TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
TIKVAH-SPORT
Photo
ለ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሽኝት ተደረገ !

በ ሴቶች የ አፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ የሆነው የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ ውድድሩ ወደ ሚካሄድበት ኬንያ ከ ማቅናታቸው አስቀድሞ የ ሽኝት መርሀ ግብር ተካሂዷል ።

በ ዋቢ ሸበሌ በተደረገው የ ሽኝት መርሐ ግብር የ ኢትዮጵያ ደጋፊዎች ማህበር በ ስፍራው በመገኘት ሸኝተዋል ።

የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነገ ረፋድ ላይ ወደ ኬንያ እንደሚያቀኑ ይጠበቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በልዩነት የሚደምቅ አንድነት!
ከ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር እሁድ የ ወዳጅነት ጨዋታ የሚያደርገው የ ዩጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ባሕር ዳር መድረሱን የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስነብቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ !

የ 2021 / 22 የ ውድድር ዓመት የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ እጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ ከ ምሽቱ 1:00 ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል ።

ቡድኖች በ አራት ቋት ሲደለደሉ ሙሉ ዝርዝሩ በምስሉ ላይ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዩፋ የ አመቱ ምርጥ ተጫዋች ማን ይሆናል ?
public poll

ንጎሎ ካንቴ – 2K
👍👍👍👍👍👍👍 71%

ጆርጂንሆ – 519
👍👍 17%

ኬቨን ዴ ብሮይነ – 389
👍 12%

👥 3123 people voted so far.
የ ዩፋ የ አመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?
anonymous poll

ቶማስ ቱሄል – 1K
👍👍👍👍👍👍👍 68%

ሮቤርቶ ማንሲኒ – 477
👍👍 22%

ፔፕ ጋርድዮላ – 238
👍 11%

👥 2204 people voted so far. Poll closed.
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከ ሴራሊዮን ብሔራዊ ቡድን በሚያደርገው ጨዋታ ሚጠቀመው የቋሚ 11 አሰላለፍ

ግብ ጠባቂ
ተክለማሪያም ሻንቆ

ተከላካዮች
ሱሌማን ሀሚድ
አስቻለው ታመነ
ያሬድ ባዬ
ረመዳን የሱፍ

አማካዮች
ታፈሰ ሰለሞን
ሱራፌል ዳኛቸው
ይሁን እንደሻው
መሱድ መሀመድ
ሽመክት ጉግሳ

አጥቂ
አማኑኤል ገ/ሚካኤል

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ሞት ምድብ ?

የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የ ምድብ ድልድል ዛሬ ምሽት ሲካሄድ ታላላቅ ክለቦች በ አንድ ምድብ የ መገናኘት እድል ይኖራቸዋል ።

ለ አብነት ያክል :-

ምድብ አንድ :- ባየር ሙኒክ ፣ ፒኤስጂ ፣ ፖርቶ እና ኤሲ ሚላን

ምድብ ሁለት :- ማንችስተር ሲቲ ፣ ባርሴሎና ፣ አያክስ እና ቤሽኪታሽ

ምድብ ሶስት :- ቼልሲ ፣ ሪያል ማድሪድ ፣ ቤንፊካ እና ክለብ ብሩጅ ከ ሞት ምድቦች መካከል ናቸው ተብሎ ይጠበቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሎዛ አበራ
" ለ እንቁጣጣሽ ጥሩ ስጦታ ይዘን እንመጣለን " ሎዛ አበራ

የ ሉሲዎቹ እና የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ ፊት መስመር አጥቂ ሎዛ አበራ ሌላ ደማቅ ታሪክ ለመፃፍ ተቃርባ ትገኛለች ።

በ አፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ለመሳተፍ ኬንያ ያቀናው የ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብ በ ውድድሩ የተሻለ ውጤትን እንደሚያመጣ ሎዛ ጠቁሟለች ።

" ለ ደጋፊዎቻችን ለ እንቁጣጣሽ ጥሩ ስጦታ ይዘንላችሁ እንመጣለን ብዬ አስባለው " ስትልም በ አስተያያቷ ተናግራለች ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን !

በ አሰልጣኝ ጋሪዝ ሳውዝጌት የሚመሩት እንግሊዞች ከ ፊታቸው ላለባቸው የ አለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች የ ቡድን ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ 0 - 0 ሴራሊዮን

* የ አቋም መፈተሻ ጨዋታ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ሕዝብ አንፈልግሽም ልቀቂ ካለኝ ስልጣኔን በደስታ እለቃለሁ "

ኮማንደር ደራርቱ ዛሬ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ “ሕዝብ አንፈልግሽም ልቀቂ ካለኝ ስልጣኔን በደስታ እለቃለሁ” ብላለች ፡፡

ከ ሰሞኑ የ ኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ለ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ተጠይቆ የነበረው “ኃላፊነትዎን ይለቃሉ ወይ?” የሚል ጥያቄ ለ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉም ቀርቦ ነበር ፡፡

የ ኢትዮጵያ ህዝብ በ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ኃላፊነት እንድቀጥል ካልፈለገ ለመልቀቅ ዝግጁ መሆኗን የ ኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ መናገሯን #AlAin አስነብቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ተወዳጁን የ ቤልጅየም ግራንድ ፕሪ - የ ሞተር ስፖርት ውድድር

ቅዳሜ ነሐሴ 22 እና እሁድ ነሐሴ 23 በ ዲኤስቲቪ SS Motorsport Channel no. 235 ይመልከቱ!!

#UnmatchedEntertainment

የዲኤስቲቪን ቤተሰብ ይቀላቀሉ!

https://bit.ly/3D2O1t4
ማንችስተር ሲቲ ተጫዋቹን አገደ !

የ ፕርሚየር ሊጉ ክለብ ማንችስተር ሲቲ በ ፖሊስ መከሰሱ የተገለፀውን ቤንጃሚን ሜንዲ ማገዱን አሳውቋል ።

ሲቲዎች ለ ህጋዊ ሂደት ተገዢ መሆናቸውን ገልፀው ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ክለቡ ተጨማሪ አስተያየት ከመስጠት እንደሚቆጠቡ አሳውቀዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ማንችስተር ሲቲ ?

የ ፕርሚየር ሊጉ አሸናፊዎች ማንችስተር ሲቲ ከ ሮናልዶ ወኪል ጋር ተጫዋቹን ለ ማዘዋወር ንግግር መጀመራቸው ይፋ ሆኗል ።

የ ሮናልዶ ወኪል ሆርጌ ሜንዴዝ ዛሬ ጠዋት ከ ጁቬንቱስ ክለብ ሀላፊዎች ጋር ሲነጋገሩ በ ተጫዋቹ ቀጣይነት ላይ መክረዋል ።

በ ሮናልዶ እና ጁቬንቱስ መካከል ክለቡን እንዲለቅ እስከ አሁን ከ ስምምነት አልተደረሰም ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አሸነፈች !

ትላንት ምሽት በ ስዊዘርላንድ ሉዛን በተደረገው የ ዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ በ 1,500 ሜትር ውድድር ስታሸንፍ በ ሌሎች ውድድሮች የተሳተፉ የ ሃገራችን አትሌቶች መልካም ውጤት አስመዝግበዋል

በ ውጤቱም :-

በ 3,000 ሜትር ወንዶች

2ኛ በሪሁ አረጋዊ በ7:33.39
5ኛ ሰለሞን ባረጋ በ7:37.62
6ኛ ሙክታር ኢድሪስ በ7:40.30
ጌትነት ዋለ ውድድሩን አላጠናቀቀም

በ ሴቶች 1,500 ሜትር
1ኛ ፍሬወይኒ ኃይሉ በ4:02.24
6ኛ ሂሩት መሸሻ በ4:05.28

#EAF

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ስንብት !

ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ ኮንቲናሳ ( የ ጁቬንቱስ የ ልምምድ ማዕከል ) መድረሱ ተገልጿል ።

ሮናልዶ በ ልምምድ ማዕከል የ ቡድን አጋሮቹን ሊሰናበት መሆን ሲነገር የ ጁቬንቱስ ቀጣይነቱ ሊገታ መቃረቡ ተዘግቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የ ዩሮፓ ሊጉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ማነው ? ቪያሪያልን አሸናፊ አድርጎ የተገባደደው የ ተጠናቀቀው የ ውድድር ዓመት ዩሮፓ ሊግ የ አመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩዎች ይፋ ተደርገዋል ። ይህንንም ተከትሎ በ አመቱ ምርጥ ተጫዋችነት ብሩኖ ፈርናንዴዝ ፣ ኤዲሰን ካቫኒ እና ጄራርድ ሞሬኖ መመረጣቸው ተገልጿል ። @tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዩሮፓ ሊግ የ አመቱ ምርጥ ተጫዋች !

የ አዲሱ የ ውድድር ዓመት የ ዩሮፓ ሊግ የ ምድብ ድልድል ከ ደቂቃዎች በኋላ ይፋ ሲደረግ የ አመቱ ምርጥ ተጫዋች ታውቋል ።

የ ዩሮፓ ሊጉ አሸናፊ ቪያሪያል የ ፊት መስመር ተጫዋች ጄራርድ ሞሬኖ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና ኤዲሰን ካቫኒን በ መብለጥ አሸናፊ መሆኑ ይፋ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዩሮፓ ሊግ የ ምድብ ድልድል ይፋ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe