TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
" ሜሲ በፒኤስጂ በጣም ደስተኛ ነው "

የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ የበላይ ሀላፊ ናስር አል ከላይፊ የኮከባቸውን ሊዮኔል ሜሲ ኮንትራት በቀጣይ ወራት ለማራዘም እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ናስር አል ከላይፊ ሲናገሩም " ከሜሲ ጋር ከዓለም ዋንጫው በኋላ በጋራ የምናወራ ይሆናል ፣ በፒኤስጂ ቤት በመሆኑ በጣም ደስተኛ ነው በክለቡ መቆየት እንደሚፈልግ አስባለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ድል ቀንቷቸዋል !

በዱባይ ሱፐር ካፕ እየተሳተፉ የሚገኙት የአሰልጣኝ የርገን ክሎፑ ስብስብ ሊቨርፑል 4ለ1 በሆነ ውጤት የሴርያውን ክለብ ኤሲ ሚላን አሸንፈዋል።

ሞሀመድ ሳላህ ፣ ቲያጎ አልካንታራ እና ዳርዊን ኑኔዝ ( 2X ) የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ኤሲ ሚላንን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ሴልሜከርስ በመጀመሪያ አጋማሽ ማስቆጠር ችሎ ነበር።

ሊቨርፑል በዱባይ ሱፐር ካፕ የመጀመሪያ ጨዋታ በሊዮን 3ለ1 መሸነፋቸው አይዘነጋም።

ኤሲ ሚላን በጨዋታው በመለያያ ምት 4ለ3 ማሸነፍ ችለዋል።

በፕርሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስድስተኛ ላይ የሚገኙት ሊቨርፑሎች ከአስር ቀናት ቆይታ በኋላ የሊጉ ጨዋታቸውን ከ አስቶን ቪላ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫን እንደሚያሸንፉ ተስፋ አለኝ "

የፈረንሳይ ሊግን እየመሩ የሚገኙት ፒኤስጂ ፕሬዝዳንት ናስር አል ከላይፊ ዓለም ዋንጫውን " ሁለተኛ ሀገሬ " የሚሏት ፈረንሳይ እንድታሸንፍ እንደሚፈልጉ ገልፀዋል።

እንደ ፕሬዝዳንቱ ንግግር " ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫውን እንደሚያሸንፉ ተስፋ አለኝ ምክንያቱም ፒኤስጂ የፈረንሳይ ክለብ ነው ለእኔ ደግሞ ሁለተኛ ሀገሬ ነው።

አርጀንቲና ከሊዮኔል ሜሲ ጋር ጥሩ የዓለም ዋንጫን አሳልፈዋል ፣ የሚቻል ቢሆን ዓለም ዋንጫውን ለሁለቱም እሰጣለሁ " ሲሉ ናስር አል ከላይፊ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ሮናልዶ ጫማውን ቢሰቅል አይገርመኝም "

በማንችስተር ዩናይትድ ቤት የክርስቲያኖ ሮናልዶ የቡድን አጋር የነበረው ፓትሪስ ኤቬራ ከቅርብ ቀናት በፊት ከሮናልዶ ጋር በስልክ መገናኘቱን ገልጿል።

ፓትሪስ ኤቬራ ከሮናልዶ ጋር ስለነበረው ቆይታ ሲናገር " ከሮናልዶ ጋር ስለ ዓለም ዋንጫ አላወራንም ፣ ሆኖም ግን ስለ ቤተሰቡ እና ህይወቱ አውርተናል።

ስለ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እኔ ላወራ አልችልም ሆኖም ግን ጫማውን ቢሰቅል አልገረምም " ሲል ፓትሪስ ኤቭራ ተናግሯል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዋናው የዋናው አልባሳት የንግድ ምልክት ነው !

በጤና ቡድኖች እና በደጋፊዎች ተመራጭ እና ምቹ የሆኑትን ትጥቆች እንደተለመደው በተመጣጣኝ ዋጋ በመረጡት ዲዛይን እና የቀለም ምርጫ ሰርቶ ያቀርብልዎታል።

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት

ማልያችን መለያችን ዋናው ወደ ፊት. . . . .
#QatarWorldCup 🇶🇦

12:00 ክሮሽያ ከ ሞሮኮ

BET NOW ON :- https://Betika.et

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የተመደበለን ዳኛ ላይ ስጋት አለኝ "

በዛሬው ዕለት በክሮሽያ እና ሞሮኮ መካከል ለሚደረገው የደረጃ ጨዋታ ፊፋ ኳታራዊውን የመሐል ዳኛ አብድራህማን አል ጃሲም መመደቡ አሰልጣኝ ዝላትኮ ዳሊችን አላስደሰተም።

አሰልጣኙ በዛሬው ዕለት እንደተናገሩት " አብድራህማን አል ጃሲምን ለዚህ ጨዋታ መመደቡ ላይ ስጋት አለኝ ፣ በዳኛው አቅም ላይ ጥርጣሬ የለኝም ነገር ግን ከጨዋታው በኋላ ስለ ዳኝነቱ እንደማናወራ ተስፋ አለኝ " ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኳታር ምን ያህል ገቢ አገኘች ?

የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሊጠናቀቅ የአንድ ቀን እድሜ ብቻ ሲቀረው እስከ ትላንትናው ዕለት በተሰራ ጥናት ኳታር ያገኘችው ገቢ ተገልጿል።

ኳታር የዛሬ እና የነገ ጨዋታዎችን #ሳያካትት ውድድሩን በማዘጋጀቷ የተጣራ ወደ 7.5 #ቢልዮን ዶላር ማግኘቷ ተዘግቧል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ለሀገራችን ታሪክ መፃፍ እንፈልጋለን "

የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን በአምበልነት እየመራ ሁለተኛ የዓለም ዋንጫውን ለማሸነፍ የተቃረበው ሁጎ ሎሪስ ከነገው ጨዋታ በፊት አስተያየቱን ሰጥቷል።

ሎሪስ በአስተያየቱም " ለሀገራችን ፈረንሳይ ደማቅ ታሪክ መፃፍን እንፈልጋለን ፣ የነገውን ጨዋታ ለማሸነፍ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን " ሲል ከጨዋታው በፊት ተደምጧል።

ሁጎ ሎሪስ ሀገሩ የምታሸንፍ ከሆነ በዓለም ዋንጫው ታሪክ በተከታታይ ዓመት በአምበልነት ዋንጫውን ያነሳ በታሪክ የመጀመሪያው ተጫዋች ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሜሲ እንዲያሸንፍ የሚፈልጉ ፈረንሳዊያን አሉ "

የፈረንሳይን ብሔራዊ ቡድንን በአሰልጣኝነት እየመሩ ሁለተኛ የዓለም ዋንጫቸውን ለማንሳት የተቃረቡት ዲድዬ ዴሻምፕ " አርጀንቲና ብዙ ደጋፊዎች " አሏት ሲሉ ተደምጠዋል።

እንደ አሰልጣኙ አስተያየትም " አላማችን በስተመጨረሻ ዋንጫውን ማንሳት ነው ፣ አርጀንቲና በዓለማችን ላይ ብዙ ደጋፊዎች እንዳሏቸው አውቃለሁ።

ሙሉ ትኩረቴ የነገውን የዓለም ዋንጫ ማሸነፍ ብቻ ነው ፣ ፈረንሳዊያንን ጨምሮ ሊዮኔል ሜሲ ዋንጫውን ሲያነሳ መመልከት የሚፈልጉ አሉ " ሲሉ ዲድዬ ዴሻምፕ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ሊዮኔል ሜሲ ማሸነፍ ይገባዋል "

የቀድሞ የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር አጥቂ አንድሬ ፔር ጂኝያክ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ ሜሲ ማሸነፍ ይገባዋል ሲል ተናግሯል።

እንደ ተጫዋቹ አስተያየት " ፈረንሳዊ ነኝ ነገር ግን ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫን እንዲያሸንፍ እፈልጋለሁ ምክንያቱም በእግር ኳስ ህይወቱ ላበረከተው አስተዋፅኦ ይገባዋል " ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#QatarWorldCup 🇶🇦

በ 2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ በጉዳት ለሀገራቸው ፈረንሳይ ግልጋሎት መስጠት ያልቻሉ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋቾች በነገው ዕለት ኳታር እንደሚገኙ ተዘግቧል።

እንደ ሀገሪቱ የመገናኛ ብዙሀን ዘገባዎች መሰረት ፖል ፖግባ ፣ ንጎሎ ካንቴ እና ፐርስኔል ኪምፔምቤ በነገው ዕለት የሚደረገውን የፈረንሳይ እና አርጀንቲና ጨዋታ በስታዲየም እንደሚታደሙ ተገልጿል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ምባፔ አቅም ያለው እና ጠንካራ ተጫዋች ነው "

አርጀንቲናን እየመሩ በዓለም ዋንጫው ለፍፃሜው የደረሱት አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ ለኪሊያን ምባፔ ያላቸውን አድናቆት ከጨዋታ በፊት ገልፀዋል።

" እኔ እንደማስበው የነገው ጨዋታ ከግለሰቦች ይልቅ ቡድኖቹ ላይ ያተኩራል ምባፔ አቅም ያለው እና ጠንካራ ተጫዋች ነው ፣ ነገር ግን በሁለቱም ቡድኖች በኩል ጥሩ ተጫዋቾችን እንመለከታለን " ሲሉ ሊዮኔልስ ስካሎኒ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" የነገው ጨዋታ ሜሲ ከ ምባፔ አይደለም "

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሊዮኔል ስካሎኒ የነገው የፍፃሜ መርሐ ግብር የግለሰቦች ጨዋታ ብቻ እንዳልሆነ በሰጡት አስተያየት ተደምጠዋል።

ሎዮኔል ስካሎኒ ሲናገሩም " የነገው ጨዋታ አርጀንቲና ከ ፈረንሳይ እንጂ ምባፔ ከ ሜሲ አይደለም ፣ የራሳችን ጠንካራ ጎኖች አሉን እንደማስበው እንደ ቡድን የነገውን ጨዋታ ራሳችን እንወስናለን " በማለት ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የጨዋታ አሳለለፍ !

12:00 ክሮሽያ ከ ሞሮኮ

🇲🇦 Bono - Hakimi, Dari, El Yamiq, Attiat-Allah - Amrabat, El Khannouss - Ziyech, Sabiri, Boufal, En-Nesyri.

🇭🇷 Livakovic - Stanisic, Sutalo, Gvardiol, Perisic - Modric, Kovacic - Majer, Kramaric, Orsic - Livaja.

@tikvahethsport @kidusyoftahe
7 ' ክሮሽያ 1 - 0 ሞሮኮ

ግቫርዲዮል

@tikvahethsport @kidusyoftahe
9 ' ክሮሽያ 1 - 1 ሞሮኮ

ግቫርዲዮል ዳሪ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
42 ' ክሮሽያ 2 - 1 ሞሮኮ

ግቫርዲዮል ዳሪ
ኦርሲች

@tikvahethsport @kidusyoftahe