❤57👍17🤔4
ባንካችን አቢሲንያ የ2024/25 የበጀት ዓመት የሥራ አመራር ጉባዔውን አካሄደ

አቢሲንያ ባንክ የተጠናቀቀውን የ2024/25 በጀት ዓመት የሥራ አመራር ጉባዔውን ሐምሌ 17 እና 18 ቀን 2017 ዓ.ም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሲያካሂድ ቆይቶ ሊበረታቱና ሊሻሻሉ የሚገባቸውን የሥራ አፈፃፀሞች በመለየትና የባንኩን ቀጣይ ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ በስኬት ተጠናቅቋል።

በስብሰባው ላይ በዋና ዋና ቁልፍ መለኪያዎች አፈፃፀም ከዕቅድ አንፃር የተሠሩ ሥራዎች በዲስትሪክቶች በሰፊው የተነሱ ሲሆን አፈጻፀማቸው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንፃር የበለጠ የተሳካበት ዓመት እንደነበረ ተገልጿል።

የዲጂታል ዘርፉን ለማሳደግ በባንካችን እየተተገበረ በሚገኘውና ባንካችንም የሚታወቅበትንና የኢንዱስትሪው መሪነቱን ባረጋገጠበት የዲጂታል ዘርፍም  አዳዲስ የቴክኖሎጂ አሰራሮችን በመተግበር ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ማምጣት ይቻል ዘንድ ሁሉም ዲስትሪክቶች እንዲሁም በዋናው መ/ቤት የሚገኙ የሥራ ክፍሎች ሥራቸው የተገመገመበት ጉባዔ ነበር፡፡

በጉባዔው በአፈፃፀማቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች የምስጋና እና ማበረታቻ የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው ሲሆን ሽልማታቸውንም ከባንካችን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ መኮንን ማንያዘዋል እና ከባንካችን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ ተረክበዋል፡፡

በዚህም መሠረት የሃዋሳ ዲስትሪክት የአንደኝነትን ደረጃን ሲቀዳጅ በሁለተኝነት የምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት እንዲሁም የመካከለኛው አዲስ አበባ ዲስትሪክት በ3ተኛነት ደረጃ አጠናቀዋል፡፡

በተጨማሪም በዓመቱ አፈፃፀም ልዩ ተሸላሚና ዕውቅና የተሰጠው በተለይም የዓመቱን ተጨማሪ  የተቀማጭ ሂሳብ ዕድገት አፈፃፅም ከተከታታይ ሩብ ዓመታት አንፃር በመጨረሻዎቹ ሩብ ዓመታት በከፍተኛ  መሻሻል  /Great Come Back/ አበረታች ዉጤት ላስመዘገበው የጂማ ዲስትሪክት የዕውቅና ስርተፍኬት ተሰጥቶታል።
ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚሁ ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባዔ ላይ የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ አመራር አባላት፣ የባንኩ ሥራ አመራር አባላት፣ የዋናው መ/ቤት እና የዲስትሪክት ዳይሬክተሮች እንዲሁም የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
❤88👍23👏7🤔6🔥2🤩2😱1
ተጨማሪ ጉርሻ !
ውድ ደንበኛችን ከውጪ ሃገር በደሃብሺል፣ በዌስተርን ዩኒየን፣ መኒግራም፣ ትራንስ ፋስት፣ ወርልድ ሬሚት፣ ቴራፔይ፣ ኢትዮ ዳሽ፣ ሪያና ሌሎች ገንዘብ አስተላላፊዎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን በኩል ሲቀበሉ ወይም ሲመነዝሩ፤ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን ከቀልጣፋ መስተንግዶ ጋር ተጨማሪ ጉርሻ እናበረክትልዎታለን!

አቢሲንያ
የሁሉም ምርጫ!
የባንካችን ትክክለኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች Facebook Instagram LinkedIn Twitter Website TikTok Telegram
❤20👍1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአቢሲንያ ባንክ ከወረቀት ንክኪ ነጻ  ሞዴል ቅርንጫፍ የምርቃት ሥነ-ሥርዓት ቀጥታ ስርጭት

ባንካችን አቢሲንያ ከወረቀት ንክኪ ነጻ ሞዴል ቅርንጫፉን  ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በዋናው መ/ቤት በታላቅ ድምቀት እያስመረቀ ይገኛል። እንኳን ደስ አላችሁ ! እንኳን ደስ አለን! እያልን የቀጥታ ስርጭቱን በፌስቡክ እና በኢንስታግራም እንድትከታተሉ እንጋብዛለን። መልካም ቀን! ON FACE BOOK : https://www.facebook.com/share/v/1CPAfb2WJH/ ON INSTAGRAM: https://www.instagram.com/abyssinia_bank/ ON LINKEDIN: https://www.linkedin.com/video/live/urn:li:ugcPost:7354780887864991744/
❤46👏14😱2👍1
ባንካችን አቢሲንያ በሁሉም ቅርንጫፎቹ ወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎት መስጠት ጀመረ
ባንካችን አቢሲንያ በዛሬው ዕለት በአዲስ መልክ በተዋቀረው የባንካችን ራስ ልዩ ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ፣ የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የበላይ የሥራ አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የወረቀት አልባ የባንክ አገልግሎቱን በይፋ አስመርቆ ስራ አስጀምሯል።
ይህ አዲስ አሠራር ገንዘብ ማስተላለፍ፣ ጥሬ ገንዘብ ማስገባትና ማውጣት፣ ሒሳብ መክፈትና ሌሎች በቅርንጫፍ በኩል የሚሰጡ ማናቸውንም አገልግሎቶች በራስ አገዝ ወይም በሠራተኞች በመታገዝ ደህንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ነው፡፡
አገልግሎቱ ስማርት ኪዮስኮችንና ታብሌቶችን እንዲሁም የጣት አሻራንና የፊት ገጽን እንደ መለያ የሚጠቀም ሲሆን፣ ጊዜ የሚወስዱ የአሠራር ሂደቶችን በማስወገድ የባንካችንን የአገልግሎት ደረጃ ፈጣን፣ አስተማማኝና ግልጽ ከማድረግ አኳያ ጉልህ ለውጥ የሚያመጣ ይሆናል፡፡
በተጨማሪም ደንበኞች ወረፋ መጠበቅ ሳያስፈልጋቸው ፈጣን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የጥሬ ገንዘብ መቀበያና መክፈያ /Recyclers/ እና በመጠኑ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ለመቀበል የሚያስችሉ ማሽኖች /Bulk Deposit Machines/ በተመረጡ ቅርንጫፎች የተዘጋጁ ሲሆን፣ በቀጣይም በሁሉም ቅርንጫፎች ተደራሽ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
አገልግሎቱ የእንግሊዝኛ ቋንቋን ጨምሮ በተለያዩ ሃገራዊ የቋንቋ አማራጮች ማለትም በአማርኛ፣ በአፋን ኦሮሞ፣ በሱማሊኛ፣ በትግሪኛ፣ በአፋርኛና በሲዳምኛ የቀረበ ሲሆን፣ ሁሉንም ደንበኞች ማዕከል ባደረገ መልኩ የዕድሜ፣ የትምህርት ደረጃ ወይም ሰዎች ለቴክኖሎጂ ባላቸው የክህሎት መጠን የማይገደብ፣ ቀላል፣ አመቺና ተስማሚ ተደርጎ የቀረበ ነው፡፡
❤148👍25🥰7🤩4🤔2