TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.3K photos
1.48K videos
5 files
3.37K links
Download Telegram
ኦዚል በፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ሜዜነት ታጅቦ ተሞሽሯል፡፡ የአርሰናሉ ጀርመናዊ ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋች ሜሱት ኦዚል ከእጮኛው የቀድሞ ቱርካዊት የቁንጅና አሸናፊ እና ሞዴል አሚኔ ጉልስ ጋር በቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይፕ ኤርዶጋን ሜዜነት ታጅቦ በባንክ ኦፍ ቦስፈረስ በሚገኝ ቅንጡ ሆቴል በትዳር ተሳስሯል፡፡

ይህ የ30 ዓመት ኮከብ በባለፈው ዓመት የሩሲያ ዓለም ዋንጫ መዳረሻ ላይ ከፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ጋር ፎቶ መነሳቱን ተከትሎ ከጀርመናውያኑ ጋር አቃቅሮታል፡፡

በዚህ የተነሳ ኦዚል ከዓለም ዋንጫው በኋላ ብሔራዊ ቡድኑ ከውድድሩ በጊዜ መሰናበቱን ተከትሎ ኦዚል ከአቅም በታች ተጫውቷል በማለት በጀርመናውያኑ ዘንድ የስድብ እና ትችት ደርሶበታል፡፡

እርሱም ስናሸንፍ እንደ ጀርመናዊ ስንሸነፍ ደግሞ እንደ ስደተኛ የምቆጠር ከሆነ ሁሉም ይቅር፤ በማለት በደጋፊዎቹ የዘረኝነት ትንኮሳ እንደደረሰበት እና እንዳልተከበረ ተናግሮ ከብሔራዊ ቡድኑ ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

በሰማኒያ የተሳሰሩት ሁለቱ ባለትዳሮች ከ2017 ጀምሮ ግንኙነት የጀመሩ ሲሆን በ2018 ሰኔ ወር ቀለበት አስረዋል፡፡

ከወራት በፊትም ሁለቱ ጥንዶች በሰርጋቸው ዕለት የሚታደሙ ወዳጆቻቸውን ጥሪ ሲያደርጉ የመጀመሪያው የሆኑት ከተለያዩ ሀገራት መሪዎች ጋር በፖለቲካዊ ጉዳዮች ቃላት ከመሰነዛዘር የማይቆጠቡት የቱርኩ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ናቸው፡፡ እሳቸው የጥሪ ካርዱን ከተቀበሉ በኋላ ለአንተ የሰርግ እና የደስታ ቀን የሚሆን ጊዜ አላጣም እመጣለሁ ብለው ነበር፡፡

እነሆ ፕሬዚዳንት ኤርዶጋን የምርጫ ቅስቀሳ እያላቸው ቃላቸውን አክብረው ከሁለቱ ሙሽሮች ጎን ቁመው በጋብቻ አስተሳስረዋል፡፡

ትዳራችሁ በፈጣሪ የተባረከ፤ ለወግ ለማዕረግ ያብቃችሁ በማለትም መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

የሜሱት ኦዚል ቤተሰቦች የዘር ሀረግ ከቱርክ የሚመዘዝ ቢሆንም እርሱ ግን የተጫወተው ለተወለደባት እና ለአደገባት ሀገር የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ነው፡፡

ቢቢሲ
Manchester United have made a bid of £84m for Napoli and Senegal defender Kalidou Koulibaly. (Source: Corriere dello Sport)
José Mourinho has told friends he would seriously consider managing Newcastle and is open to talks with the club's potential new owner Sheikh Khaled bin Zayed Al Nehayan. (Source: Sunday Mirror)
Antoine Griezmann has agreed to join PSG this summer. The forward was expected to leave Atlético Madrid for Barcelona but has opted to move to the French capital. (Source: SPORT)
Juan Mata signed a three-year deal at Manchester United today that will keep him at the club until 2022. (Source: SPORT)
#UpdateSport የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ባደረጉት ጨዋታ ያለምንም ግብ ሲለያዩ ደጋፊዎች አላስፈላጊ ምልክቶችን በማሳየት ከጨዋታው በፊትም መጠነኛ ግጭት መከሰቱ ተገልጧል። የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ እና የመቀሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ቡድኖች ጨዋታ ከዚህ ቀደም በጸጥታ ስጋት የተነሳ ተሰርዞ የፕሬሚየር ሊጉም ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ ተደርጎ ነበር።

Via #DW
@tikvahethsport
ፕላቲኒ ታሠሩ...

