TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ከ 20 ዓመት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን !

ከጥቂት ቀናት በኋላ በ ታንዛኒያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው ከ 20 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድር ኢትዮጵያ በምድብ ሶስት ከ ሱዳን እና ኬንያ ጋር መደልደሏ ይታወሳል ።

ይህንንም ተከትሎ ሴካፋ የውድድሩን የመርሐ ግብር ቀናቶች ይፋ ሲያደርግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የቡድን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከ ሰባት ቀናት በኋላ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ።

ይህንንም ተከትሎ :-

ህዳር 14 :- ኢትዮጵያ ከ ኬንያ

ህዳር 16 :- ኢትዮጵያ ከ ሱዳን ጋር የሚጫወቱ ይሆናል ።

[ በ @Hatricksport የቀረበ ]

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ የነገ ጨዋታ የቴሌቪዥን ሽፋን ያገኝ ይሆን ?

የዋልያዎቹን ሁለት የወዳጅነት ጨዋታ በቀጥታ ስርጭት ሽፋን በአዲስ ቴሌቪዥን ፣ በ ኤፍ ኤም 96.3 እና በ ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾች ሲያስተላልፍ የነበረው አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የነገውንም ጨዋታ ለማሰራጨት በጥረት ላይ ናቸው ።

የካፍ ውድድሮችን የስርጭት መብት ባለቤት ከሆነው የፈረንሳዩ ካናል ፕሉስ ጋር ጨዋታው በቀጥታ ስርጭት ለ ኢትዮጵያዊያን በሚደርስበት መንገድ ላይ ፌደሬሽኑ ድርድር እያደረገ ስለመሆኑ ከታማኝ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ችለናል።

የተጀመረው ንግግር በስኬት የሚጠናቀቅ ከሆነ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረገውን ጨዋታ አዲስ ሚዲያ ኔትወርክ እንደ ከዚህ ቀደሞቹ ጊዜያት በሁሉም የስርጭት አማራጮቹ ጨዋታውን ወደ አድማጭ ተመልካች ያስተላልፋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ፓል ስኮልስ ዛሬ 46ኛ የልደት በዓሉን እያከበረ ይገኛል። እኛም ስኮልስ ካስቆጠራቸው ግቦች መካከል ድንቅ ድንቁን ጋበዝናቹ።

@tikvahethsport    @GoitomH
ኬቨን ዴ ብሩን እና ማንችስተር ሲቲ !

ቤልጅዬማዊው ኮከብ የማንንችስተር ሲቲ የአማካይ ተጫዋች ኬቨን ዴ ብሩን በ ኢቲሀድ ስታዲየም የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት ለመፈራረም ከ ክለቡ ጋር በመነጋገር ላይ እንደሆነ አሳውቋል ።

ኬቨን ዴ ብሩን አያይዞም በማንችስተር ሲቲ ለረጅም ጊዜያት መቆየትን እንደሚፈልግ ገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኔይማር እና ጉዳቱ

በጉዳት ምክንያት ከብራዚል ብሄራዊ ቡድን ውጪ የተደረገው ኔይማር ከጉዳቱ እያገገመ መሆኑን እና በመጪው አርብ ክለቡ ፒኤስጂ ከ ሞናኮ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ላይ ሊሰለፍ እንደሚችል ላ ፓሪዚያን ዘግቧል።

@tikvahethsport    @GoitomH
#LIVE

"ውጤቱን እንደሰማችሁት በኒጀር 1 ለ 0 ተሸንፈናል ተጨዋቾቼ ባመንበትና በተዘጋጀንበት ለመሄድ ሞክረዋል ።

ቁጥሮች ይህን ያሳያሉ ነጥብ ባለማግኘታችን ተከፍተናል በነበረን አጠር ያለ ዝግጅት ባየነው ዕድገት ያለው አቋም አሳይተናል ።

ለነገው ጨዋታ ሪከቨር እንዲያደርጉና የስነልቦና አቅማቸውን ለመፍጠር እየሰራን ነው ያለው ይሄ ነው" ሲሉ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ አስተያየታቸውን ለጋዜጠኞች ሰጥተዋል ።

[ በዮሴፍ ከፈለኝ የቀረበ ]

@tikvahethsport @kidusyoftahe
20 ጋዜጠኞች 50 የቪ አይ ፒ ሰዎች እንዲገቡ ብቻ ካፍ በድጋሚ በተደረገ ጥረት መፈቀዱን አቶ ባህሩ ጥላሁን አሳውቀዋል ።

[ ዮሴፍ ከፈለኝ ]

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የዋልያዎቹ የነገው ጨዋታ የቴሌቪዥን ስርጭት ውሳኔ አገኘ !

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በነገው ዕለት የ ኒጀር አቻቸውን ሲገጥሙ ጨዋታውን አዲስ ቲቪ እንደ ቀደመው ጊዜ ጨዋታውን ለማስተላለፍ ጥያቄ አቅርቦ የነበረ ቢሆንም ጥያቄው ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል ፡፡

ይህንንም ተከትሎ ጨዋታው እስከ አሁን ባለው መረጃ የቀጥታ ሽፋን የማያገኝ ይሆናል ፡፡

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የራሞስ መግለጫ ተሰረዘ

በማድሪድ ስላለው ቆይታ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ሰርጂዮ ራሞስ መግለጫውን መሰረዙን ላ ሮሀ ዘግቧል።

@tikvahethsport    @GoitomH
ቶተንሀም ተጫዋቹ በቫይረሱ መያዙ ተገለፀ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የመስመር ተጫዋቹ ማት ዶሀርቲ በኮሮና ቫይረስ መያዙን አሳውቀዋል ።

ማት ዶሀርቲ በቫይረሱ መያዙን ተከትሎ በመጪው ቅዳሜ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር በሚደረገው የፕርሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሚያመልጠው ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አልጄርያ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች !

የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤቷ አልጄርያ ከደቂቃዎች በፊት ከ ዚምቧቡዌ ጋር ሁለት አቻ መለያየታቸውን ተከትሎ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን በመከተል ለ 2022 የአፍሪካ ዋንጫ ማለፍ ችለዋል ።

በ ጀማል ቤልማዲ አሰልጣኝነት እንዲሁም ሪያድ ማህሬዝ አምበልነት የሚመራው የአልጄርያ ብሔራዊ ቡድን ተከታታይ 22 ጨዋታዎች ሳይሸነፉ መጓዝ ችለዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የአፍሪካ ዋንጫ መረጃዎች !

- የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬም ቀጥለው ሲካሄዱ ደቡብ ሱዳን ዩጋንዳን በማሸነፍ ተስፋዋን አለምልማለች ።

- ሳኦ ቶሜ እና ስዋቲኒ ( ስዋዚላንድ ) የምድባቸውን ጨዋታ ማሸነፍ ሲሳናቸው ከወዲሁ አለማለፋቸውን አረጋግጠዋል ።

- ኢትዮጵያዊያኑ የመሐል ዳኞች ቴዎድሮስ ምትኩ እና ፋሲል ዮሐላሸት በተጠባባቂ ዳኝነት እንዲሁም በሁለተኛ ረዳት ዳኛነት የሞዛምቢክ እና ካሜሮን ጨዋታን እንደሚመሩ ይጠበቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋይኒ ሩኒ አሰልጣኝ ሆኗል

እንግሊዛዊው ዋይኒ ሩኒ ደርቢ ካውንቲ በቀጣይ የሚያደርጋቸውን ሶስት ጨዋታዎችን ከሌሎች የጊዚያው አሰልጣኞች ቡድን ጋር በመሆን ቡድኑን በአሰልጣኝነት የሚመራ ይሆናል።

@tikvahethsport    @GoitomH
-የማንችስተር ዩናይትዱ አሌክስ ቴላስ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ተረጋግጧል።

@tikvahethsport    @GoitomH
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቼልሲ የወሩን ምርጥ ጎል አሳወቀ !

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ የወርሀ ጥቅምት ምርጥ ጎል ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጓል ።

ይህንንም ተከትሎ ቲሞ ቨርነር በ ሳውዝሀምፕተን ላይ ያስቆጠራት የሊጉ የመጀመሪያ ጎሉ የክለቡ የወሩ ምርጥ ጎል በመባል ተመርጣለች ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሸገር ደርቢ በአዲስ አበባ የመታየት ዕድሉ ጠቧል !

የመጀመርያ አምስት ሳምንታት አርባ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲካሄድ የሸገር ደርቢ የለም ።

ከስድስተኛ ሳምንት ጀምሮ እስከ አስረኛ ሳምንታት ድረስ የሚካሄዱ አርባ ጨዋታዎች ጅማ ላይ ሲካሄድ የሸገር ደርቢ በስድስተኛው ጨዋታ ላይ ይከሰታል፡፡

ይህም ጨዋታው ጅማ ላይ የሚካሄድ ሲሆን በሁለተኛ ዙርም ጨዋታው የሚካሄደው ከ መቐለ ፣ ድሬዳዋ እና ሀዋሳ ስታዲየሞች በአንዱ የሚካሄድ መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡

ይህም የሸገር ደርቢን የአዲስ አበባ ታዳሚ እንደማያየው እና በአጠቃላይ ሁለቱም የሸገር ደርቢ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ አለመካሄዱን የተረጋገጠ ሆኗል ።

[ በዮሴፍ ከፈለኝ የቀረበ ]

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሴናል ተጫዋቹ በኮሮና ቫይረስ ተያዘ !

በዘንድሮው የውድድር ዓመት በመድፈኞቹ ቤት ብቃታቸውን እያሳዩ ከሚገኙ ተጫዋቾች ቀዳሚው የሆነው ሞሐመድ ኤል ኔኒ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ይፋ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ !

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተጫዋቾች እና የክለብ አባላት ከ ጥቅምት ሰላሳ እስከ ህዳር ስድስት ለ 1,207 ሰዎች ባደረጉት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አስራ ስድስት ሰዎች መያዛቸውን ይፋ ሆኗል ።

ይህም ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበት እንደሆነ በመረጃው ይፋ ተደርጓል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሉዊዝ ሱዋሬዝ በቫይረሱ ተይዟል !

ዩራጋዊው የአትሌቲኮ ማድሪድ የፊት መስመር አጥቂ ሉዊስ ሱዋሬዝ በኮሮና ቫይረስ መያዙን የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል ።

ይህንንም ተከትሎ ሱዋሬዝ በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ ከ ቀድሞ ክለቡ ባርሴሎና ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe