NOUS 💬 ናውስ የሐሳብ መድረክ
3K subscribers
27 photos
ውሳጣችን የሚብሰለሰሉ ማኛውም ሐሳቦችን ለምን ለሌሎች አናጋራም ?
- መሳደብ / የጥላቻ ቃላት
- የሰው ክብር ዝቅ ማድረግ
- ሰዎች መግለጫዬ ነው የሚሉትን ማንነት፣ ሃይማኖት፣ አስተሳሰብ ማንቋሸሽ አይቻልም።

#Nous
#ናውስ
Download Telegram
" አትላኩ !

ወጣቶች በምንም አይነት የፍቅር ሁኔታ ላይ ቢሆኑ በስሜታዊነት ብቻ ያለ ስሌት የሚያደርጉት ነገር ነገ ዋጋ እንዳያስከፍላቸው መጠንቀቅ አለባቸው።

በምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን የእርቃን ፎቷችሁን አትላኩ። አስፈላጊም አይደለም።

የእርቃን ፎቶ ላኪልኝ ለሚሉ ሁሉ መልሳችሁ አይሆንም የሚል መሆን አለበት።

ስንቶች ሳያውቁት መከራ ውስጥ ገብተዋል። ስንቶች ' የእርቃን ፎቶሽን ዘረግፈዋለሁ ' እያሉ በማስፈራራት ልጆቻችንን የሚያሰቃዩ አሉ።

ራሳቸውን ለማጥፋት የሞከሩ ልጆችንም አውቃለሁ።

ወላጆች ኃላፊነት አለብን ፤ ልጆቻችንን ቀርበን ማነጋገር እንዲጠነቀቁ ማሳሰብ ፤ ከቤት እራሳቸውን ችለው እስኪወጡም መከታተል ግድ ይለናል።

እኛ ጥረት እናድርግ ሌላውን ፈጣሪ ይሞላበታል። " - ሊዲያ ባህሩ

ሐሳባችሁን ለማጋራት ፦ @nousethBOT

@nousEthiopia
" እዚህ ቦታ የለንም !!

ምንም እንኳን እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪካችን በጦርነት የታጀበ ፣ በእርስ በእርስ ግጭት ውስጥ ያለፈ አሁንም እያለፈ ያለ ፣ በብዙ አለመግባባት እና ንትርክ ውስጥ ያለ ቢሆንም እጅግ የምናከብረው ባህል፣ ወግ ስርዓት ያለን ህዝቦች ነን።

በወቅታዊ ሁኔታ / ክፉ ነገር ባጋጠመን ወቅት ፣ ተስፋ አልታየን ባለ ጊዜ በአንዳንድ ጉዳዮች ' እኔ ምን አገባኝ ' ብለን የምናልፍም አይደለም።

ይህን ያነሳሁት በምንም ሁኔታ ውስጥ ብንሆን #ግብረሰዶማዊነት በሀገራችን በፍጹም ቦታ ሊኖረው እንደማይገባ ለማስታወስ ነው።

ግብረሰዶማዊነት በየትኛውም ሃይማኖት የሃጥያት ሁሉ አውራ ነው።

እኛ ኢትዮጵያውን የተሰራንበት የተገነባንበት መንገድ ለእንደዚህ አይነቱ ድርጊት ቦታ እንዳንሰጥ ሆነን ነው።

ዛሬ ዛሬ ግን በዘመናዊነት ሰበብ እድሜ ለማህበራዊ ሚዲያ ለመብት ተሟጋች ነን የሚሉ የሀገራችን ሰዎች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። እነዚህ ሰዎች ልጆቻችንን ይዘው እንዳይጠፉ ለአፍታም ቢሆን እድል ልንሰጣቸው አይገባም።

ልጆቻችን በማህበራዊ ሚዲያ የሚያዩትን እንዲመርጡ፣ በሃይማኖታዊ ስርዓት ውስጥ አልፈው እንዲመጡ ማድረግ ፣ ማህበረሰቡ ስለሚጠየፋቸው ነገሮችም ማስተማር ይገባል።

ልጆችን / ወጣቶችን ክፉኛ መጫን ሳይሆን እያስተማሩ ፣ እያሳወቁ የውሳኔ አቅማቸውን ማሳደግ ይገባል።

መጥፎን ድርጊት መጥፎ ነው ማለት ይገባል። ዛሬ ጉዳዩ አሳስቦን ካልተነጋገርን ነገ ዋጋ መክፈላችን ነው። " T.

በማንኛውም ጉዳይ ሐሳብ ለማጋራት @nousethbot ይጠቀሙ።

@nousEthiopia @nousEthbot
" ወጣቱን ስልጣኔ ምን እንደሆነ እንዲረዳ ብናደርገው መልካም ነው።

ባለሁበት አከባቢም፣ በሩቅም ብዙ ወላጅ ተከታትሎ ያሳደጋቸው ወጣቶችን አይቻለሁ፤ ነገር ግን ውጤቱ የሚጠበቀውን ያህል አይደለም።

ልጆች/ወጣቶች ማንኛውንም ነገር ከራሳቸው ፈጥረው አያደርጉም በአብዛኛው ከሚያዩት ፊልም፣ የሙዚቃ ክሊፖች፣ ቲክ ቶክ trends፣ reels ... ወዘተ ያዩት እና የሠሙት ሁሉ እውነት እና በህይወት routine ውስጥ መኖር ወይም ሁሉም የሚያደርገው ነገር ይመስላቸዋል።

