TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#Paris2024

አሜሪካዊው የአጭር ርቀት ሯጭ ኖሀ ላይልስ የ 100ሜትር ወንዶች ሩጫ ፍፄሜ ውድድርን በበላይነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት መሆን ችሏል።

የፍፃሜ ውድድሩን አሜሪካዊው አትሌት ኖሀ ላይልስ የግሉን ምርጥ ሰዓት 9.79 በማስመዝገብ ማጠናቀቅ ችሏል።

በውድድሩ ጃማይካዊው ቶምፕሰን ሁለተኛ እንዲሁም ሌላኛው አሜሪካዊ ኬርሌይ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የወቅቱ የ 100ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ጣልያናዊው ጃኮብስ ከሜዳልያ ውጪ ሆኖ አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024           #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 800 እና 5000 ሜትር ፍፃሜ እንዲሁም የወንዶች 3000ሜ መሰናክል ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ምሽት 2:04 :- 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ማጣሪያ ( አትሌት ጌትነት ዋለ ፣ ለሜቻ ግርማ እና ሳሙኤል ፍሬው )

- ምሽት 4:45 :- 800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ( አትሌት ወርቅነሽ መሰለ  እና ፅጌ ድጉማ )

- ምሽት 4:15 :- 5000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ( ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና መዲና ኢሳ )

*በውድድሩ ኢትዮጵያ እስካሁን አንድ የብር ሜዳልያ ማሳካት ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024           #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የሴቶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ እንዲሁም የሴቶች 1500ሜ ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ቀን 5:05 :- 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ( አትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ ፣ ብርቄ ሀየሎም እና ድርቤ ወልተጂ )

- ምሽት 4:10 :- 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ( አትሌት ሎሚ ሙለታ እና ሲምቦ አለማየሁ )

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዛሬ ከምሽቱ 4፡14 ብርቅዬ አትሌቶቻችንን በፓሪሱ ኦሎምፒክስ 3000 ሜትር መሰናክል የሴቶች ፍፃሜ ይሳተፋሉ!

💥ሀገራችንን ወክለዉ የሚሳተፉ አትሌቶቻችን:
ሴምቦ አለማየሁ
ሎሚ ሙለታ

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን! 💚💛❤️

የፓሪስ ኦሎምፒክስን በ350 ብር በጎጆ ፓኬጅ ይከታተሉ! ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ዛሬውኑ ደንበኝነትዎን ያራዝሙ!
👇
https://mydstv.onelink.me/vGln/dg1

#Paris2024 #LikeAChamp #ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia
#Paris2024           #TeamEthiopia 🇪🇹

የ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር በዛሬው ዕለት ሲቀጥል ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የፍፃሜ እና ማጣሪያ አትሌቲክስ ውድድሮች ይጠበቃሉ።

በዛሬው ዕለት የወንዶች 3000ሜ መሰናክል ፍፃሜ እንዲሁም የወንዶች 5000ሜ እና የሴቶች 1500ሜ "repêchage" ማጣሪያ ውድድሮች ይደረጋሉ።

ኢትዮጵያ በማን ትወከላለች ?

- ቀን 6:10 :- 5000ሜ ወንዶች ማጣሪያ (ሀጎስ ገብረህይወት ፣ ቢኒያም መሀሪ እና አዲሱ ይሁኔ)

- ቀን 7:45 :- 1500ሜ ሴቶች "repêchage"
ማጣሪያ ( አትሌት ብርቄ ሀየሎም )

- ምሽት 4:40 :- 3000ሜ ወንዶች መሰናክል ፍፃሜ ( አትሌት ለሜቻ ግርማ ፣ ጌትነት ዋሌ እና ሳሙኤል ፍሬው )

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 5000ሜ ወንዶች ማጣሪያ ውድድር በሁለተኛው ምድብ ማጣሪያ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ቢኒያም መሀሪ እና አዲሱ ይሁኔ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጧል።

አትሌት ቢኒያም መሀሪ የማጣሪያ ውድድሩን 13:51:82 በሆነ ሰዓት በመግባት #ሁለተኛ ደረጃን እንዲሁም አዲሱ ይሁኔ  የማጣሪያ ውድድሩን 13:52:62 በሆነ ሰዓት በመግባት #ስምንተኛ  ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የ 5000ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:00 ሰዓት የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በዛሬው ዕለት በተደረገው የ 5000ሜ ወንዶች ማጣሪያ የመጀመሪያ ምድብ ውድድር ላይ ወድቀው የነበሩ አራት አትሌቶች ለፍፃሜ እንዲያልፉ መደረጉ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ ብሪታንያዊው ጆርጅ ሚልስን ጨምሮ ሶስት የወደቁ አትሌቶች በቅዳሜው የፍፃሜ ውድድር ተሳታፊ ይሆናሉ።

በውድድሩ መሐል ወድቆ የነበረው ብሪታንያዊው ጆርጅ ሚልስ ከውድድሩ በኋላ አንተ ነህ ጠልፈህ የጣልከኝ በሚል ለፍፃሜ ከደረሰው ከፈረንሳዊው ሁጎ ሀይ ጋር ተጋጭቶ ነበር።

