚሰማሩባቸው የቢዝነስ ዘርፎች ላይ የውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ ይከለክላል።

ከተከለከሉት መካከል የችርቻሮ ንግድ፣ የሞባይል ገንዘብ ማስተላለፊያ ፣ የሞባይል እና ኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የፀጉር እና የውበት ስራ እንደዚሁም የአካባቢ ፅዳት ይገኙበታል።

በተጨማሪ የድለላ፣የፖስታ አገልግሎት ፣ አስጎብኚ እንደዚሁም የሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ማቋቋም እና መምራት ተከልክለዋል።

ውሳኔው የተወሰነው ብዙ ታንዛኒያውያን በሚሳተፉበት ዘርፍ ላይ ከውጪ ዜጎች የሚኖርን ወድድር ለመቀነስ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ የታንዛኒያ ውሳኔ ከኬንያ ተቃውሞ የገጠመው ሲሆን ኬንያ በ8 ሃገራት መካከል የተፈረመውን የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ዜጎች በነፃነት የመንቀሳቀስ እና የመስራት መብት ይገድባል ብላለች።

የኬንያ ብሔራዊ የንግድ ኮሚቴ ሊቀመንበር በርናርድ ሺናሊ ኬንያ ተመሳሳዩን እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠንቅቀው፤ ከታንዛኒያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቆም እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በታንዛኒያ ከ250,000 በላይ ኬንያውያን እንደሚኖሩ እና እንደሚሰሩ ተገልጿል።

በሌሎች የአፍሪካ ሃገራትም ተግባሩ የተለመደ ሲሆን በኡጋንዳ የውጪ ሃገር ዜጋ ቢዝነስ ለመጀመር በትንሹ 250,000 ዶላር ኢንቨስት ማድረግ አለበት።

በተመሳሳይ ሩዋንዳ የውጪ ዜጎች የትራንስፖርት ዘርፉን ጨምሮ የተመረጡ ዘርፎች ላይ የውጪ ዜጎች እንዳይሳተፉ እገዳ አስቀምጣለች።

Source: NilePost, BBC

@tikvahethMagazine
92👍6👏3🙏1
በቡሩንዲ በነዳጅ እጥረት እና በትራፊክ ቅጣቶች የተማረሩ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አድማ ላይ ናቸው ተባለ።

በቡሩንዲ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መንግስት ያስቀመጠው ታሪፍ ከነዳጅ ወጪው ጋር የማይነፃፀር በመሆኑ እና በቅጣቶች በመማረራቸው አገልግሎት ማቆማቸው ተሰምቷል።

የረጅም መንገድ አሽከርካሪዎች መንግስት ያስቀመጠው የክፍያ ተመን ከነዳጅ ወጪው አንፃር የማይመጣጠን ስለሆነ ከተመኑ በላይ ክፍያ እያስከፈሉ ነው ተብሏል።

ይኸንንም ተከትሎ አሽከርካሪዎቹ ከተመን በላይ በማስከፈላቸው በትራፊኮች እስከ 1 ሚሊየን የቡሩንዲ ፍራንክ ድረስ እየተቀጣን ነው ብለዋል።

አሽከርካሪዎቹ መንግስት ያስቀመጠው የጉዞ ተመን ከእውነታ የራቀ ነው ሲሉ ባለው የነዳጅ እጥረት የተነሳ ነዳጅ ከጥቁር ገበያው ላይ በተጋነነ ዋጋ እየገዙ መሆኑን ገልፀዋል።

ቡሩንዲ ባጋጠማት የውጪ ምንዛሬ እጥረት እና ሙስና የተነሳ ነዳጅ ከውጪ እንደፈለገችው ማስገባት ያልቻለች ሲሆን ባለፉት 3 አመታት በከባድ የነዳጅ እጥረት እየተፈተነች ትገኛለች።

በዚህም የተነሳ አሽከርካሪዎች ነዳጅ በጥቁር ገበያው ከታንዛኒያ 1 ሊትር ነዳጅ በ9000 የቡሩንዲ ፍራንክ ከተገዛ በኋላ ወደ ቡሩንዲ ገብቶ በ17,000 የቡሩንዲ ፍራንክ ሲሸጥ እየገዙ መሆኑን ገልፀዋል።