እነዚህ ነገሮች አግባብ እንዳልሆኑ፣ ለመዝናኛ የተፈጠሩ ሀሳቦች ብቻ እንደሆኑ ከወላጆች ተጨማሪ ሁሉም አውቆ ሊያሳውቅ ይገባል እላለሁ።

አመሠግናለሁ 🙏 "

(Rocket)

@nousEthiopia
#ኢትዮጵያ

" መቼ ነው እኛ ወጣቶች በሀገራችን ለመለወጥ ተስፋ አድርገን ፣ ጥሩ ስራ አግኝተን፣ እድሜያችን ሳይገፋ ቤተሰብ መስርተን ፣ ወልደን ከብደን ህልማችንን የምንኖረው።

እኔ በእድሜዬ እዚህ ሀገር ዘላቂ የተረጋጋ ሁኔታ አንድም ቀን እይቼ አላውቅም።

ትንሽ እንደመማሬም እንዳነበብኩት ባለፉት የቆዩ ታሪኮቻችን ፍጹም የእድገት እና የተረጋጋ የአንድነት ጊዜ እንደነበረን አላስታውስም። አብዛኛው ግጭት፣ እርስ በእርስ መገዳደል፣ ንጉስ ንጉስን ለመጣል መዋጋት፣ ለማስገበር መዋጋት ነው።

የቅርብ ጊዜውን ብናይ መንግስትን ለመጣል መዋጋት፣ አመጽ መጥራት ነው ታሪካችን።

በዚህ መሃል ክፉኛ የሚጎዳው ወጣቱ ነው። ለውጊያ የሚጠቀሙት ወጣቱን ነው። ከፊትም የሚያሰልፉት ወጣቱን ነው።

ምረጡን እንለውጥላችኃለን የሚሉት ወጣቱን ነው፣ ነገ ህይወታቹን እንቀይራለን ተነሱና ተዋጉ የሚሉት ወጣቱን ነው።

ታዲያ በዚህ አይነት የሀገር ሁኔታ በአዙሪት ውስጥ ባለ ሀገር ውስጥ እንዴት አብዛኛው ወጣት ይለወጣል ? ለዛም ነው ሳይወድ በድግዱ ሀገሩን ጥሎ የሚሰደደው።

መቼ ነው በሀገሬ ተስፋ የሚኖረኝ ? ወጣትነት እኮ የማይመለስ ጊዜ ነው ዛሬ ካልሰራሁ እድሜን በሙሉ በድህነት ውስጥ እየማቀኩ መኖሬ እርግጥ ነው።

ይህ ያሳስበኛል። መፍትሄውም ግራ ነው የሚገባኝ። " T.

@nousEthiopia
#ኢትዮጵያ

" በወጣቶች ጉዳይ የተነሳው ሐሳብ ተመለከትኩት ትክክል ነው።

ሰው ወዶ አይደለም፣ ሰው ሀገር ጠልቶ አይደለም ባገኘው አጋጣሚ ሀገሩን ጥሎ የሚሰደደው።

በህገ ወጥ መንገድ ህይወቱን ለመቀየር ሲል የባህር ሲሳይ የሚሆነው ፥ በረሃ ላይ ህይወቱን የሚያጣው ወዶ አይደለም።

ያማል በቃ ! ወጣትነት አጭር ጊዜ ነው ካልተሰራበት ያልፋል።

እሺ የምሰማው መርዶ፣ ሰቆቃ ነው። እኔ ለምሳሌ ቤተሰቦቼን በአማራው ክልል ጦርነት አጥቻለሁ። ምን አይቼ ተስፋ ላድርግ ?

መልስ ብዬ ባለፉትን አመታት ሳይ ታሪካችን ጦርነት ነው። አካባቢያችን የነበረው ጦርነት ነው።

ከዛ በፊት ሳይ አድማ አመጽ፣ ውጥረት፣ ጭቅጭቅ ነው ? መቼ ተረጋግተን እንደምንኖር አላውቅ።

ከዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ውጤት ከወጣው 5 ዓመት ሆነኝ ምንም የረባ ስራ የለኝም። ይኸው ስንከራተት እኖራለሁ።

በቃ ህይወት ይቀጥላል ብዬ ስንት አመት ከጠበቀችኝ ጓደኛዬ ጋር ወደ ትዳር ልገባ ነው። ከዛ ደግሞ ልጆች ይመጣሉ ስለነሱ መኖር ስጀምር እድሜያችን ይገፋል።

ድሮ ሰላሳዎቹ ሳልገባ መኪና፣ ቤት ፣ የተሻለ ህይወት ኖሮኝ ልጆች ወልጄ እኖራለሁ እል ነበር ግን ህይወትን ማሸነፍ እንኳ ከበደኝ።

ይህ ነው የብዙዎቻችን ታሪክ። " - ይቤ

@nousethiopia
" በሀገራችን የወጣቱን ተስፋ ከሚያቀጭጩ ሀገሪቷም እንዳታድግ ከሚያደርጉት ጉዳዮች አንዱ #ሙስና ነው።

ሀገራችን በሚገርም ሁኔታ ፦
- ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ በጀት ላይ የሚሰረቅባት
- ከወጣቶች የስራ እድል ተብሎ ከሚመደበው የሚሰረቅባት
- ከሆስፒታል ከመንገድ ስራ የሚሰረቅባት

... ምን ይቀራል ከሁሉም የሚሰረቅባት ናት።

አንድ ባለስልጣን የሚዘርፈው ብር ለስንት ወጣት የስራ እድል ይፈጥራል ? የስንት ሰው ህይወት ይቀይራል ?

ሌላው ይቀር እንዴት ራስን ብቻ ወዶ ከዩኒቨርሲቲዎች ይሰረቃል።

በሙስና የተገኛ ሀብት መቼም ሰላም አይሰጥም። በእህቱ፣ በወንድሙ ፣ በዘመዱ ስም ያስቀምጥ ፣ ገንዘቡን ንብረት ያፍራበት መቼም ዋስትና አይሆንም አንድ ቀን ዋጋ ይከፍልበታል።

የቸገረው ማህበረሰብም የሌባው ቤት በራፍ ላይ ሆ ብሎ መቆሙ አይቀርም።

' ለስራው ተገቢውን ብር ስለማይከፈል ነው ሙስና የሚሰሩት ' የምትባል ሙስናን ኖርማል የማድረግ ሁኔታ አለች መጀመሪያ ህሊና ይቀድማል። ከስርቆት ነጻ መሆን ይቀድማል። ስራው ካልተስማማው መልቀቅ እና ሌላ የተሻለ ገቢ መፈለግ ነው አለቀ ! ስንት ስራ አጥቶ ሀገርን ማገልገል ፈልጎ ቁጭ ያለ አለ።

ዛሬ በትንሹ መብላት የጀመረ ከፍ ሲደረግ ከፍ ያለ ብር መዝረፉ አይቀርም።

ሙስና ሀገር ያደኸያል። ወጣቶችን ተስፋ ያስቆርጣል ወይም ወደ ተሳሳታ መንገድ እንዲገቡ ያደርጋል። " -T

@nousEthiopia
🤔 የአዲስ አበባ ምሽት መዝናኛ ቤቶች

" ዛሬ አንድ ጉዳይ ላንሳ።

ምን መሰላችሁ ሰዎች ምን እና እንዴት እንደሚዝናኑ የሚያውቁት እራሳቸው ናቸው። ምርጫቸውን አልነካም።

ግን ደግሞ ባህልና ወግ አለን። ትውልድ አለን። መጠንቀቅ ይገባል።

በፊት ክለብ ውስጥ መታየት ያስፈራን የነበርን ሰዎች ዛሬ በቀጥታ በቪድዮ እየጠጣን ፣ እያጨስን መታየት የዘመናዊነት ጥግ አድርገነዋል።

ክለብ ውስጥ እየጠጡ ቪድዮ ቀርጾ ማሰራጨት አዲስ ፋሽን ሆኗል።

እንደምታውቁት የማህበራዊ ሚዲያ ከመልካም ነገር ይልቅ ለትውልድ የማይጠቅመው ነገር በፍጥነት ይዳረሳልናል ምናለ መዝናናታችን በስርዓት እና ትውልድን በማይገፋፋ መልኩ ቢሆን።

ሌላው በጣም ደግሞ ግርም እያለኝ ያለው ፍጹም ስርዓት አልባ የሆነ ተግባር በቪድዮ እየቀረጹ ማሰራጨት አላማው ምንንድነው ?

ይህን እንድል ምክንያት የሆነኝ በእድሜ ከፍ ያሉ የሚመስሉ ሴት ዘፋኞች በየመድረኩ የሚያደርጉት ድርጊት ነው።

ልጅ ቤተሰብ፣ ትዳር፣ ጓደኛ ፣ ዘመድ ይኖራቸው ይሆናል ፤ ሌላው ሁሉ ይቅር ለሴት ልጆቻቸው ምን ያስተምራሉ ? ዘፈን ዘፍነው የሚከፈላቸው ከሆነና ሌላ አላማ ከሌላቸው በስርዓቱ ለምን ስራቸውን አይሰሩም ?

ድሮ የመድረክ ዘፋኞች እንዲህ ለትውልድ መሰናክል ነበሩ ? ተመልካቻቸውን የሚያከብሩ እንጂ።

ትውልዱስ ምን ይማር ? በእንዲህ ያለው መንገድ የሚገኝ ገንዘብስ በእውነት ምን ይጠቅማል ? በቻ ስንሰራም ሆነ ስንዝናና ለትውልድ እያሰብን ቢሆን ጥሩ ነው። " T.

@nousethiopia
በሪሃና

" በከተማችን አዲስ አበባ የቤት ኪራይ ከጫፍ እስከ ጫፍ ዋጋው እየናረና አስጨናቂ በመሆኑም መፍትሔ á‹¨áˆšá‹ŤáˆľáˆáˆáŒˆá‹ ጉዳይ እንደሆነ የሚታወቅ ነው።

በቅርቡም መንግስት የአከራይ ተከራይ ኪራይ አዋጅ ያወጣ ቢሆንም አከራዮች በጣም በአብዛኛው በሚባል መልኩ ዋጋ ጨምረው በማከራየት ምንም አላገዳቸውም።

ምናልባት ከዚህ የተሻለ መፍትሔ ያስፈልጋል።

ቢያንስ ለምሳሌ መንግስት እንደ ኪራይ ቤቶች ተቋም ኖሮ ቤት እየሰራ በተመጣጣኝ ዋጋ ቢያከራይ ለህብረተሰቡም ጥሩ እፎይታ ለመንግስትም ገቢ የሚሆን ይመስለኛል።

በዚ ጉዳይ ላይ ሌሎች ሰዎችም እንደ መፍትሔ የሚያነሱት ነገር ካለ ቢያጋሩን። "

@nousethiopia
ፍትሕ ባልሰፈነበት ሁኔታ ሰላም መፍጠር ይቻላል ?

ሰዎች በተጎዱ ቁጥር ቂም መቋጠራቸው አይቀርም።

ሰው ቤተሰቡን ፣ ወዳጁን ፣ ጓደኛውን ፣ወገኑን በግፍ በተነጠቀ ቁጥር በውስጥ ፍቅር ሳይሆን ቂም ጥላቻ ነው የሚያድርበት ይህ ደግሞ ሰዋዊ ባህሪ ነው።

ይህ እንዳይሆን ደግሞ ፍትህን በማስፈን ተበዳይን መካስ ይገባል።

ሰው ለምን ጥላቻ አደረበት ? ማለት እና ሰዎቹን ለመረዳት ከመጣር ይልቅ መልሰን እናቆስላቸዋለን።

ማንም ከመሬት ተነስቶ ጥላቻ በውስጡ አያድርም። ያየውን የሰማውን የደረሰበትን ነው መልሶ የሚያንጸባርቀው።

ስለዚህ ሰዎችን እንዳይጎዱ ማድረግ ችግር ከተፈጠረ እንኳን ፍትህ በማስፈን መካስ ካልተቻለን መግባባት እና ሰላም ይኖራል ብሎ ማሰብ አይቻልም።

@nousethiopia
" ትምህርት !

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በየማህበራዊ ሚዲያው እየቀረቡ የፈለጉትን መናገር ፤ ሰውም ደግሞ ወዲያና ወዲህ ሳይል " ጀግና ! " እያሉ ማድነቅ አዲስ ፋሽን እየሆነ ነው።

አንዳንዶቹ ገና በወጣትናት እድሜያቸው የህይወት ተሞክሮ አካፋይ ሆነው ብቅ ይሉና " ትምህርት ምን ይሰራል ? ተምሬ የት ደርሳለሁ ? ዩኒቨርሲቲ አቋርጬ ወጣሁ ፣ በትምህርት አላምንም ፣ ዩኒቨርሲቲ እድሜ መፍጀት ነው ፣ ንግድ ነው የሚሻለኝ ብዬ ገባሁበት " እያሉ ሲናገሩ ይደመጣል።

ዛሬ ይህችን ቴክኖሎጂ እንኳን እንዲጠቀሙ የረዳቸው ትምህርት መማራቸው እንጂ ከየት ያመጡት ነበር።

እውነት ነው የሀገራችን የትምህርት ነገር አስከፊ ነው ሰው ተምሮ ደህና ኑሮ ላይኖር ይችላል ፣ ሰው ተምሮ የፈለገበት ላይደርስ ይችላል ግን ቢያንስ ህይወቱ ላይ አንዳንች ነገር መማሩ ይጨምርለታል።

ያለው ችግር እንዲስተካከል መታገል ይገባል። ስለዚህ ለመረዳት እንኳን መማር ያስፈልጋል።

አንዳንዱ ጎበዝ ደግሞ በትምህርቱ የተሻለ ደረጃ ይደርሳል። ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ ይሰራል፣ ድርጅት ይመሰርታል ፣ ሚሊየነር ይሆናል !! አያቆምም እኮ መማሩን ይቀጥላል።

ስለዚህ ትንንሽ ልጆች ትምህርት እንዳይማሩ፣ ተስፋ እንዲቆርጡ አታድርጓቸው።

መማር ያስከብራል። ንግድ ፣ መዝናኛ ውስጥ ቢገባ እንኳን የተማረ ሰው ብዙ ዕድል ይኖረዋል። ይከበራል። ይፈለጋል።

በተለይ ዘመን አመጣሽ ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ገንዘብ እና እውቅና ያገኙ ወጣቶች ናቸው ልጆች እንዳይማሩ የሚገፋፋ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚታዩት። ታረሙ !

ዩኒቨርሲቲ አቋርጦ መውጣት ጀግንነት አይደለም። ትምህርት አለመጨረስ ጀግንነት አይደለም።

ትምህርታችንን እንማር ! ከጎን እንስራ ! እውቀት እንጨብጥ። ዛሬ የትም ቦታ ብትሄዱ የትምህርት ማስራጃ ያስፈልጋል፣ የት ጨረሳችሁ መባሉም አልቀረም።

የተሻለ እድል ካገኘን እየሰራን እንማር። መማራችን ይጠቅመናል እንጂ አይጎዳንም። ሌላው ይቅር ከሰዎች ጋር እንዴት መኖር እንዳለብን ያስገነዝበናል።

ተምሮ፣ አውቆ ምንም ይሁን ትምህርቱም ጨርሶ ገንዘብም ይዞ የተገኘ ጀግና ነው።

ስለዚህ ልጆች እንዳይማሩ አትገፏፏቸው። ይልቅ የምትጠቀሙበት ቲክቶክ፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ፣ ቴሌግራም ፣ የምታነቡት እንግሊዘኛ፣ የምታነቡት መረጃ ተምራችሁ እንደሆነ አስረዷቸው።

በመማር ሳይንቲስት ፣ ዶክተር ፣ ተመራማሪ መሆን እንደሚቻል ፤ ነጋዴም ቢኮን የተማረ ሲሆን ትርፋማ ተፈላጊ እንደሚሆን አስረዷቸው።

እባካችሁ ዛሬ እድል ቀንቷችሁ ብትታወቁና ገንዘብ ብታገኙ ለነገ ዋስትና የላችሁምና ትንንሽ ልጆችን ተማሪዎችን ተስፋ አታስቆርጡ !

@nousethiopia
የኢኮኖሚ ሪፎርም

ለኢኮኖሚ ባለሙያዎች የቀረበ የውይይት መድረክ ፦

መንግሥት " በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርዓት " አስተዋውቋል።

ውሳኔው ብር፤ ዶላር እና ፓውንድን ከመሳሰሉ ዋና ዋና የመገበያያ ገንዘቦች አኳያ ያለው የምንዛሬ ተመን ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል።

አንዳንዶችም በIMF እና WB ምክር ወደዚህ መገባቱ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያይል ይችላል ይላሉ።

መንግሥትን ጨምሮ ሌሎች ማሻሻያው ምንም እንኳን አንዳንድ አሉታዊ ተፅእኖ ቢኖሩ ትልቅ ለውጥ እንደሚያመጣ እየገለጹ ናቸው።

ለዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ የመንግስት ሰራተኞች የማክሮ ኤኮኖሚ ማሻሻያዎቹ ሊያስከትሉ ከሚችሉት የአጭር ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የደመወዝ ድጎማ እና ማሻሻያዎች ለተወሰኑ ጊዜያት ይደረጋሉ ተብሏል።

በነዳጅ ዋጋ ላይ የሚከተለውን ጭማሪም መንግስት በከፊል #እንደሚደጉም አሳውቋል።

በአጠቃላይ ባለሞያዎች ማሻሻያው እንደ ሀገር እንዲሁም ለሰራተኛው ፣ ለዝቅተኛ የማህበረሰብ ክፍል
፦
- ምን ጥቅም አለው ?
- ምን ጉዳት አለው ?
- በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ምን እንጠብቅ ?

የሚለውን በድምጽም ይሁን በጽሁፍ በዚህ አጋሩን።

@nousethiopia
#Ethiopia

(የባንክ ጉዳዮች ባለሞያው ሙሼ ሰሙ)

" የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም የፖሊሲ መግለጫውን ተመልክቺያለሁ። መግለጫው በአጭሩ ሲቃኝና ሲጨመቅ ይህንን ይመስላል። እጠቅሳለሁ።

' የውጭ ምንዛሬ ግብይት በገበያ አማካኝነት እንዲበየን የማድረግ ሂደት ነው። '

ይህንን ውሳኔ ተከትሉ የሚከሰቱ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ( Derivates & Consequence ) እንደሚኖሩ ግልጽ ነው።

ተግዳሮቶቹን ለመከላከል የታቀዱ በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ የሚወሰዱ እርምጃዎች በመግለጫው ላይ ተዘርዝረዋል።

የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫዎች ዝርዝርና ግልጽነት የሚጎድላቸው እንዲሁም በርካታ አማላይ ምኞቶች የታጨቁበት ከመሆናቸው አኳያ ዝርዝር የአፈጻጸም ትንታኔ የሚፈልጉ ናቸው።

በመርህ ደረጃ ፓሊሲው የሚያተኩርበትን ዓላማ ለግንዛቤ ከመግለጫው እጠቅሳለሁ።

' የፊስካል ፖሊሲ ማሻሻያው ዋና ትኩረቱ የመንግስት ገቢን ማሳደግ፤ የመንግሥት ወጪንና የድጎማ ሥርዓትን ውጤታማ ማድረግ ነው ' ይላል።

ዓላማው ከአጭር ጊዜ መፍትሔዎች ጋር የሚጣረስ ነው።

በአንድ በኩል በከፍተኛ ደረጃ ድጎማ እንደሚኖር የሚጠቅስ ሲሆን በሌላ በኩል በከፍተኛ ደረጃ የመንግስት ገቢን ማሳደግን ያመላክታል። ድጎማና ገቢ ግንኙነታቸው ተቃርኗዊ ነው። የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የፓሊሲ ዝርዝሩን በሚመለከት ወደፊት የምናየው ስለሆነ አመላካች አንቀጹን ከሰነዱ ጠቅሼ ልለፈው።

የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን በተመለከተ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች በገንዘብ ሚኒስቴርና በብሔራዊ ባንክ በኩል በየጊዜው የሚገለጹ ይሆናል።

ወደ አጭር ጊዜ መፍትሔዎቹ እንምጣ።

ፓሊሲው በአብዛኛው እንደ መፍትሔ ያቀረበው ድጎማና አስተዳደራዊ እርምጃዎችን ነው።

አስተዳደራዊ አቅምና ብቃቱን ከየት እንደሚገኝና መጠነ ሰፊ ድጎማው ምንጩን ከምን እንደሚሆኑ ዝርዝሩን ወደፊት የምናየው ይሆናል።

የአጭር ጊዜ ኢኮኖሚያዊ የመፍትሔ ዝርዝሮች ከመግለጫው እጠቅሳለሁ።

1) የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን መንግስት በከፊል የሚደጉም ይሆናል (ድጎማ)

2) የመልካም አስተዳደር ብልሹነት እና ሕገ ወጥነት መከላከል (አስተዳደራዊ)

3) የማኅበራዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራሞችን መደጎም ( ድጎማ)

4) ዝቅተኛ ባለ ደሞዝ የመንግሥት ሠራተኞችን መደጎም (ድጎማ)

4) ለማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሙ ድጋፍን ያሰባስባል (ድጎማ)

5) እንደ ብሔራዊ ባንክ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ላሉ ተቋማት ድጋፍ ያደርጋል ( ድጎማ)

6) ማሻሻያው የዜጎቻችን ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ ከፍተኛ የክትትልና ድጋፍ ይደረጋል ( ድጎማና አስተዳደራዊ) .. ወዘተ

በዚህ መሰረት ፦

➡ ድጎማው የመንግስት ዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋዮችና የሴፍቲ ኔት ተጠቃሚዎች ላይ ያነጣጠረ ነው። ፓሊሲው ከኢኮኖሚያዊ ቀውሱ ለመታደግ ያቀደው ከ10% የማይበልጠውን ማህበረሰብን ነው ።

➡ መጠነ ሰፊ ድጎማው ከበጀት ውጭ የተለየ ገቢን የሚጠይቅ ነው። ድጎማውን እንዴት ለመሸፈን ታቅዷል። በብድር፣ በእርዳታ ከባለ ሐብቶች በማሰባሰብ፣ ገንዘብ በማተም ? ትልልቅ ፕሮጀክቶችን በማጠፍ ?!

➡ ድጎማ በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ዘንድ ተቀባይነት የሌለውና የተወገዘ ተግባር ነው። የሚጠበቀውን ብድር በውጭ ምንዛሪ ማግኘትና ድጎማን ካልታወቀ ምንጭ መደጎም እንዴት ይጣጣማል?! በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ዘንድ ተቀባይነቱስ ምን ያህል ነው ?!

➡ የሰላም እጦት፣ ግጭትና የምርታማነት መዳከም፣ አምራች ኋይል( ወጣቱ) በግጭት መጠመዱ በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አለው። ተጽእኖው ከፓሊሲው ጋር የሚኖረው ተቃርኖ አልተወሳም?! ለምን

➡ ሙስና፣ የፍትሕና የመልካም አሰተዳደር እጦትን በአስተዳደራዊ መንገድ ብቻ እስከ አሁን መፍታት አልተቻለም። ወደፊትም በአጭር ጊዜ መፍታት ከባድ ነው። አስተዳደራዊ መፍትሔ እንደ አጭር ጊዜ መፍትሔ ሆኖ መቅረቡ ከምን አመክንዮ የተነሳ ነው?!

➡ የውጭ ምንዛሪ አቅርቦትና የዋጋ ንረት አንዱና ዋነኛ ተግዳሮት የአቅርቦትና የፍላጎት አለመጣጣም ነው። ይህንን ችግር ለመፍታት አቅርቦቱን ስለማሳደግ የቀረበው አማራጭ የብድር፣ የእርዳታና የደጋፍ አማራጭ ብቻ ነው። ምን ያህል ዘላቄታ አለው ?!

➡ ድጎማ ለአቅመ ደካሞች መፍትሔ ሊሆን ይችላል። ከዚህ ይልቅ ለተገቢው ስራ ተገቢውን ክፍያ መክፈል ወይም ደሞዝን ማሳደግ አማራጭ ሆኖ አለመቅረቡ ውጤታማነቱ ጥያቄ ላይ የሚጥል ነው።

➡ መካከለኛ ገቢ ወይም ቋሚ ገቢ ( ደሞዝ) ያለው ዜጋ (Disposable income) ካላደገ ገበያውና ኢኮኖሚው መቀጨጭና አለመነቃቃቱ የሚጠበቅ ነው። ቋሚ ተከፋዮን ማህበረሰብ (የተደራጀው ብቻ ከ4 ሚሊየን በላይ ነው) ገቢውን ማሳደግ ቢቻል ፍላጎት በመጨመር ምርትንና አቅርቦትን ማሳደግ ይቻላል። ይህ ትኩረት ለምን አላገኝም?!

(በሙሼ ሰሙ)

@nousethiopia
ገበያ እንዴት ነው ?

ዛሬ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተለይ የውጭ ምንዛሬ በየገበያው እንዲመራ መወሰኑን ተከትሎ ገበያው ላይ ለውጦች ታይተዋል።

ዘይት እና ከውጭ ታሽገው የሚመጡ ቁሳቁሶች ላይ ጭማሪ ታይቷል። በተለይ መርካቶ።

አንዳንድ ነጋዴዎች እቃ ሲጠየቁ የለም ማለትም ጀምረዋል።

የዶላር ዋጋ ጨምሯል በማለት ከዚህ ቀደም ዶላር ሳይጨምር ያስገቡትን በመደበቅ እንዲሁም ዋጋውን ከፍ አድርጎ ለመሸጥ ሲስገበገቡ ተስተውሏል።

በዚህ ሁሉ ማህበረሰቡ ፈተና ማየቱ እንደማይቀር እሙን ነው።

ነጋዴው አብሮ ከማህበረሰቡ ጋር የማይኖር ይመስል ከዚህ ቀደም ያስገባውን ምርት ጨምሮ ለመሸጥ መሞከር ትዝብት ላይ የሚጥል ነው።

እናተስ ዛሬ ምን ታዘባችሁ ?
ማሻሻያው ምን ይዞ ይመጣል ብላችሁ ትጠብቃላችሁ ?

@nousethiopia
ያስተዛዝባል !

