ሰላም ጤና ወዳጆች፡ በሃምበርግ ዩኒ በየሳምንቱ ረቡዕ ምሽት Music in Africa የተባለ ለሁሉም ክፍት የሆነ የምርምር ማቅረቢያ ፕሮግራም ጀምረናል። ለ14 ሳምንታት ይቆያል። በZOOM መሳተፍ ለምትፈልጉ ፕሮግራሙ ይኸው።
ረቡዕ ከምሽቱ 1 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ ማለት ነው።
እዛ እንገናኝ።
ረቡዕ ከምሽቱ 1 ሰዓት በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጀምሮ ማለት ነው።
እዛ እንገናኝ።
አጼ ምኒልክ እንደታመሙ ስለሕመማቸው ብዙ አይነት ወሬ ይነገር ነበረ። መርስዔ ኀዘን ግን ለራሳቸው የመሰላቸውን እንዲህ ሲሉ ይተርካሉ፡
« «በነሐሴ ወር በጾመ ፍልሰታ ውስጥ አንድ ቀን ጧት ጃንሆይ ለጸሎት ወደ ሥዕል ቤት ኪዳነ ምሕረት ሄደው ጸሎት ከአደረሱ በኋላ ወደ ቤተ መንግሥታቸው ተመለሱ። እንቍላል ግንብ አጠገብ ያለው የወለሉ ሜዳ የድንጋይ ደረጃ ተነጥፎበታል። ጃንሆይ መንገድ ሲሄዱ ፈጠን ፈጠን እያሉ ነውና ከእልፍኛቸው አጠገብ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው የዝናም ውሐ የሸፈነው የድንጋይ ደረጃ አዳለጣቸውና በድንገት ሸብረክ አሉ። የተከተሏቸውም ሰዎች በቶሎ አንሥተው ከእልፍኝ አስገቧቸው። ከዚህ ቀን ጀምሮ ታመው እልፍኝ ዋሉ» ሲባል ሰምቻለሁ። ስለ ሕመማቸው ለመጀመሪያ ጊዘ ለሕዝብ የተነገረው ግን እግራቸውን ታመዋል እየተባለ ነበር።»
ይህ የሆነው በ1900 ዓ.ም. መሆኑ ነወ።
ከዚሁ ገጽ በላይ ደግሞ የፈንጣጣ ክትባት እንዴት ይሰጥ እንደነበረም ይገልጻሉ። እሱን ፎቶ ላይ ታገኙታላችሁ።
ምንጭ፡ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ትዝታዬ - ስለራሴ የማስታውሰው 1891-1923
ገጽ፡ 66

መርስዔ ኀዘን በግለታሪካቸው ከሚያስታውሷቸው ነገሮች መካከል የልጅ ኢያሱን የክርስትና ስም ነው። እስቲ ገምቱ የቱ እንደሆነ?
Anonymous Quiz
23%
ኃይለ፡ ሥላሴ
16%
ክፍለ፡ ያዕቆብ
29%
ፍቅረ፡ ማርያም
32%
ሣይለ፡ ጊዮርጊስ
ጦብያን በታሪክ
ሰላም ኤቭሪባዲ፡ ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ጋር ብዙ አፍታ ቆይታ በPDF ያለው አለ? ከብዙ ምስጋና ጋር።
አመሰግናለሁ። ደርሶኛል። የምትፈልጉት ጻፉልኝ እና እልክላችኋለሁ
1907 ዓ.ም. እና ቡና
~ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ከዘገቡልን ~
«እንዲሁ ደግሞ ዕጣን እየተጨሰ ቡና የመጠጣት ልማድ በባላገር የተጀመረው በዚያው ጊዜ ነው። ከዚያ በፊት ግን ይህ ዓይነት ልማድ የሚታየው በነጋዴዎችና በእስላሞች በተለይም በቃልቾች ዘንድ ነበር። በበረሃ ስፍራ የሚኖሩ ነፍጠኞችም የዚሁ የቡና ልማድ ነበረባቸው።
ስለዚህም እነዚያ ነፍጠኞች ወይም ነጋዴዎች ወደ አገር ቤት በተመለሱ ጊዜ ዕጣን እያጨሱ ቡና ይጠጡ ነበርና ሌላውም እነሱን አይቶ ተከተለ። ይልቁንም የየመንደሩ ሴቶች የቡና ማኅበር እያበጁና ተራ በተራ እየተጠራሩ ቡና ሲያፈሉና ሲጠጡ መዋል ጀመሩ። ይኸውም ልማድ በባላገርም ሆነ በከተማ እየተስፋፋ ስለሄደ ብዙ ሰው የቡና ሱሰኛ ሆነ።
በዚያ ጊዜው ጨዋው ህዝብና የቤተ ክህነት ሰዎች ዕጣን አጭሶ ቡና መጠጣትን እንደ ነውር ወይም እንደ አምልኮ ባዕድ አድርገው ይመነለከቱት ነበር። ስለዚህም እነዚያን የቡና ማኅበርተኞች በመንቀፍ
ነይ ቡና ጠጪ
መቼም አታዳምጪ
ነጭ ቡና* እንጠጣ
ድሩም ማጉም መጣ
እየተባለ በየሠርግ ቤቱ ይዘፈን ጀመር። ሆኖም ውሎ አድሮ ነቀፌታውና ነውርነቱ እየቀረ ሄዷል።»
-------
*ነጭ ቡና፡ «በዚያን ጊዜ ድርና ማግ ሲዘጋጅ ደቦ ጠርቶ፣ ቡና እየጠጡ የማስፈተል ባህል ተለምዶ ስለነበር «ነጭ ቡና» ማለታቸው ከድርና ከማጉ ጋር በማያያዝ ዘፋኞች ለፌዝና ለነቀፋ ይዘፍኑት የነበረ ነው። ምንጭ - አቶ ሥዩም ዘነበ (አቶ ሥዩም የታሪክ ጸሐፊው ዘመድ፣ በ90 ዓመት ዕድሜው አሁንም በሕይወት ያለ ነው።)»
----
ምንጭ፡ ትዝታዬ፣ ስለራሴ የማስታውሰው፣ ገጽ 102
መልካም ዐርብ ☕️ ለቡና ወዳጆች በሙሉ ፡)

የአዲስ መጽሐፍ ማስታወቂያ፡ Pierre Guidi's Educating the Nation in Ethiopia: State, Society and Identity in Wolaita (1941-1991)
በጎንደር ዘመነመንግሥት ከሮ ስለነበረው የተዋሕዶዎች እና የቅባቶች የሃይማኖት ክርክር
የቅብዓቶች ባህል «የእግዚአብሔር ቃል በድንግል ማርያም ማኅፀን ሲፀነስ ከእርስዋ የተነሣው ሥጋ በመንፈስ ቅዱስ ቅብዓት የአብ የባሕርይ ልጅ ሆነ» ሲል
የተዋሕዶዎች ደግሞ «የእግዚአብሔር ቃል በድንግል ማርያም ማኅፀን ሲፀነስ ከእርስዋ የተነሣው ሥጋ በተዋሕዶ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆነ» የሚል ነው።
ታድያ በጎንደር ዘመነ መንግሥት የነዚህ ሁለት ዕይታዎች ክርክር በየዘመኑ እየተነሣ እርስበርስ ሲሸናነፉና በአዋጅ ሲያስነግሩ ኖረዋል።
ለምሳሌ፡
«በአእላፍ ሰገድ ዮሐንስ ዘመን፣ 1672 ዓ.ም. ጥቅምት 10 ቀን የሃይማኖት ጉባኤ ቆሞ ነበርና የቅብዓቶች አፈ ጉባኤ አባ አካለክርስቶስና የተዋሕዶዎች አፈ ጉባኤ አባ ኒቆላዎስ በየበኩላቸው ከመጻሕፍት እየጠቀሱ በንጉሡ ፊት በብዙ ተከራከሩ። በክርክሩም ላይ አባ አካለክርስቶስ ተረትቶ ጳጳሱና እጨጌው አወገዙት። ንጉሡ አእላፍ ሰገድ ዮሐንስም የተዋሕዶዎችን መርታት የቅብዓቶችን መረታት አይተው «ከበረ ሥጋ በተዋሕዶ» ተብሎ አዋጅ እንዲነገር አደረጉ። እርሳቸው ራሳቸው ግን የግል እምነታቸውን ሲገልጡ «እኔ ራሴ በተረቺዎቹ በኩል ነኝ» ብለው ተናገሩ ይባላል።»
እንዲሁም፡ «ቅብዓቶች በአድራር ሰገድ ቴዎፍሎስና በአድባር ሰገድ ዳዊት ዘመን አሸናፊዎች ሆነው ነበርና «በቅብዓት የባሕርይ ልጅ» እንዲባል ዓዋጅ እየተነገረላቸው ደስ የተሰኙበት ጊዜም ነበር።»
ምንጭ፡ ትዝታዬ - ስለራሴ የማስታውሰው (1891–1923)
በመርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፣ ገጽ 112–113