የቀድሞው የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚሼል ፕላቲኒ ፈረንሳይ ውስጥ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ፕላቲኒ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ለጥያቄ በመፈለጋቸው ነው ለእሥር የበቁት ተብሏል።

ፕላቲኒ የማህበሩ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት ኳታር ያለአግባብ የዓለም ዋንጫ አዘጋጅ ሆና እንድትመረጥ አግዘዋል በሚል ነው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት።

የ63 ዓመቱ የቀድሞ የፈረንሳይ መሃል መስመር ተጫዋች ፕላቲኒ ከአውሮፓ ኳስ መሪነታቸው የተወገዱት 2015 ላይ ነበር።

Via bbc
ፈርናንዶ ቶሬስ የእግር ኳስ ጨዋታ ማቆሙን አስታወቀ

የስፔን፣ የቼልሲ፣ የሊቨርፑል እና የአትሌቲኮ ማድሪድ አጥቂ ሆኖ ሲጫወት የኖረው ፈርናንዶ ቶሬስ እግር ኳስ ጨዋታ ማቆሙን አስታውቋል።

የ35 ዓመቱ ቶሬስ ላለፉት 18 ዓመታት አግር ኳስ የተጫወተ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት በጃፓን ጄ1 ሊግ ሳጋን ቶሱ እየተጫወተ ሲሆን በመጪው እሁድ እግር ኳስ ስላቆመበት አጠቃላይ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ገልጿል።

ቶሬስ የዓለም፣ የአውሮፓ፣ እና የሊግ ዋንጫዎችን ከሀገሩ ስፔንና ከተለያዩ ክለቦች ጋር አንስቷል።

ምንጭ፦ቢቢሲ
የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ በግብፅ ካይሮ ይጀመራል!

ለመጀመሪያ ግዜ 24 ቡድኖችን ያሳተፈው ሰላሳ ሁለተኛው የአፍሪካ ዋንጫ በግብጽ ካይሮ ዛሬ ይጀመራል፡፡ በመክፈቻው ጨዋታ አዘጋጇ ግብፅ ዙንባቤውን ከምሽቱ አምስት ሰአት ላይ የምታስተናግድ ይሆናል፡፡

የዘንድሮ የአፍሪካ ዋንጫ ካሜሮን በጸጥታና በዝግጅት ችግር ምክንያት አዘጋጅነቷ ተነጥቆ ለግብጽ የተሰጣት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የአፍሪካ ዋንጫ ኪዘህ ቀደም በጥር ወር ላይ የሚካሄድ ሲሆን ዘንድሮ ግን በሰኔ ወር እንዲካሄድ ተወስኗል፡፡

በግብጹ አፍሪካ ዋንጫ ካለው ሙቀት አንጻር በ32 ተኛውና በ75 ተኛው ደቂቃ የውሀ እረፍት የሚኖረው ይሆናል፡፡ ውድድሩ ከሰኔ 14 እስከ ሃምሌ 14 የሚካሄድ ሲሆን በስድስት ምድብ ተከፍሎ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የአፍሪካ ዋንጫ እኤአ በ19 57 በሱዳን አዘጋጅነት የተጀመረ ሲሆን ግብጽ አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ሳሙሄል ኤቶ አስራ ስምንት ጎል በማግባት የአፍሪካ ዋንጫ የምንግዜም ጎል አግቢ ነው፡፡

የ2019 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጇ ግብጽ ሰባት ግዜ በማሸነፍ የአፍሪካ ዋንጫን ብዙ ግዜ በማንሳት ቀዳሚ ነች፡፡

ምንጭ:- ቢቢሲ
🗞ቀን 14/10/2011 ዓ/ም
@tikvahethsport
Four players have been called away from #EthPL for #AFCON2019 assignment:

Ethiopia Bunna:

Shabani Hussein-🇧🇮

St. George:

Patrick Matasi- 🇰🇪

Diredawa Kenema:

Itamunua Keimuine- 🇳🇦

Adama Kenema:

Robert Odongkara- 🇺🇬

Via Firew Asrat
@tikvahethsport
#update በግብጽ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ዋንጫ ከተጀመረ 13 ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን ወደቀጣዩ ዙር ያለፉት 16 ሃገራት ተለይተው ታውቀዋል።

ከምድብ ሀ አዘጋጇ ግብጽ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎና ዩጋንዳ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በምድ ለ ደግሞ ናይጄሪያ፣ ጊኒና ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳተፈቸው ማደጋስካር አልፈዋል።

በምድብ ሐ ሴኔጋል እና አልጄሪያ፤ በምድብ መ ሞሮኮ፣ አይቮሪ ኮስትና ደቡብ አፍሪካ ምርጥ 16ቱን የተቀላቀሉ ሲሆን በምድብ ሠ ቱኒዚያና ማሊ እንዲሁም በምድብ ረ ካሜሩን፣ ጋናና ቤኒን ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በዚህም መሰረት ከመጪው አርብ ጀምሮ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ሞሮኮ ከቤኒን
ዩጋንዳ ከሴኔጋል
ግብጽ ከደቡብ አፍሪካ
ማደጋስካር ከዴሞክራቲክ ኮንጎ
ናይጄሪያ ከካሜሩን
አልጄሪያ ከጊኒ
ማሊ ከአይቮሮ ኮስት
ጋና ከቱኒዚያ የሚጠበቁ ጨዋታዎች ናቸው።

Via #bbc
@tikvahethsport
#UpdateSport መከላከያ እና ደቡብ ፖሊስ ደደቢትን ተከትለው ከፕሪሚየር ሊጉ ወርዱዋል። #FBC

@tikvahethsport
ፍራንክ ላምፓርድ የቼልሲ አሰልጣኝ ሆኖ ተሾመ
--------------------------------------------------
የቀድሞ የቼልሲው አማካይ ፍራንክ ላምፓርድ የቀድሞ ክለቡን ለማሰልጠን የሶስት ዓመታት ውል ፈርሟል።

13 ዓመታትን በቼልሲ ቤት ያሳለፈው ላምፓርድ ከክለቡ ጋር 13 ዋንጫዎችን አንስቷል።

አዲሱ የሰማያዊዮቹ አለቃ “ወደ ቀድሞ ክለቤ አሰልጣኝ ሆኜ በመመለሴ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል” ያለ ሲሆን፤ “ለክለቡ ያለኝን ፍቅር ሁሉም ይረዳዋል። አሁን ትኩረቴን በቀጣዩ የውድድር ዘመን ላይ ማድረግ ነው የምፈልገው” ሲል ላምፓርድ ተናግሯል።

ደርቢ ካውንቲን ሲያሰለጥን የነበረው ላምፓርድ ወደ ጁቬንቱስ ያመሩትን ማውሪሲዮ ሳሪን በመተካት ቼልሲን የማሰልጣን ኃላፊነትን ተረክቧል።

Via #BBC
@tikvahethsport
#UpdateSport የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ላቀረባቸው ጥያቄዎች ምላሽ እስከሚያገኝ ድረስ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮቸ ራሱን ማግለሉን አስታወቀ፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በትናንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ኮሚቴ የቅዱስ ጊዮርጊስን የሜዳ ተጠቃሚነት ለማሳጣት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ሊያደርገው የነበረን ጨዋታ በዝግ ወይም አዳማ ተጫወቱ በማለት ሁለት ጊዜ እንዲቋረጥ አድርጎል ብሏል፡፡

ይህን ጨዋታ ከዚህ በፊት የተቋረጡ የሌሎች ክለቦች ጨዋታወችን ባስተናገደበት ሁኔታ የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን አላስተናገደም ሲል በፌዴሬሽኑ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል፡፡

እንዲሁም በ29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ለፋሲል ከነማ የተሰጠው ፎርፌ አግባብነት የሌለውና አድሏዊ መሆኑንም ነው በመግለጫው ያመላከተው፡፡

አዲስ ከመጡት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ጋር በመተባበር፣ በመቻቻል እና በመተጋገዝ ለመስራት የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷልም ነው ያለው፡፡

በመሆኑም ፌዴሬሽኑ የወሰናቸውን ኢ – ፍትሃዊ እርምጃዎችን እንዲመረምር እና ያላአግባብ የተወሰነበትን ፎርፌ እንዲያነሳ የጠየቀ ሲሆን ያቀረባቸው ቅሬታዎች ምላሽ እስከሚያገኙ ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድሮች ራሱን ማግለሉን አስታውቋል፡፡

Via #fbc
@tikvahethsport