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በተለይ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ (ዶላር እና ሌሎች ምንዛሬዎች መውጣት መውረድ) ገበያውን እንደሚያናጋው የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።

በተለይ ሁኔታው በዝቅተኛ ማህበረሰብ ክፍል / ዝቅተኛ የወር ገቢ ያለው ዜጋ ላይ የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ እንደሚሆን ለማንም ግልጽ ነው (ምንም እንኳን መንግሥት የሚመጣውን ጫና ለመቋቋም እርምጃዎች እወስዳለሁ ቢልም)።

ነገር ግን የነጋዴዎች ተግባር ብዙዎችን ያበሳጨ ፣ ያስቆጣ ሆኗል።

ገና ማሻሻያው ከመደረጉ ከወራት በፊት ያስገቡትን ምርት፣ ቁሳቁስ ላይ ጭማሪ ለማድረግ ሲጥሩ ተስተውሏል።

እነዚህ ነጋዴዎች ከማህበረሰቡ ጋር አብረው የማይኖሩ ይመስል ያለ አንዳች ምክንያት በዚህ ልክ ራሳቸውን ወደው ወገናቸውን ለመጉዳት የሚሄዱበት ርቀት አሳፋሪም ጭምር ነው።

አንዳንዶቹ ምርታቸውን ደብቀው " የለም " ማለትም ጀምረዋል።

ለመሆኑ ማሻሻያ ሳይደረግ ከወራት በፊት ያስገቡት ምርት / ቁሳቁስ ላይ " ዶላር ጨምሯል " በማለት በምን አግባብ ነው የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉት ? ለምንስ ነው ከገዛ ወገናቸው ምርት የሚደብቁት ? እነሱስ የሚኖሩት ከህብረተሰቡ ጋር አይደለም ? አብረው ደስታንና ሀዘንን ችግርን የሚጋሩት ከዚሁ ህዝብ ጋር አይደለም ? ፤ ነገ አንድ ነገር ቢሆኑ የሚደርስላቸው ይኸው ዛሬ ዋጋ እየጨመሩ የሚያሰቃዩት ህዝብ አይደል ?

ህዝቡ ነገ ምን ይጠብቀኛል ፤ ኑሮው እንዴት ልገፋው ነው ብሎ በተጨነቀበት በዚህ ወቅት መሰረታዊ አቅርቦትን መደበቅ እና ዋጋ መጨመር ምን አይነት የጭካኔ ተግባር ነው ? ምን አይነት ስግብግብነትስ ነው ?

ይህ የነጋዴዎች ተግባር ጭንቀት ላይ ጭንቀት የሚጨምር እጅግ የሚያስተዛዝብ ነው። እንዲህ ያለ ወቅት መረዳዳት እና መተዛዘን ሲገባ ትርፍ ለመሰብሰብ መሮጥ አሳፋሪ ነው።

ከምንም በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው ነዋሪ ጫናው እንደሚበረታበት እየታወቀ ፣ እንደሚያሰቃየው እየታወቀ መቶ አመት ለማይኖር ህይወት በወገን ላይ እንዲህ መጨከን ተገቢ አይደለም።

(በናውስ የሐሳብ መድረክ)

@nousethiopia
" አንዳንድ ምግቦች በምን አግባብ ዋጋ እንደጨመሩ ግራ ያጋባል።

በኢኮኖሚው ማሻሻያ ላይ ካለንበት ሁኔታ አንጻር ሊጠቅመን ይችላል / አማራጭ የለንም የሚሉ እንዳሉ ሁሉ መንግሥት የማይሆን ውሳኔ ወስኖ ወደለየለት ምስቅልቅል እያስገባን ነው የሚሉ ድምጾችም እየተሰሙ ነው።

ውሳኔውን መቃወም እና መንግሥትን መውቀስ እንደተጠበቀ ሆኖ አንዳንድ ነጋዴዎች ግን የለየለት ስግብግብነት እየታየባቸው ዝም ብሎ መታለፍ የሌለበት ነው።

የሆነ አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ከልክ ያለፈ ትርፍ ለማግኘት የሚሄዱበት መንገድ እጅግ አስደንጋጭ ነው።

በኮሮና ወቅት ህዝቡ ለህይወቱ በሚጨነቅበት ሰዓት አንድ ማስክ ከ200 ብር ድረስ ሳኒታይዘር እስከ 300 ብር ሲሸጥ እንደነበር የቅርብ ትውስታችን ነው።

አሁን ደግሞ ዶላር ጨመረ በሚል ቀድሞ የገባ ምርት ሳይቀር መደበቅ እና ዋጋ መጨመር ተያይዘዋል።

ገና ለገና ነገ ገበያው ይናጋል በሚል ከህዝቡ ምርት መሸሸግ ላይ ተጠምደዋል። ሲጠየቁ " የለም " ሆኗል መልሳቸው።

ከዚህ ባለፈ እዚሁ ሀገር ውስጥ ያለ ምርት ሳይቀር በዶላር ሰበብ መጨመር ይዘዋል። ቆይ ዶላር ጭራሽ የማይፈልጉ ምርቶችን መጨመር ምን የሚሉት ስግብግብነት ነው ?