ሰዎችም አንድ ጉዞ ለማድረግ እስከ 100,000 የቡሩንዲ ፍራንክ እያወጡ እንደሆነ ሲዘገብ በአንድ ወቅት ስለ ጉዳዩ የተጠየቁት የሃገሪቱ ፕሬዚዳንትም መፍትሄን ከመፈለግ ይልቅ ዜጎች በዚህ የቀውስ ጊዜ ፈጣሪን እንዲጠይቁ መናገራቸው መነጋገሪያ መሆኑ ይታወሳል።

Source: SOS media, Breaking Burundi, Community Voice

@TikvahethMagazine
102🤣20👏8😢8👍6👎2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍በደማቁአ ፒያሳ

🎁 ከመንግስት ጋር በመተባበር በከተማችን አዲስ አበባ የመጀመሪያውን ግዙፍ እና ቅንጡ የገበያ ማዕከል በፒያሳ
ከ Temer real estate ሱቅ ከነ ገቢያው ይዘንሎት መተናል!

ለልማት ተነሺዎች እና ለመርካቶ ነጋዴዎች
✍️ 2B+G+5  luxury Mall
ከ 3,900,000 ጠቅላላ ዋጋ ጀምሮ
✍️ ቅድመ ክፍያ 900  ሺህ
✍️ ከ20 ካሬ ጀምሮ
✍️ በ1/6 ወር መረከቢያ ጊዜ


❇️ ሞሉ የሚሰጣቸው አገልግሎት

☑️ Elevator # 4
☑️ Escalators # 6
☑️ Back up Generetor
☑️ Terrace
☑️ Cinema House
☑️ Restaurant, Cafe,
☑️ water park

☎️ ለበለጠ መረጃ :-

+2519 23 93 11 30 ይደወሉ.
14👎1😢1
Want to build a global tech career right from Ethiopia?

Tikvah Ethiopia families, join us for an exciting freelancing workshop led by a Senior Software Engineer, Temkin "Chapi" Mengistu (@chapidevtalks), with real-world experience working with international clients.

What’s it about?

Discover how to start and grow your career in freelancing as a tech professional, from building your profile to finding clients, managing projects, and getting paid globally.

Who is it for?

You
ng people who are involved in the tech space, whether you're just starting or looking to take your freelance game to the next level.

What you’ll learn:

▪️How freelancing works in the tech industry
▪️Where and how to find freelance jobs
▪️Building your profile and pricing your work
▪️Project management and client communication

📅 Date: Saturday, August 2, 2025
Time: 9:00 AM
📍 Location: Addis Ababa, around 22
▪️Cost: FREE!

Organized by: Tikvah Ethiopia

🔗Limited spots available – register now!

https://forms.gle/wu3xPSNskKKDmo8k7
16🔥5👍2
ሳፋሪኮም እና ፔይፓል ኤምፔሳን ከአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ጋር ለማስተሳሰር ተስማሙ።

ሳፋሪኮም ከፔይፓል ጋር በመሆን ኤምፔሳን በፔይፓል አለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ውስጥ ለማካተት አጋር ሲሆን በአጋርነቱ መሰረት 35 ሚሊየን የኤምፔሳ ደንበኞች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል።

በአጋርነቱ መሰረትም ተጠቃሚዎች የፔይፓል አካውንታቸውን ከኤም ፔሳ ጋር በማስተሳሰር የገንዘብ ዝውውሮችን በቀላሉ ማከናወን ይችላሉ ተብሏል።

ለጊዜው አገልግሎቱ በኬንያ በሚገኙ ተጠቃሚዎች ላይ የሚጀመር ሲሆን በሂደት ኤም ፔሳ ወደሚሰራበቸው ሌሎች አካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል።

ሳፋሪኮም በኤምፔሳ ሱፐር አፑ ሰዎች በቀጥታ ከፔይፓል ገንዘብ ማውጣት እንዲችሉ የሚያስችል አማራጭንም አካቷል።

ሰዎች በቀጥታ የፔይፓል ገንዘባቸውን ከኤምፔሳ ማውጣታቸው በተለያየ መንገድ የሰሩትን ገንዘብ ሳይንዛዛ በቀጥታ እንዲያወጡ ያስችላል።

በተጨማሪ ተጠቃሚዎች ሁለቱን አካውንቶች በማስተሳሰር በቀላሉ የገንዘብ ዝውውሮችን መፈፀም ይችላሉ ተብሏል።

ኤም ፔሳ በአፍሪካ ቀዳሚው የሞባይል ገንዘብ መተግበሪያ እንደሆነ ሲዘገብ ከ50 ሚሊየን በላይ ደንበኞችን በማፍራት በየዕለቱ ከ1.1 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ዝውውሮችንም ያሳልጣል።

ፔይፓል በአለም አቀፍ ደረጃ ከ400 ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎች ሲኖሩት በተለይ ለኦንላይን ስራዎች ዋነኛ የክፍያ አማራጭ ሆኗል።

በኬንያ በሚገኘው ኤምፔሳ የሚጀምረው አገልግሎት ወደ ኢትዮጵያም እንደሚመጣ ሲጠበቅ በርካታ ወጣቶች በኦንላይን ስራዎች ያገኙትን ገንዘብ በቀላሉ እንዲያወጡ ያስችላል።

Source: Tech Point, Tech Africa

@TikvahethMagazine
👏16548👍10🔥2🕊2
"በየቀኑ ለ15 ደቂቃ ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግ የልብ ጤናን በማሻሻል ለሞት የመጋለጥ ዕድልን በ20 በመቶ ይቀንሳል" - ጥናት

የአሜሪካ ተመራማሪዎች 79,850 ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አካባቢዎች የተወሰዱ ወጣቶች ላይ ባደረጉት ጥናት ቀስ ብሎ ለ3 ሰዓት የእግር ጉዞ ከማድረግ ይልቅ ለ15 ደቂቃ የሚደረግ ፈጠን ያለ የእግር ጉዞ ይበልጥ ለጤና ይጠቅማል የሚል መደምደሚያ ላይ ደርሰዋል።

ተመራማሪዎቹ የእግር ጉዞ በተለይ ፈጠን ያለ የእግር ጉዞ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሰዎች ከልብ ህመም በመጠበቅ ውስጥ ጉልህ ድርሻ የሚኖረው እንቅስቃሴ ነው ብለዋል።

የጥናቱ ተመራማሪዎች ከ2002-2019 ባለው የ17 አመታት መረጃ ላይ ተመስርተው ባደረጉት ጥናት በየቀኑ በትንሹ ለ15 ደቂቃ ፈጠን ያለ የእግር ጉዞ ማድረግ ለሞት የመጋለጥ ዕድልን በ20 በመቶ እንደሚቀንስ አግኝተናል ብለዋል።

የዓለም የጤና ድርጅት የሰውነት እንቅስቃሴ ካለማድረግ የተነሳ በየዓመቱ 2 ሚሊየን ሰዎች እንደሚሞቱ የገለፀ ሲሆን እንደ ልብ ህመም ላሉ በሽታዎችም ከሚያጋልጡት ውስጥ ዋነኛው ነው።

በእንግሊዝ ብቻ በየሳምንቱ 420 ጎልማሶች በልብ ህመም የተነሳ ይሞታሉ ተብሏል።

ተመራማሪዎች እና የጤና ባለሙያዎች ሰዎች ራሳቸውን ከበሽታ ለመጠበቅ እና የሞት ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ሲመክሩ ሁሌም የሚታይ ጉዳይ ነው።

Source: Daily Mail

@TikvahethMagazine
71🤣22👎2
"ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዷል" - ቡናና ሻይ ባለስልጣን

በ2018 የስራ ዘመን ከቡና፣ ሻይና ቅ/ቅመም ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት መታቀዱን የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 470ሺህ ቶን ቡና በመላክ ከ2.65 ቢሊየን ዶላር በላይ የተገኘበት መሆኑ መገለጹ ይታወሳል።

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 ዕቅድ በተገመገመበት ወቅት እንደገለጹት፥ በተያዘው በጀት ዓመት ከ600ሺህ ቶን ቡና ለገበያ በማቅረብ ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ ለማግኘት ታቅዷል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ለክልል የስራ ኃላፊዎች ባቀረቡት ጥሪ፤ EUDR/ አውሮፓ ህብረት ያወጣውን ከደን ጭፍጨፋ ነጻ የሆነ ምርት የመግዛት መመሪያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ፣ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተመሰረተ፣ በጥራትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ቡና ወደ ገበያ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡

@TikvahethMagazine
42👎14
"ለ7 መምህራን እውቅና ሰጥተናል" - ላሳልያን የሽልማትና ድጋፍ ማህበር

ላሳልያን የሽልማትና ድጋፍ ማህበር ከ20 እስከ 40 አመታት እና ከዚያ በላይ በመምህርነት ሙያ ላገለገሉ 7 መምህራን እውቅ እና ለእያንዳንዳቸው የ10ሺህ ብር ሽልማት መስጠቱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የማህበሩ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዶክተር ሀብታሙ አለሙ "እውቅና የተሰጣቸው ለረጅም አመት ላስተማሩ፣ ጥሩ ስነምግባር ላላቸው፣ ለተማሪዎች ጥሩ ውጤት ማምጣት እና ጥሩ ስነምግባር መላበስ እንዲሁም ከትምህርት ውጭ መፅሀፍቶችን በማሳተም በርካታ አስተዋጽኦ ላበረከቱ መምህራኖች ነው" ብለዋል።

