TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.3K photos
1.48K videos
5 files
3.37K links
Download Telegram
ግብጽ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናበተች!

በአፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጇ ግብጽ በደቡብ አፍሪካ ተሰናብታለች፡፡ ትናንት ምሽት በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ አስተናጋጇን ግብጽን 1ለ0 አሸንፋ ለሩብ ፍጻሜ ደርሳለች፡፡ ግብጽ በጥሎ ማለፉ በመሰናበት ካሜሩንን ተከትላለች፤ ደቡብ አፍሪካ ደግሞ ካሜሩንን 3ለ2 አሸንፋ ካሰናበተችው ናይጀሪያ በሩብ ፍጻሜ ትጫወታለች፡፡

Via #ENA
@tikvahethsport
#ETHIOPIA🇪🇹

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች በሮም ማራቶን አሸንፈዋል።

በሴቶች አትሌት ሴቻለ ደለሳ አዱኛ 2:26:08 በሆነ ጊዜ በቀዳሚነት ስትገባ ኬንያዊቷ አትሌት ግላዲስ ጄሩቶ በ2:28:46 በሆነ ሰዓት ሁለተኛ እንዲሁም ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ታደለች ነዲ በ2:31:00 ሰዓት በመግባት ሶስተኛ ወጥታለች።

በወንዶች ደግሞ አኢትጵያዊው አትሌት ፍቅሬ ፍቅሬ በቀለ ተፈራ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል በ2:06:48 በሆነ ሰዓት በመግባት በቀዳሚነት ውድድሩን አጠናቋል። #ENA

@tikvahethsport
" በሰላም ገብተዋል "

በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል።

ነገ በተመረጡ የመዲናችን አካባቢዎች ህዝቡ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያ ከፍ ላደረገው የአትሌቲክስ ቡድን አድናቆት በመግለፅ አቀባበል ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

#ENA

@tikvahethiopia