ህዝቡ እየተሰቃየ ነው። መንግሥት ደግሞ ገና እኮ ጫናው ይቀጥላል ለወራት ወይ ለአመት በማለት እየተናገረ ነው።

በተለይ ዝቅተኛ እና ቋሚ ገቢ ያለው ማህበረሰብ የሚወርድበትን ሁሉ መሸከም አይችልም። " - ናውስ የሐሳብ መድረክ

@nousethiopia
#Ethiopia

አትሌቲክሳችን ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልገዋል። ይህ መሆን ያለበት ደግሞ በትክክለኛ በባለሙያ ነው።

የኦሎምፒክ ውጤቱ አንገት የሚያስደፋ ነው። የተዘመገቡት አንዳንድ ውጤቶችም በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ዘርፍ ያልተለመዱና ለመስማት የሚከብዱ ናቸው።

በጭቅጭቅ፣ በንትርክ፣ በየሚዲያ ላይ በሚደረግ ምልልስ የተጀመረው የፓሪስ ውድድር ኢትዮጵያን የማይመጥን እጅግ ዝቅ ያለ ውጤት ተመዝግቦበት አልቋል።

ጥፋት ከደረሰ እና ውጤት ከጠፋ በኃላ የሚቀርብ ይቅርታ ተቀባይነት የለውም።

የሚያስፈልገው ሁሉም የአትሌቲክሱ ቤተሰብ ቁጭ ብሎ በእርጋታ መክሮ ፤ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ብቻ ነው።

ሁሉም ዜጋ በየፊናው የተሰማውን ብስጭት፣ ንዴት እየገለጸ ነው። ይህ የሚጠበቅ ነው። ምክንያት ? ሀገሩ ነው፣ ክብሩ ነው። የሚጠብቀውን ሳያገኝ ሲቀር ህዝቡ ያዝናል ፣ይበሳጫል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ እውነተኛ ለውጥ ይፈልጋል።

እውነትም " ለሀገራችን ክብርና ፍቅር አለን " የሚሉ የአትሌቲክሱ አካላት በእርጋታ ፣ በንግግር ችግሮች እንዲፈቱ ያድርጉ።

ይህም በመሪዎች እና አመራሮች ደረጃ " ለጠፋው ውጤት ፣ ዝቅ ላለው የህዝባችን ክብር ኃላፊነት እንወስዳለን ፤ ይህ የመጣው ስላልሰራን ነው " ብሎ ቦታ መልቀቅን ፤ ለሌላው እድል መስጠትን ያካትታል።

በአትሌቶች ዘንድም የውጤታችን መጥፋት እንዴት እንደተከሰተ ፤ ምናልባት የተሻሉ አትሌቶችም ካሉ ለነሱ ቦታ እያስረከቡ መሄድም እንዲቻል በጥልቀት መገምገም ይገባል።

በአትሌቶች እና አሰልጣኞች መካከልም ተግባብቶ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ በቡድን አለመስራት ችግርም ካለ መፈተሽ አለበት።

በአጠቃላይ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ህዝቡ የሚፈልገው ክብሩ እንዲመለስለት ብቻ ነው ፤ ሙያውን የሚያውቅ በቦታው ተገኝቶ ለውጥ አምጥቶ በሀገሩ ውጤት ተደስቶ ማየት ነው።

የሚዲያ ምልልስ ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ በዚህ መሃል ደግሞ የሚፈጠር የውጤት ውድቀት ህዝብን ፍጹም አይመጥንም።

ጉዳዩ ሙያዊነውና ለባለሙያዎቹ እንተወው ፤ እውነት ግን " የሀገራችን ክብር ይመለከተናል " የሚሉ የሀገር ጉዳይ ብቻ አላማቸው ከሆነ ሌላ ፍላጎት ከሌላቸው ጭቅጭቅ እና ንትርክ ትተው ቁጭ ብለው መነጋገር አለባቸው። ኃላፊነት መውሰድም አለባቸው።

በአሁኑ ውጤት ያልተበሳጨ፣ ያላዘነ ፣ አንጀቱ ያላረረ ዜጋ የለም በዚህም ደግሞ በስሜታዊነት አስተያየቱን እየሰጠ ነው። ለውጥ እንዲመጣ ወደ ክብራችን እንድንመለስ ጥያቄ እያቀረበ ነው።

ነገር ግን አንዳንድ አስተያየቶችም ጥንቃቄ ይፈልጋሉ የአትሌቶችን ስነልቦና እንዳይጎዳ።

ባለፈው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና " ያለእናተ ሰው የለም ፤ ጀግኖች " እያልን ያወደስናቸውን ልጆች ዛሬ ውጤት በመጥፋቱ በብስጭት እና ሀዘን ስሜት ያልተገባ ቃል እንዳንናገር መጠንቀቅ ይገባል።

ዳግም ህዝቡ በሚኮራበት አትሌቲክስ እንዳያዝን ተነጋግሮ ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ህዝቡ ክብሩ እንዲመለስለት ይፈልጋል። አራት ነጥብ !

ስር ነቀል ለውጥ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ !

#የሐሳብ_መድረክ

@nousethiopia
#Ethiopia

" ኢትዮጵያ ፓሪስ ላይ በአትሌቲክሱ ያስመዘገበችው ዝቅተኛ ውጤት በቀናት ውስጥ ተረስቶ አጀንዳው ተቀይሯል።

ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት ኃላፊነቱን የሚወስደው ማነው ? ቀጣዩ እርምጃስ ምንድነው ? ወይስ ጉዳዩ ተረሳስቶ ይቀራል ነው ?

ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ስሟ ከፍ ብሎ የሚጠራባት አትሌቲክስ ታሟል። ስለሆነም ስር ነቀል ለውጥ መምጣት አለበት።

ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የአትሌቲክስ ሰዎች ሁሉ ቁጭ ብለው መክረው ለውጥ ያምጡ። 

ለነገ ዛሬ ካልተሰራ ተመሳሳይ ነገር ይጠብቀናል። "

@nousethiopia