TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
#BKETHPL

በ ሁለተኛ ሳምንት ከተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች የተወሰዱ ምስሎች ከላይ ተያይዟል ።

ተጨማሪ ምስሎችን በ ኢንስታግራም :- https://www.instagram.com/p/CVkOAslo2zD/?utm_medium=copy_link መመልከት ይችላሉ ።

#Betika
#CentralHawassaHotel

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#BKETHPL

የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በሁለተኛ ሳምንት የተደረጉ ጨዋታዎችን ተከትሎ ውስን የ ዲስፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል ።

ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ #ብቸኞቹ ተቀጪ ክለቦች ሲሆን ተጫዋቾቻው አምስት የቢጫ ካርድ ማየታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል ።

በሁለተኛው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ከ ሰላሳ ስምንት ተጫዋቾች በተጨማሪም ዋና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም የቢጫ ካርድ ተመልክተዋል ።

የ ባህር ዳር ከተማው ኦሴ ማውሊ እና የ ፋሲል ከነማው ፍቃዱ ዓለሙ በ ሶስት ጎሎች የ ከፍተኛ ግብ አግቢነቱን እየመሩ ይገኛሉ ።

የ ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ ።

#CentralHawassaHotel
#Betika

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ፒኤስጂ ኮከቦቹን በጉዳት ማጣቱን ቀጥሏል !

የ ፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ ወሳኝ ተጫዋቾቹ መጎዶታቸውን ሲቀጥሉ ከጥቂት ቀናት በፊት ማርኮ ቬራቲ እና ሊዮናርዶ ፓሬዳስ መጎዳታቸው የሚታወስ ነው ።

አሁን በወጣ መረጃ ፈረንሳዊው ኮከባቸው ኪሊያን ምባፔ ባጋጠመው ጉዳት ቡድኑ ነገ ከ ሊል ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ እንደማይሰለፍ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ጆርጂና ሮድሪጌዝ !

የ አምስት ጊዜው የ ባሎን ዶር አሸናፊው ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ እና ባለቤቱ ጆርጂና ሮድሪጌዝ አዲስ ልጅ እየተጠባበቁ መሆኑ ተገልጿል ።

ጆርጂና ሮድሪጌዝ የ ሶስት ወር እርጉዝ መሆኗ ሲገለፅ ክርስቲያኖ ሮናልዶ አምስተኛ ልጁን እንደሚያገኝ ይጠበቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ስላደረክልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለው "

በባለፈው ሳምንት ለረጅም ጊዜ በ ካምፕ ኑ የሚያቆየውን ኮንትራት የፈረመው ተስፈኛው ታዳጊ ፔድሪ የ ሮናልድ ኩማንን ስንብት ተከትሎ መልዕክቱን አስተላልፏል ።

" ሁኔታዎች እኛ በምንፈልግበት መንገድ ባለመሆኑ አዝኛለሁ ፣ ስላደረገልኝ ነገር ሁሉ አመሰግናለው ።

በግልም ሆነ በሙያክ ወደ ፊት መልካሙን ሁሉ እንዲገጥምክ እመኛለሁ " በማለት ፔድሪ ለ ኩማን ያለውን መልዕክት አስተላልፏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቡናማዎቹ የገንዘብ ቅጣት ተላለፈባቸው !

የ ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ በ ሸገር ደርቢ ጨዋታ የክለቡ ደጋፊዎች የእለቱን ዳኛ አፀያፊ ስደብ ስለ መሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦበታል ።

የክለቡ ደጋፊዎች ለፈፀሙት ጥፋት ክለቡ ሀምሳ ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መቀጣታቸውን ለማወቅ ተችሏል ።

#CentralHawassaHotel
#Betika

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሻኛ ከዳቢት ... ታላቅ ከታናሽ ... ለማወራረድ ተዘጋጅተዋል? ቅዳሜ እና እሑድን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ድራፍት ጋር በኢግዚቢሽን ማዕከል!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎችን በዲኤስቲቪ ሱፐር ስፖርት ቻናሎች ከቤትዎ በቀጥታ ይከታተሉ!