ይህ ተግባር ለ3ኛ ጊዜ መካሄዱን እና ከዚህ ቀደም በሁለት ዙር ለ10 መምህራኖች እውቅና መስጠታቸውን ጨምረው ተናግረዋል።

እውቅና ከተሰጣቸው መምህራኖች ውስጥ 5ቱ ከመንግስት ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ከግል ትምህርት ቤት ናቸው። ማኅበሩ፥ ለእያንዳንዳቸው የ10ሺህ ብር ሽልማትና ለሁሉም ዋንጫ መሸለሙን ገልጾልናል።

በተጨማሪ ማህበሩ ተቋቁሞ ስራ ከጀመረበት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ከ2ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ መለገሱንና በዘንድሮው አመትም በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ 350 ለሚሆኑ ተማሪዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ ዶ/ር ሃብታሙ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ማኅበሩ በቀረጸው አዲስ ፕሮጀክትም "ወደ 9ኛ ክፍል በጥሩ ውጤት በማምጣት ያለፉ ተማሪዎችን ፈትነን እና አወዳድረን 10 ለሚሆኑ ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ሙሉ ወጫቸውን ሸፍነን በግል ትምህርት ቤት እንድማሩ ለማድረግ ምዝውገባ እያካሄድን ነው" ሲሉ ነው የተናገሩት።

@TikvahethMagazine
33🤣16👍4👎2🙏2🤔1💔1
#ጥቆማ

ንባብ ለህይወት ፕሮጀክት ያዘጋጀው 10ኛው አመታዊ "ንባብ ለህይወት" የመጽሐፍት አውደ ርዕይ በዛሬው ዕለት በይፋ ተከፍቷል።

እስከ ሀምሌ 27/2017 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ ዓውደ-ርዕይ ላይ በርካታ አዳዲስ መጽሐፍቶች እንደሚመረቁ እና መጽሐፍቶችን በቅናሽ ማግኘት እንደሚቻል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

@tikvahethmagazine
👍2312🔥1🤔1
ሶማሊያ ከ34 ዓመት በኋላ አየር መንገዷን ወደ ስራ ልትመልስ መሆኗን አስታወቀች።

ሶማሊያ ከ34 አመታት በኋላ አየር መንገዷ ወደ ስራ ሊመለስ መሆኗን ስትገልፅ ሁለት የኤይርባስ A320 አውሮፕላኖችንም መግዛቷን አስታውቃለች።

የሃገሪቱ የትራንስፖርት እና ሲቪል አቪየሽን ሚኒስትር መሐመድ ፋራህ የአውሮፕላን ግዢው መፈፀሙን አረጋግጠው በቀጣይ ሁለት ወራት ወደ ስራ ይገባሉ ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም"ከ34 አመታት በፊት ስራ ያቆመውን የሶማሊ አየር መንገድን መልሰነዋል፤ ዛሬ በሁለት አውሮፕላን የጀመርነው ሶስት እያለ እየጨመረ ይሄዳል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ሚኒስትሩ" በመላው አለም ያሉ የሶማሊ ማህበረሰብ የሌሎችን አየር መንገድ በመጠቀም ገንዘብ ያወጣሉ" ሲሉ የስራ ዕድል በመፍጠር እና በውጪ ሃገራት አየር መንገዶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ የሶማሊያን ኢኮኖሚ ያግዛል ብለዋል።

የሶማሊያ አየር መንገድ ምስረታውን በ1964 ያደረገ ሲሆን በ1991 በሃገሪቱ የእርስ በእርስ ጦርነት ከተከሰተ በኋላ ስራውን አቁሟል።

የሶማሊያ አየር መንገድ ዳግም ወደ ስራ መመልስም በጦርነት የላሸቀውን ኢኮኖሚ እንዲያንሰራራ ከማገዙ በተጨማሪ የፈረሱ ብሔራዊ ተቋማት ወደ ስራ በመመለስ ረገድ የተጀመረውን ስራ የሚያጠናክር ነው ተብሏል።

Source: Eastleigh Voice

@tikvahethmagazine
85🤣53👍16🤯4