Tikvah Discussion and Poll
1.46K subscribers
5 photos
Download Telegram
"Tikvah-Ethiopia"

ይህ የቲክቫህ ገፅ ፥ አዲሱን የቴሌግራም Voice Chat መጀመርን ተከትሎ የተከፈተ ሲሆን ፤ በዋነኝነት የቲክቫህ አባላት የድምፅ ውይይት እንዲያደርጉ የሚያስችል ነው።

ውይይቶቹ የተለያዩ ሀገራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮሚያዊ አጀንዳዎች የሚያተኩሩ ፣ አሁን ያለውን የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ወደተሻለ ደረጃ ፣ ከመሰዳደቢያነት ወደ ተቀራርቦ መነጋገሪያ መድረክ እና ለችግሮች መፍትሄ መፈለጊያ ይሆን ዘንድ የሚረዳ ነው።

በተጨማሪ በድምፅ መስጫ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ድምፅ እንዲሰጥባቸው (በአባላት ጥቆማ ) ፥ የሰዎችን አስተያየት የምንመለከትበት መድረክ ይሆናል።

@TikvahPollandDiscussion
ሀሳብን ለመግለፅ/ለመወያየት ፦

- ሰዎችን ማንቋሸሽ
- ከሃሳባችን ይልቅ ማንነታችን፣ ብሄራቸውን ጥርቶ መዝለፍ
- ሰዎችን በሚከተሉት እምነት ማንቋሸሽ
- አብሮነትን የሚጎዱ ቃላትን መጠቀም
- ከሰውነት ይልቅ ሌሎች ጉዳዮችን ማስቀደም በፍፁም የተከለከለ ነው።

ይህን ተፈፃሚ የማያደርጉትን ከአባልነት እንሰርዛለን። ሀሳብን በጫዋነት በመግለፃ እጅግ ከባድ የሆነውን ፈተና አብረን እንሻገር።

@tikvahpollanddiscussion
ዛሬ የመጀመሪያው ቀን የውይይት መድረካችን ሀሳባችንን በፅሁፍ የምንገልፅበት ነው።

አንድ ሀገር እየኖርን ለምን አብረን ማዘን ፣ አብረን መደሰት አቃተን ?

በእርግጥ ለመወያያ ምክንያት የሆነን የማህበራዊ ሚዲያው ሁኔታ ነው። ማህበራዊ ሚዲያው በትንሹም ቢሆን መሬት ላይ ያለው ሁኔታ ያስረዳናል።

ለምን አብረን ማዘን ? መደሰት አቃተን ? ምን ይሆን ሰዎች እንዲጨካከኑ ያደረጋቸው ? ምን ይሆን የአንዱ ሞት ለአንዱ ምንም የማይሰማው / የሌላኛውም እንደዛው ? ለምን ይሆን የኛ ወገን ብቻ ሲነካ የሚያመን ?

ይህ ሁሉ ነገር አሁን የመጣ ነው ? ወይስ የነበረ ? ቢያንስ እስከ 30ዎች ያሉ ወጣቶች ብዙ ነገር አይተዋል፤ ይህ ትውልድ ብዙ ነገር ታዝቧል። የአንዱ ሞት ለሌላው ግድ የማያሰጠው /የአንዱ ችግር ለሌላው ስሜት የማይሰጠው ከምን በመነጨ ነው ?

መፍትሄው ምንድነው ?

@tikvahDiscussionandPoll
ውድ አባላት ፦

በምን ጉዳይ እንድንነጋገር ፤ አባላትም ሃሳባቸውን /ድምፃቸውን እንዲሰጡ ትፈልጋላችሁ ፤ ከታች በአስተያየት መስጫው ላይ አስፍሩ።

ሀሳቦቹ በቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ትልቅ ግብዓት ይሆናሉ።

@tikvahDiscussionandPoll
እንዴት ቆያችሁ ?

ሰላም እና ጤና ከእናተ አይለይ ውድ ቤተሰቦቻችን።

ዛሬ እጅግ አሳሳቢ እየሆነ ስለመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን እንነጋገራል።

ሀገራችን ላይ ያለው የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እናተ ጠንቅቃችሁ የምታውቁት ነው።

ሰዎች ሀሳብ እንኳን መሰንዘር በማይችሉበት ደረጃ እንዲሸማቀቁ፣ አንገት እንዲደፉ ይደረጋል፤ በእያንዳዱ ፅሁፍ ስር የስድብ፣ ጥላቻ ቃላትን መመልከት ተለምዷል።

ሰዎች ከኛ የተለየ ሃሳብ ስላላቸው ብቻ ይሰደባሉ፣ በማንነታቸው ይተነኮሳሉ።

ስድብ እና ጥላቸው የተወሰኑ መድረኮች ላይ ነው ተብሎ እንዳይተው በእያንዳንዱ ፁሀፍ፣ ዜና፣ ፎቶ፣ ሌላው ቀርቶ ሃይማኖታዊ ፅሁፉሮች ስር ስድብ የሚያሰፍሩ ሰዎች ቁጥራቸው ቀላል የሚባል አይደለም።

ለመሆኑ ሰዎች ሳይሳደቡ /ሳያንቋሽሹ፣ ሳያሽሟጥጡ ሃሳባቸውን መግለፅ አይችሉም ?

ይህ መጥፎ ልምድ ከየት መጣ ? መፍትሄውስ ምንድነው ?

NB. ሆን ተብለው ለስድብ፣ ለጥላቻ፣ ግጭት ለመቀስቀስ፣ ለማባባስ፣ ሰዎችን ለማጋጨት የተከፈቱ እጅግ በርካታ አካውንቶች እንዳሉም ይታወቅ።

@tikvahDiscussionandPoll
እንዴት ሰነበታችሁ ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች ?

ሙሉ ጤንነትን ከረጅም እድሜ ጋር እንመኝላችኃለን።

ዛሬ በቅርቡ ስለሚደረገው ምርጫ እንነጋገራለን።

በሀገሪቱ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች ቢኖሩም፤ አሁንም የዜጎች ሞት ቢቀጥልም ፤ መጭው ምርጫ በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ እየተጠበቀ ነው።

የምርጫ ሂደቱን እንዴት እያያችሁት ነው ?

ከምርጫው ምን ተስፋ ታደርጋላችሁ ?

ስጋታችሁስ ምን ይሆን ?

የምርጫ ካርድ ወስዳችኃል ? ካልወሰዳችሁስ ለምን ?

ከላይ በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ምላሻችሁን ፤ የናተንም ስለ ምርጫው እይታ አጋሩ።

@tikvahDiscussionandPoll