አንድም ጨዋታ አንድም ጎል አያምልጥዎ!🔥🔥

አዲስ ዲኮደር በ 699 ብር ሲገዙ የ 1 ወር ነፃ የሜዳ ፓኬጅ ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!

https://bit.ly/2WDuBLk

የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ!

https://bit.ly/3D2O1t4

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #DStvየራሳችን #EthiopianPremierLeague
TIKVAH-SPORT
#BKETHPL የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በሁለተኛ ሳምንት የተደረጉ ጨዋታዎችን ተከትሎ ውስን የ ዲስፕሊን ውሳኔዎች ተላልፈዋል ። ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ #ብቸኞቹ ተቀጪ ክለቦች ሲሆን ተጫዋቾቻው አምስት የቢጫ ካርድ ማየታቸውን ተከትሎ የ 5,000 ብር ቅጣት ተላልፎባቸዋል ። በሁለተኛው ሳምንት በተደረጉ ጨዋታዎች ከ ሰላሳ ስምንት ተጫዋቾች በተጨማሪም ዋና አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነ ማርያም…
ሲዳማ ቡና ቅጣት ተላለፈበት !

ከ ሁለተኛው የውድድር ሳምንት ጀምሮ የኮቪድ ምርመራ በአክሲዮን ማህበሩ አስተባባሪነት በአንድ የምርመራ ማዕከል ብቻ እንዲያደርጉ የተወሰነውን አቅጣጫ በመጣሳቸው ሲዳማ ቡናዎች ቅጣት ተላልፎባቸዋል ።

ይህም የክለቡ ድርጊት ፍትሃዊ አሰራር እንዳይሰፍን ከማድረጉ በተጨማሪ በክለቦች መካከል በ ክለቦች እና በአክሲዮን ማህበሩ መካከል የነበረውን መተማመን እንዲሸርሸር ማድረጉ በውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ታምኖበታል።

በመሆኑም ክለቡ ለፈጸመው ጥፋት በኢትዮጵያ እግር ኳስ የዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት ሀያ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጡ ውሳኔ ተላልፎባቸዋል ።

#CentralHawassaHotel
#Betika

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" በ አል ሳድ ስራዬ ላይ አተኩሬያለው "

የ ሮናልድ ኩማንን ስንብት ተከትሎ ዳግም ስሙ ከ ባርሴሎና ጋር የተያያዘው ዣቪ ሀርናንዴዝ " በ አል ሳድ ስራዬ ላይ አተኩሬያለው " ሲል ተደምጧል ።

ዣቪ በሰጠው አስተያየት " በአሁን ጊዜ በ አል ሳድ ቤት ባለብኝ ስራዬ ላይ አተኩሬያለሁ ፣ ስለ ሌላ ነገር ማውራት አልችልም " ሲል በወቅታዊ ጉዳይ ላይ አስተያየቱን ሰጥቷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
Samsung Galaxy A71
Storage: 128 GB
Camera: 64+12+5+5 MP
Battery: 4500 mAh
RAM: 8 GB
Price : 19,500 Birr

Contact US
0925927457
0953964175 @heymobile
0910695100
@HEYOnlinemarket
አስደሳች ዜና ለየቅርጫት ኳስ አፍቃሪያን በሙሉ!የእርስዎ ተወዳጅ የNBA ቡድን አዳዲስ ማሊያዎችን ከNዋM sportswear ይዘዙ ።

CALLING ALL BASKETBALL LOVERS!🏀🗑 Get the lastest jersey of your favorite NBA team from NWAM SPORTSWEAR🔥

Get ready to HOOP!

ለተጨማሪ መረጃ : @NwaMsport 0911912441 or 0911535658 ለማዘዝ : @bilu14 @Order_NwaM
#BKETHPL

ሶስተኛ ሳምንት የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ በዛሬው ዕለት በ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም መካሄዱን ይጀምራል ።

9:00 ሀዋሳ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና

12:00 አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ዲቻ

#CentralHawassaHotel
#Betika / https://www.betika.com

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#CECAFA

የ ኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ሴት ብሄራዊ ቡድናችን የሚሳተፍበት የ ሴካፋ ውድድር በነገው ዕለት በ ዩጋንዳ መካሄዱን ይጀምራል ።

የ ኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች የ ሴት ብሔራዊ ቡድናችን በመክፈቻው ዕለት ከ ጅቡቲ ጋር ከ ቀኑ 7:30 ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል ።

ብሔራዊ ቡድናችን የሚሳተፍበት ሙሉ የ ጨዋታ መርሐ ግብር በምስሉ ላይ ተያይዟል ።

#CentralHawassaHotel
#Betika

@tikvahethsport @kidusyoftahe