TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ሮማ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በጣልያን ሴርያ የሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሮማ ከጁቬንቱስ ጋር ያደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሮማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ጂያንሉካ ማንቺኒ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሮማ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ሽንፈት ያስተናገደው ጁቬንቱስ በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሮማ ከ ሳሱሎ እንዲሁም ጁቬንቱስ ከ ሳምፕዶርያ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ቡና ከወላይታ ድቻ ነጥብ ተጋርተዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

ቡናማዎቹ በተከታታይ ያደረጓቸውን አራት የሊግ መርሐ ግብሮች በአቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

ኢትዮጵያ ቡና አቻ መውጣቱን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ወላይታ ድቻ በበኩላቸው በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀያ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከ ፋሲል ከነማ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe