TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
" ለሀገሬ 🇪🇹 ክብር ስል ሪከርዱን አስመልሳለሁ " አትሌት ለተሰንበት ግደይ 

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ 5000ሜትር ሪከርድ በኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ከሀገራችን ስለተወሰደበት መንገድ ስትናገር ቁጭት ውስጥ ሆና ነው።

የ 1500ሜትር የገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ ከዛም በቀናት ልዩነት የራሷ የ 5000ሜ ሪከርድ በፌዝ ኪፕዬጎን ሲሰበር መመልከት " የሀገር ክብር " እንደመነካት ነው ትላለች።

" የሚፈለገው ብር አይደለም ሁለቱ ሪከርድ ከሀገራችን ሲወጣ በጣም ተበሳጭቻለሁ " የምትለው ለተሰንበት ግደይ " ይህን ሪከርድ እንደማስመልስ ቃል እገባለሁ ለራሴ #ሳይሆን ለሀገሬ #ኢትዮጵያ ክብር ስል " ትላለች።

በስተመጨረሻም " ኢትዮጵያ ሀገራችን ሁሌም የወርቅ ሀገር እንድትሆንልኝ እመኛለሁ " ስትል ንግግሯን ትቋጫለች።

የአለም ሻምፒዮናው በነገው ዕለት ሲጀምር በ 10,000ሜትር ፍፃሜ የምትወዳደረው ለተሰንበት ግደይ እንደ ኦሪገን ውድድር ሁሉ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ ለማምጣት ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe