TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia

ዛሬ ፓሪስ ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት ሦስት የፍጻሜ ውድድሮች ይደረጋሉ።

አሁን 3:00 ለይ የወንዶች የማራቶን ውድድር የሚካሄድ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ፦

🇪🇹 በአንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ
🇪🇹 በአትሌት ዴሬሳ ገለታ
🇪🇹 በአትሌት ታምራት ቶላ ትወከላለች።

ምሽት 2:50 የወንዶች 5000 ሜትር ፍፃሜ የሚካሄድ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ ፦

🇪🇹 በአትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት
🇪🇹 በአትሌት አዲሱ ይሁኔ
🇪🇹 በአትሌት ቢኒያም መሀሪ ትወከላለች።

ምሽት 3:15 የሴቶች 1500 ሜትር ፍፃሜ ይደረጋል ፤ በዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ
🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 በአትሌት ድርቤ ወልተጂ ትወከላለች።

@tikvahethiopia @tikvahethsport
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia : የሴቶች ማራቶን ሊጠናቀቅ 5 ኪሎሜትር ይቀረዋል።

ከባድ ፉክክር ነው ያለው።

5 አትሌቶች ሌሎቹን ቆርጠዋቸዋል።

ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ትዕግስት አሰፋ እና አማኔ በራሶ ከፊት መስመር ይገኛሉ።

2 የኬንያ አትሌቶች እና የኔዘርላንዷ ሲፋን ሀሰን አብረው እየተከተሏቸው ነው።

ይቀናን🙏
@tikvahethiopia
#Ethiopia

በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚካሄደው የዘንድሮው የሴካፋ ሀገራት የካፍ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ማጣሪያ ውድድር የፊታችን ቅዳሜ ይጀመራል።

ውድድሩን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ከውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

የአፍሪካ እግርኳስ የበላይ ካፍ ለውድድሩ የሚሆን 219,000 ዶላር ድጋፍ ማድረጉን በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።

ውድድሩ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንደሚያገኝ ተያይዞ የተገለፀ ሲሆን ጨዋታዎቹን በአካል ለመመልከት መግቢያ በነፃ መሆኑም ተነግሯል።

በውድድሩ ሁለት ዋና ዳኞች እና ሁለት ረዳት ዳኞች እንዲመሩ ከኢትዮጵያ መመደባቸው ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

በፔሩ ሊማ እየተደረገ በሚገኘው የአለም ከ 20ዓመት በታች የአለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ወርቋን አግኝታለች።

አትሌት መዲና ኢሳ የውድድሩን የሻምፒዮና ሪከርድ በመስበር ለሀገሯ በ 5000ሜ ወርቅ አስገኝታለች።

አትሌት መዲና ከሁለት አመት በፊት በተደረገው የአለም አትሌቲክ ሻምፒዮና ላይ ማሸነፏ አይዘነጋም።

“ ከኦሎምፒክ ማግስት ሪከርድ በመስበር የአለም ሻምፒዮና ባለቤት በመሆኔ ተደስቻለሁ “ መዲና ኢሳ ከድሏ በኋላ ተናግራለች።

አትሌት መቅደስ አለምሸት በርቀቱ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ሌሊት በተደረገ ሌላ ውድድር በ 5000ሜ ወንዶች አትሌት አብዲሳ ፈይሳ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

በወቅታዊ የሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ኢትዮጵያ :-

- አንድ ወርቅ እና ሁለት ብር በማግኘት ከአለም አንደኛ ደረጃን በመያዝ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመራች ትገኛለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

በፔሩ ሊማ እየተካሄደ በሚገኘው ከ 20ዓመት በታች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ መሪነቷን አስጠብቃለት።

ሌሊት በተደረገ የ 3000ሜ መሰናክል ሲምቦ አለማየሁ የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ለሀገሯ አስገኝታለች።

ውድድሩ አርብ ( ዛሬ ) ሌሊት ሲቀጥል 10,000ሜ ሴቶች ፣ 800 ወንድ እና ሴት እንዲሁም 3000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በሁለት ወርቅ እና ሁለት ብር የሜዳሊያ ሰንጠረዡን ከአለም በመምራት ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

በሀገሩ ፔሩ ሊማ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው ከ 20ዓመት በታች የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ #አራተኛዋን ወርቅ አግኝታለች።

በ ሴቶች 3000 ሜትር የፍፃሜ ውድድር :-

- አትሌት አለሽኝ ባወቀ የወርቅ ሜዳልያ እንዲሁም

- አትሌት ማርታ አለማየሁ የነሀስ ሜዳልያ አሸናፊ ሆነዋል።

አትሌት ማርታ አለማየሁ ነሐስ ሜዳሊያ ስታገኝ ከቀናት በፊት በውድድሩ በ 3000ሜ መሰናክል ሪከርድ በመስበር ያሸነፈችው ሲምቦ አለማየሁ እህት ነች።

በወንዶች የ 800ሜ ወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን ወርቅ ስታገኝ አትሌት ጀነራል ብርሀኑ በቀዳሚነት ውድድሩን አጠናቋል።

ከአሜሪካ እኩል በሻምፒዮናው አራት ወርቅ ያላት ሀገራችን ኢትዮጵያ በብር ሜዳሊያ ተበልጣ ከአለም 2️⃣ኛ ላይ ትገኛለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አሁንም ብዙዎች የቤት ባለቤት ሊሆኑ ነው!
ሰስተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ ተጀመረ!
👉በርካታ የቤት አማራጮች
👉ከባለሙያዎች ምክር የሚያገኙበት
👉ከሪል ስቴት ገንቢዎች እና ኤጀንሲዎች ጋር የፖናል ውይይት የሚያረጉበት
👉ለግንባታዎ የሚያስፈልጉዎትን ቁሳቁሶች በቀጥታ ከአቅራቢዎች የሚያገኙበት 

ታላቅ እድል!
ከነሐሴ 24፣ 25 እና 26 በስካይ ላይት ሆቴል እንጠብቅዎታለን!

ለበለጠ መረጃ ወደ 0994373737 ወይም 0923799133 ይደውሉ!

 🌻 በአዲስ አመት አዲስ ቤት🌻

#realstateagent #Ethiopia #realtors #adissabeba #arki #realstates #expo #ethiopia #realstate #ethiopian #addisababaethiopia #addisababa🇪🇹 #buyhome #realestateinvesting101 #events #realestateagent #realestate
#Ethiopia 🇪🇹

በፔሩ ሊማ ሲካሄድ የቆየው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሌሊቱን ፍፃሜውን አግኝቷል።

በመጨረሻው ቀን ውሎ በ 1500 ሜትር አትሌት አብዲሳ ፈይሳ 3:40.51 በመሮጥ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ ታሪክ በዚህ ርቀት ወርቅ ስታገኝ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በሊማ የአለም አትሌቲክስ በ 5000ሜ የብር ሜዳሊያ ማግኘቱ ይታወቃል።

በ1500 ሜትር ሴቶች ሳሮን በርሄ 4:16.64 በሆነ ጊዜ ወርቅ ስታገኝ በ3000 ሜትር መሰናክል ሀይሉ አያሌው የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆኗል።

ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ:-

6️⃣ ወርቅ፣
2️⃣ ብር እና
2️⃣ የነሀስ ሜዳሊያ በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ ከአፍሪካ ደግሞ አንደኛ በመሆን አጠናቃለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የ 2016ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ የኮከቦች ሽልማት በድሬዳዋ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

የሊጉ ክለቦች ከቀጥታ ስርጭት የሚያገኙትን ክፍያ ሲቀበሉ በሻምፒዮኑ ንግድ ባንክ እና ወራጁ ሀምበሪቾ መካከል የ 10ሚልዮን ብር ልዩነት መኖሩ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ :-

1ኛ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 18,372,924 ብር
2ኛ መቻል - 17,190,949 ብር
3ኛ ኢትዮጵያ ቡና - 16,068,481 ብር

4ኛ ባህርዳር ከተማ - 15,059,520 ብር
5ኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ - 14,110,065 ብር
6ኛ ፋሲል ከተማ - 13,238,116 ብር
7ኛ አዳማ ከተማ 12,443,674 ብር

8ኛ ሀድያ ሆሳዕና - 11,726,739 ብር
9ኛ ሀዋሳ ከተማ - 11,887,310 ብር

10ኛ ኢትዮጵያ መድን - 10,525,387 ብር
11ኛ ሲዳማ ቡና - 10,040,971 ብር

12ኛ ድሬዳዋ ከተማ - 9,634,062 ብር
13ኛ ወላይታ ድቻ - 9,316,159 ብር
14ኛ ወልቂጤ ከተማ - 9,052,763 ብር

15ኛ ሻሸመኔ ከተማ - 8,878,373 ብር
16ኛ ሀምበሪቾ ዱራሜ - 8,781,490 ብር ገቢ ማግኘት ችለዋል።

ይህ ገቢ ክለቦቹ ከቴሌቪዥን መብት ሽያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ገቢዎች ተቀንሶ ለክለቦች የሚደርስ ክፍያ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ( 2016ዓ.ም ) የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ የአመቱ ኮከቦች ሽልማት በድሬዳዋ ተካሂዷል።

የሊጉ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአመቱ የኮከቦች ሽልማት በሶስት ዘርፎች አሸናፊ መሆን ችለዋል።

በዚህም መሰረት :-

➡️ የአመቱ ኮከብ ተጫዋች - ባሲሩ ኡመር

- ጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጫዋች ባሲሩ ኡመር በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ታሪክ የአመቱ ኮከብ ሽልማትን ያሸነፍ የውጭ ሀገር ተጫዋች ሆኗል።

- ባሲሩ ኡመር 210,000 ብር ተሸላሚ መሆን ችሏል።

➡️ የአመቱ ተስፈኛ (ወጣት) ተጫዋች - ቢንያም አይተን

- ቢንያም አይተን የ 105,000 ብር ተሸላሚ ሆኗል።

- አዳማ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በዚህ የሽልማት ዘርፍ ለተከታታይ አመት ተጫዋች ማስመረጥ ችለዋል።

➡️ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ - አሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ

- አሰልጣኝ በፀሎት ልዑል ሰገድ የ 200,000ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

➡️ የአመቱ ኮከብ ግብ አስቆጣሪ - አሊ ሱሌማን ( ሀያ ጎል )

- ኤርትራዊው የሀዋሳ ከተማ አጥቂ አሊ ሱሌማን የ 200,000ሺህ ብር ተሸላሚ ሆኗል።

➡️ የአመቱ ኮከብ ግብ ጠባቂ - ፍሬው ጌታሁን

- ፍሬው ጌታሁን 150,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶለታል።

➡️ የአመቱ ምርጥ ምስጉን ረዳት ዳኛ - ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ፋሲካ ዮኋላሸት

- ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ፋሲካ የኋላሸት የ 105,000 ብር ተሸላሚ ሆነዋል።

➡️ የአመቱ ምርጥ ኮከብ ዋና ዳኛ - ኢንተርናሽናል ባምላክ ተሰማ

- ኢንተርናሽናል ባምላክ ተሰማ 105,000 ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከደቂቃዎች በኋላ ከዩጋንዳ ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ ቋሚ አሰላለፍ ታውቋል።

ግብ ጠባቂ

- አብዮ ካሳዬ ( አምበል )

ተከላካይ

- ደግፌ አለሙ ፣ ግሩም ሀጎስ ፣ ዋንጫ ቱት እና አብዱሰላም የሱፍ

አማካይ

- ይታገሱ ታሪኩ ፣ ሚኪያስ ፀጋዬ እና ሰለሞን ገመቹ

አጥቂ

ዳገም አወቀ ፣ አንተነህ ተፈራ እና ናትናኤል ሰለሞን በመሆን ወደ ሜዳ የሚገቡ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

የ 2017 ሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪ.ሜ. ሩጫ በአለም አትሌቲክስ የውድድር ደረጃዎች ውስጥ ተካተተ።

የአለም አትሌቲክስ ውድድሩን የሌብል ደረጃ ያለው የጎዳና ላይ ውድድር ( Label Road Race ) ሲል ዕውቅና እንደሰጠው ተገልጿል።

የአለም አትሌቲክስ የሌብል ደረጃ የሰጣቸው ውድድሮች

- በጥራት ዝግጅቶችን ከማድረግ

- ደህንነታቸው የተጠበቀ ከመሆን

- የተሳታፊዎች ውድድሩ ላይ የነበራቸው ቆይታ

- የከተማ አስተዳደሮች ለዝግጅቱ ያላቸውን ድጋፍ

- ዝግጅቱ በአትሌቲክስ ውድድር ዘርፍ አበረታች መድኃኒት ላይ ለመስራት ያለውን ቁርጠኝነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መሆኑ ተገልጿል።

የሌብል ደረጃ የአለም አትሌቲክስ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድሮችን ካስቀመጠባቸው አራት ደረጃዎች የኢሊት ፣ የወርቅ እና የፕላቲንየም ደረጃዎች መካከል አንዱ ነው።

24ኛው ዙር ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለም አቀፍ 10ኪሜ ህዳር 8 ቀን 2017 በ50ሺ ተሳታፊዎች ይካሄዳል፡፡

@tikvahethsport     @kidusyoftahe