EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)
137K subscribers
38.9K photos
476 videos
80 files
13.2K links
EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation) @etvafaanoromoo1
@ETVkidschannel
@EBCWORLD1
@etventertainment1
Download Telegram
ማስታወቂያ

ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ በቦሌ ፍላሚንጎ 7000 ካሬ ላይ ያረፈ 700 የመኪና ማቆሚያ ያለው ከ500 በላይ ሱቆች ያሉት የንግድ ማዕከል ኖህ ኮንቬንሽን!

ለበለጠ መረጃ 6100 ላይ ወይም 0948111111 ይደውሉልን!

ወይም በውጭ የስልክ መስመራችን: +1 571-547-2858

ያልተገነባ አንሸጥም!

ለበለጠ መረጃ 6100 ላይ ወይም 0948111111 ይደውሉልን!

ወይም በዉጭ የስልክ መስመራችን : +1 571-547-2858

ያልተገነባ አንሸጥም!

#Noahrealeastae #Appartment #house #noahoasis #location #home #gurdshola #guesthouse #Investment #investmentstrategies
8👍2👏1
የሀገራችን ብሩህ ተስፋ የሚጀምረው ከእርስዎ ድምፅ ነው
*******************

የሀገራችንን ዕድል ለመወሰን እና የነገዋን ኢትዮጵያ በጋራ ለመገንባት የመጀመሪያው እርምጃ የመራጮች ምዝገባ ነው።

ድምፅ መስጠት መብትዎ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚከፈል ታላቅ ውዴታም ጭምር ነው።

የምዝገባ ጊዜ፦ ከየካቲት 7 እስከ መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም

በቀኑ በመመዝገብ፣ ነገ የሀገርዎን መጻኢ ዕድል በድምፅዎ ይወስኑ! የምዝገባ ካርድዎን መውሰድዎን አይዘንጉ።

"ዛሬ እንመዝገብ፤ ነገ በድምፃችን እንወስን!"
20👍2
ማስታወቂያ
የሲንቄ ባንክን QR Code በመጠቀም በሱፐር ማርኬቶች፣ በካፍቴሪያዎች፣ እና በሌሎች የንግድ ተቋማት ተገልግለው ሲያበቁ በቀላሉ ክፍያዎን ይፈፅሙ!
#Siinqee_Bank #Baankii_Siinqee #ሲንቄ_ባንክ #Siinqee_Digital #Siinqee_Ihsan #EMPOWERED_TOGETHER
6👍1
ለመመካከር ፈቅዶ የመቀመጥ ጠቀሜታዎች
*************

በዓለማችን ላይ የሚገኙ የተለያዩ ማህበረሰቦች በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ እያለፉ ችግሮቻቸውንም በራሳቸው እየፈቱ አሁን ላለበት የስልጣኔ ደረጃ ደርሰዋል።

አብዛኛው አፍሪካዊ ማህበረሰብ ግጭቶችን የሚፈታበት መንገድ ተቀራራቢነት ቢኖረውም፤ ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው አንድ ቁልፍ ድርጊት አለ፤ እርሱም ለመነጋገር መቀመጥ ነው።

ለመመካከር መቀመጥ ለሀገራዊ ምክክር፣ ለግጭት አፈታት እና ለሌሎች የሰላም ግንባታ ሂደቶች ምን ዓይነት በጎ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ለሚለው የሚከተሉት ሀሳቦች ያብራራሉ፦

👉ሥነ-ልቦናዊ ጠቀሜታዎች፡-በግጭት ውስጥ ያሉ አካላት ለመነጋገር ፈቅደው ሲቀመጡ በርካታ ጠቀሜታዎች እንደሚገኙ በዚህ ዙሪያ የተካሄዱ ጥናቶች ያስረዳሉ።

ሰዎች ለመነጋገር ሲቀመጡ የመንፈስ መረጋጋት ውስጥ በመሆን፣ ራሳቸውን በመግዛት እና የማመዛዘን አቅማቸውን በመጠቀም የተረጋጋ ስብዕናቸው ዕውን ይሆናል፤ ይህም ለውይይት እና ለምክክር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።

👉ዲሞክራሲያዊ ጠቀሜታዎች፡-ለመመካከር መቀመጥ ራሱን የቻለ የእኩልነት መገለጫ ነው። ሁሉም አካላት ለንግግር ሲቀመጡ አንዳቸው ከሌላቸው እንደማይበልጡ ማሳያ ነው።

ከዚህም ባሻገር ሀገራዊ ምክክርን በሚመስሉ መድረኮች ላይ ሰዎች ክብ ቅርፅ ሰርተው መቀመጣቸው የሀይል ሚዛንን ለማመጣጠን ይረዳል።

👉ማህበራዊ መተማመንን መሰረት ያደረጉ ጠቀሜታዎች፡-በሀገራዊ የምክክር ሂደት የሁሉም ባለድርሻ አካላት በአንድነት ለመነጋገር መቀመጥ እና መዘጋጀት እርስ በእርስ እንዲተማመኑ ያስችላቸዋል።

ይህም አንዱ ወገን ሌላኛው ወገን ያጠቃኛል ብሎ ከማሰብ ይልቅ፤ ተቃውሞውን፣ ስጋቱን እና ፍላጎቶቹን ለመናገርና የሌላውን ለማድመጥ እንዲፈቅድ በማድረግ መተማመንን ያጎለብታል።

*የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን
14🔥3🙏3👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ቃል በተግባር !

በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ለሃይቅ የተበረከተ ድንቅ ስጦታ!

#ገበታለትውልድ

#PMOEthiopia
18👏4🔥2
ምርጫው አካታች እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ
*****************

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ያካተተና አሳታፊ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሴቶች፣ የወጣቶችና የአካል ጉዳተኞች ተሳትፎን ለማሳደግ ያለመ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሯ፤ ምርጫው ነፃ፣ ተዓማኒና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፏቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸው ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ነዋይ በበኩላቸው፤ ምርጫው አካታችና ፍትሐዊ እንዲሆን ቦርዱ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፤ የሁሉም ክልሎች የዘርፉ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እና የተለያዩ አደረጃጀት ተወካዮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በአባዲ ወይናይ
28👍2
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ይሰጣል - ትምህርት ሚኒስቴር
*******
በዚህ ዓመት የሚሰጠውን የ2018 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግማሽ ዓመት አፈፃፀም መድረክ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ዓመት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መቶ በመቶ በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
ባለፉት ሁለት ዓመታት ፈተናው በወረቀትና በበይነ መረብ ሲሰጥ እንደረበር አንስተው በዚህ ዓመት የሚሰጠውን ማጠናቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመዋል።

ክልሎች በዚህ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች እንዳይኖሩ በቂ ኮምፒዩተር ፣ ኔትዎርክና አማራጭ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ልዩ ትኩረት ሰጥተው መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበው ለተማሪዎች በቂ ሥልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
32👏5🔥42
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀመሩ
**************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፤ ዛሬ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የሰው አልባ ፖሊስ አገልግሎት ወይም ስማርት ፖሊስ አገልግሎት አስጀምረናል ብለዋል።

‎ይህ አገልግሎት ዜጎች የፖሊስ አገልግሎትን በተሻለ ፍጥነት እና በቴክኖሎጂ ታግዘው እንዲያገኙ እንደሚያስችል ገልፀዋል።

በተጨማሪም አገልግሎቱ ለፖሊስ ፈጣን እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችለው እና የወንጀል መከላከል ስራውን የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል።

የዚህ አገልግሎት መጀመር በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የህግ አስከባሪ አካላት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የተጀመረው የሪፎርም ስራን ውጤታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።

#EthiopianBroadcastingCorporation #Ebcdotstream #Ethiopia
32👍19🔥6🤣2🥰1
ኢትዮጵያ - የአፍሪካዊያን የጋራ ቤት!

"ልባችንን ከፍተን፣ እጆቻችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን።
በክብር እንቀበላቸው፤ በፍቅር እናቆያቸው!"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
37👍7🙏7👏6🔥3🕊2