TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ዋልያዎቹ ሁለተኛ ልምምዳቸውን ሰርተዋል !

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር ላለበት ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች ሁለተኛ ልምምዱን በዛሬው ዕለት በንግድ ባንክ ሜዳ መስራት ችሏል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ሀይሌ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00 በንግድ ባንክ ሜዳ ሁሉም ተጨዋቾች በተገኙበት ሁለተኛ ልምምዱን ሰርቷል።

በቅርቡ ወደ ግብፅ ያመራው የፊት መስመር አጥቂው አቤል ያለው በበኩሉ የብሔራዊ ቡድንን ስብስብ ተቀላቅሎ ልምምዱን ሰርቷል።

ሁሉም የብሔራዊ ቡድኑ ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ሲታወቅ በልምምድ ወቅት የእርስ በርስ ጨዋታም ማድረግ ችለዋል።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን የሚያደርገው የሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ዛሬ አዲስ አበባ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የፊታችን ሐሙስ እና እሁድ ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር በአዲስ አበባ ስታዲየም ጨዋታዎችን ያደርጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አዲስ ምባፔ መፈለግ እመርጣለሁ " ራትክሊፍ

የማንችስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ አሁን ላይ ኪሊያን ምባፔን ከመግዛት ይልቅ አዲስ ምባፔ መፈለግ እንደሚመርጡ ገልጸዋል።

" ስኬትን ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ከማውጣት ይልቅ አዲስ ኪሊያን ምባፔን መፈለግ እመርጣለሁ " የሚሉት ባለሀብቱ አሁን ላይ ምባፔን ማስፈረም ብልህ መሆን አይደለም አዲሱን ምባፔ ፣ ቤሊንግሀም ወይም ሮይ ኪን ማግኘት ነው ብልህነት።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምባፔ ደስተኛ እንዲሆን እመክረዋለሁ " ፊጎ

የቀድሞ ፖርቹጋላዊ ተጨዋች ሉዊስ ፊጎ ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ እንደሱ ወደ ሪያል ማድሪድ በመሄድ ደስተኛ እንዲሆን ምክሩን ለግሶታል።

" ደስተኛ መሆን በህይወት ውስጥ አስፈላጊው ነገር ነው " የሚለው ሉዊስ ፊጎ እኔ ደስታን ፈልጌ ነበር እናም ለሪያል ማድሪድ ፈርሜ አምስት አመት ቆይቻለሁ ምባፔን የምመክረው ደስተኛ እንዲሆን ነው።ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🇪🇹 ዋናው 🤝 አአዩ ስፖርት ፌስቲቫል 🇪🇹

ዋናው ስፖርት አጋር የሆነበት ደማቁ የ2016 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ፌስቲቫል በአጓጊ ፉክክር እየተካሄደ ነው። ውድድሩ እስከ መጋቢት 14 በድምቀት የሚቀጥል ይሆናል።

ውድድር ካለ #ዋናው አለ!

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
" ትልቅ ተጨዋች ማምጣት ዩናይትድን አይቀይረውም "

ማንችስተር ዩናይትድን ለማሻሻል ብዙ ገንዘብ ማውጣት እና ትልቅ ተጨዋቾችን ማምጣት መፍትሔ አለመሆኑን እንግሊዛዊው ቢሊየነር ሰር ጂም ራትክሊፍ ተናግረዋል።

ሰር ጂም ራትክሊፍ በንግግራቸውም " ማንችስተር ዩናይትድን ለማሻሻል ለትልቅ ተጨዋቾች ብዙ ገንዘብ ማውጣት መፍትሔ አይሆንም ክለቡ ይህንን ለአስር አመት አድርጎታል።

ለውጥ ለማምጣት መጀመሪያ መደረግ ያለበት ትክክለኛ ሰዎችን በትክክለኛው ቦታ ላይ ማስቀመጥ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

የዚህን አመት የሊግ ዋንጫ ማን ቢያሸንፈው ይመርጣሉ ተብለው የተጠየቁት ሰር ጂም ራትክሊፍ " ሁሉንም እጥላቸዋለሁ የትኛውም እንዲያሸንፍ አልፈልግም ጠላቶቻችን ናቸው።"ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤሪክሰን በክለቡ ደስተኛ አለመሆኑን ገለፀ !

ዴንማርካዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ክርስቲያን ኤሪክሰን በማንችስተር ዩናይትድ ቤት በቂ የጨዋታ ጊዜ ባለማግኘቱ ምክንያት ደስተኛ አለመሆኑን ተናግሯል።

" የጨዋታ ጊዜ ባለማግኘቴ ደስተኛ እንዳልሆንኩ ለአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ ነግሬዋለሁ እሱም ኮቢ ማይኖ እና ሌሎች አማካዮች ጥሩ እየሰሩ መሆኑን ነግሮኛል። " ኤሪክሰን

ክርስቲያን ኤሪክሰን በዘንድሮው የውድድር አመት በሁሉም ውድድሮች ለማንችስተር ዩናይትድ የተጫወተው ለ 116 ደቂቃዎች ብቻ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያደርጋል !

የላሊጋው ክለብ ሪያል ማድሪድ በሚቀጥለው ክረምት የቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ በማምራት የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ሎስ ብላንኮዎቹ በአሜሪካ ቆይታቸው ሐምሌ ወር መጨረሻ ከካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ጋር የኤል ክላሲኮ ፍልሚያቸውን በሚትላይፍ ስታዲየም የሚያደርጉ ይሆናል።

በተጨማሪም ከጣልያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን እና ከፕርሚየር ሊጉ ክለብ ቼልሲ ጋር በአሜሪካ የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ጫማ የሰቀልኩት በተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት ነው " ሀዛርድ

ቤልጂየማዊው የቀድሞ የቼልሲ እና ሪያል ማድሪድ ተጨዋች ኤደን ሀዛርድ ጫማውን ለመስቀል የተገደደው ባጋጠመው ተደጋጋሚ ጉዳት ምክንያት መሆኑን አስረድቷል።

" ከእግር ኳስ ለመራቅ የወሰንኩት በሚያጋጥሙኝ ተደጋጋሚ ጉዳቶች ምክንያት ነው ፣ በዚህ ውሳኔዬ ደግሞ አልፀፀትም።"ሲል ኤደን ሀዛርድ ተናግሯል።

ወደኋላ ተመልሶ በነጩ የሪያል ማድሪድ ማልያ ያለውን ምስሎች ሲመለከት ትልቅ ኩራት እንደሚሰማው ኤደን ሀዛርድ አያይዞ ገልጿል።

በቀጣይ ፕሮፌሽናል አሰልጣኝ የመሆን እቅድ እንደሌለው የገለፀው ሀዛርድ " ነገርግን ታዳጊዎችን ማሰልጠን እችላለሁ እኔም ልጆች አሉኝ እግርኳስን እንዴት መጫወት እንደሚችሉ ላስተምራቸው እፈልጋለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ወደ አሜሪካ ያመራል !

ማንችስተር ሲቲ በሚቀጥለው ክረምት የቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ በማምራት የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት በአሜሪካ በሚኖረው ቆይታ ከሴልቲክ ፣ ኤሲ ሚላን ፣ ባርሴሎና እና ቼልሲ ጋር በተከታታይ የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደሚያደርጉ አሳውቀዋል።

የወዳጅነት ጨዋታዎቹ መቼ ይደረጋሉ ?

- ከ ሴልቲክ :- ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም

- ከ ኤሲ ሚላን :- ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም

- ከ ባርሴሎና :- ሐምሌ 23/2016 ዓ.ም

- ከ ቼልሲ :- ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና ወደ አሜሪካ ያቀናል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና በሚቀጥለው ክረምት የቅድመ ውድድር ዝግጅት ወደ አሜሪካ በማቅናት የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ ይፋ አድርጓል።

ባርሴሎና በአሜሪካ ቆይታቸው የኤል ክላሲኮን ጨምሮ ሶስት የወዳጅነት ጨዋታዎችን የሚያደርጉ ይሆናል።

የባርሴሎና የአሜሪካ ጨዋታዎች ምን ይመስላሉ ?

- ከ ማንችስተር ሲቲ :- ሰኔ 23/2016 ዓ.ም

- ከ ሪያል ማድሪድ :- ሐምሌ 27/2016 ዓ.ም

- ከ ኤሲ ሚላን :- ሐምሌ 30/2016 ዓ.ም የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኮቢ ማይኖ ለብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ቀረበለት !

የማንችስተር ዩናይትድ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኮቢ ማይኖ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ እንደቀረበለት ይፋ ተደርጓል።

በቀያይ ሴጣኖቹ ቤት ድንቅ ጊዜን በማሳለፍ ላይ የሚገኘው የ 18ዓመቱ ተጨዋች ኮቢ ማይኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ቀርቦለታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በመዲናችን አይን ቦታ ከቦሌ በ7ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ለቡ መብራት በተንጣለለው 65,395ካሬ ላይ ያረፈ ሠፊ መንደር፤ 5  የመዋኛ ገንዳወች፣ የከርሰምድር ውሀ፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ስፍራወችን እያንዳንዱ ህንጻወች 5 ቤዝመንት፣ ሠፊ ሰገነት፣ 5 ሊፍቶች ያላቸው፣ 50% ባንክ የተመቻቸለት፤

እጅግ ዘመናዊ በሆነው የግንባታ መሳሪያ በኮንካል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከእስቱዲዎ እስከ ባለ 4መኝታ ድረስ እንዲሁም የንግድ ሱቆችን በማራኪ ዲዛይንና በላቀ ጥራት የተዘጋጁ፤

እስከ 25% የዋጋ ቅናሽ (6,000,000ብር)
10% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም  ስትድዮ 👉56.6ካሬ=605,000ብር
    
አንድ መኝታ
    👉77.7ካሬ,=831,000ብር
ሁለት መኝታ
     👉123.3ካሬ=1,318,000ብር
ሶስት መኝታ
    👉146.8ካሬ=1,570,000ብር
አራት መኝታ
      👉186.9ካሬ=1,998,000ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ልብ ይበሉ አንድ ቤት ሲገዙ አንድ ቤት በነፃ አለው።

ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251988887999
       +251918642895
     ሀሎ      ይበሉ።
https://t.iss.one/Engineergashaw
የአውሮፓ ዋንጫ የውድድር ማጣሪያ ጨዋታዎችን እና የተለያዩ የዓለም አቀፍ ውድድሮችን በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት በቀጥታ እንመልከት!

👉 ዛሬውኑ ፓኬጅዎን ያሳድጉ። ጨዋታዎችን ከትንታኔ ፣ ከተጫዋች ብቃት እስከ ቡድን ወኔ በሱፐርስፖርት ይከታተሉ!!

📣 ትንሽ ጊዜ ብቻ የቀረው የዲኤስቲቪ ስጦታ 📣

👉ከጥር 6 እስከ መጋቢት 22 ለቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ደንበኝነትዎን ወደ ሜዳ ፕላስ ፓኬጅ ሲያሳድጉ...
እኛም ቀጣዩን የፕሪሚየም ፓኬጅ ለአንድ ወር እንጋብዝዎታለን!

የዲኤስቲቪ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram bot ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#GreatestFootballSeason #DStvEthiopia #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvSelfServiceET #Euro2024