ሰላም ጤና
ኢቲቪ/አሁን EBC/ የሚሠራ ሰው አለ እዚህ? ወይ እዛ የሚሠራ ሰው የሚያውቅ? ከarchives ክፍል መረጃ ፈልጌ ነው። አመሰግናለሁ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ማዕከል የአሁኑ ሐሙስ እና አርብ አንድ ጉባኤ እና ዐውደረእዕይ ያካሂዳል። ስለባርያ ንግድ ነው። ማስታወቂያው ይኼው:
ዘንድሮ ቀኃሥ ሃምቡርግ /ጀርመን ሀገር/ የመጡበትን 70ኛ ዐመት በማስመልከት ነፍ ፕሮገራሞች ተዘጋጅተዋል። አንዱ ትናንት የተለቀቀው የNDR ዝግጅት ነው። የኛ ተቋም ሰዎችም አሉበት ማየት ለምትፈልጉ :-)
https://www.ndr.de/fernsehen/sendungen/hamburg_journal/Hamburg-damals-Kaiser-von-Aethiopien-kommt-1954-nach-Hamburg,hamj153340.html

NDR Mediathek
Hamburg damals: Kaiser von Äthiopien kommt 1954 nach Hamburg
Haile Selassie ist das erste ausländische Staatsoberhaupt nach dem Zweiten Weltkrieg, das Deutschland einen Staatsbesuch abstattet.
Prague የሚዘጋጀው የአፍሪካ ጥናት ኮንፍረንስ call for papers/abstracts ከተለቀቀ ሰንብቷል፡
https://www.ecasconference.org/2025/call-for-papers/

የሚመጣው ሳምንት ረቡዕ ኅዳር 18 ቀን፣ በኢትዮጵያ ሰዐት አቆጣጠር 8 ሰዐት ላይ “Rethinking Political Legitimacy: Tewodros II and the Fekkare Iyesus” በሚል ርዕስ ፐሬዘንቴሽን/ሌክቸር አቀርባለሁ። መሳተፍ የምትፈልጉ በዚህ ዙም አድራሻ መቀላቀል ትችላላችሁ።
https://uni-hamburg.zoom.us/j/92260268033?pwd=YkpBUXNlV3kzdEZhT3p4TUJONlpFQT09

Zoom Video
Join our Cloud HD Video Meeting
Zoom is the leader in modern enterprise video communications, with an easy, reliable cloud platform for video and audio conferencing, chat, and webinars across mobile, desktop, and room systems. Zoom Rooms is the original software-based conference room solution…
አቤ ጉበኛ አንድ ለናቱ መግቢያ ላይ የጻፈውን አይታችኋል? እዩትማ:
ጳውሎስ ኞኞ “ይህን ሥራ ስሠራ ከሚስቴ ውጪ ያገዘኝ ማንም የለም። ደኅና እንሁን ብቻ” ካለው ጋር ተመሳሰለብኝ 😄
ሁለቱም የቴዎድሮስ ታሪክ መጽሐፎቻቸው ላይ ነው ደግሞ እንዲህ ያሉት። የካሳ ወኔ ነሸጥ እያረጋቸው ነው?