የቀድሞ እንግሊዛዊ የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ዳኒ ሚልስ ልጅ የሆነው አትሌት ጆርጅ ሚሎስ ከውድድሩ በኋላ “ እሱ ነው እንድወድቅ ያደረገኝ ሀይል ባለው ቃል አናግሬዋለሁ ፣ ማለፌ ጥሩ ነው “ ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የከፍታ ዝላይ ውድድር የወቅቱ የኦሎምፒክ ሻምፒዮኖች ጣልያናዊው ጂያንማርኮ ታምቤሪ እና ኳታራዊው ኢሳ ባርሺም ለፍፃሜ ደርሰዋል።

ሁለቱ ተወዳዳሪዎች በቶክዮ 2020 ኦሎምፒክ ውድድር በተመሳሳይ 2.37ሜ ከፍታ በመዝለል የወርቅ ሜዳልያውን መጋራታቸው አይዘነጋም።

የፊታችን ቅዳሜ በሚደረገው ተጠባቂ የኦሎምፒክ ፍፃሜ ውድድር ጂያንማርኮ ታምቤሪ እና ኢሳ ባርሺም ይጠበቃሉ።

ጣልያናዊው የከፍታ ዝላይ ተወዳዳሪ ጂያንማርኮ ታምቤሪ ከሳምንት በፊት ባጋጠመው ህመም ሆስፒታል ገብቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ለፍፃሜ መብቃት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በአንደኛው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርቄ ሀየሎም ለፍፃሜ ሳታልፍ ቀርታለች።

አትሌት ብርቄ ሀየሎም የግማሽ ፍፃሜ ውድድሩን #አስረኛ  ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

በመቀጠል በሁለተኛው ምድብ የሚገኙት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ውድድራቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:25 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 1500ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በሁለተኛው ምድብ የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

አትሌት ድርቤ ወልተጂ የማጣሪያ ውድድሩን  3:55:10  በሆነ ሰዓት ውድድሩን #አንደኛ ደረጃን እንዲሁም ጉዳፍ ፀጋዬ የማጣሪያ ውድድሩን  3:56:41 በሆነ ሰዓት #አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

የ1500ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ቅዳሜ ነሐሴ 4/2016 ዓ.ም ምሽት 3:25 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ የ200ሜ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ቦትስዋናዊው አትሌት ሌትስሌ ቴቦጎ ማሸነፍ ችሏል።

ለቦትስዋና የመጀመሪያ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ያስገኘው ሌትስሌ ቴቦጎ በኦሎምፒክ መድረክ የ200 ሜትርን ማሸነፍ የቻለ በታሪክ የመጀመሪያ አፍሪካዊ አትሌት ሆኗል።

በተለይም በውድድሩ በብዙ የተጠበቀው የ100ሜ አሸናፊው አሜሪካዊው አትሌት ኖዋ ናይልስ ውድድሩን ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ሌትስሌ ቴቦጎ 19:46 በሆነ ሰዓት አንደኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ አሜሪካዊያኖቹ ኬኒ ቤድናሬክ እና ኖዋ ናይልስ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ አስራ አራተኛ ቀን ውሎ ውድድሮች መካከል በፈረንሳይ እና ስፔን መካከል የሚደረገው የወንዶች እግርኳስ የፍፃሜ ጨዋታ እጅግ ተጠባቂ ነው።

ከጨዋታው አስቀድሞ አስተያየት የሰጠው የፈረንሳይ ኦሎምፒክ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ቴሪ ሄነሪ " ጨዋታው ከባድ ቢሆንም እኔ ብቸኛው የሚታየኝ ህልም የወርቅ ሜዳልያውን ስናሸንፍ ነው " ብሏል።

"ሀገራች ረዥም ጊዜ በእግርኳስ ወርቅ ማግኘት አልቻለችም " በማለት ስፔን ለ 32ዓመታት በእግርኳስ ወርቅ አለማግኘቷን ያስታወሰቱ አሰልጣኝ ሳንቲ ዴኒያ በበኩላቸው " ይህ ትልቅ ፈተና ነው ፤ ጨዋታው ተቀራራቢ ፉክክር ይኖረዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

በፈረንሳይ እና ስፔን የኦሎምፒክ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን መካከል የሚደረገው የፍፃሜ ጨዋታ ምሽት 1:00 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024

የአሜሪካ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብራዚል አቻው ጋር ያደረገውን የፍፃሜ ጨዋታ 1ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ሆኗል።

የአሜሪካ ሴቶች ኦሎምፒክ እግርኳስ ቡድን በታሪኩ አምስተኛ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያውን ማሸነፍ ችሏል።

አሜሪካ ሶስቱን የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳልያ ማሸነፍ የቻለችው በማርታ የምትመራውን ብራዚል በማሸነፍ ነው።

ብራዚላዊቷ ታሪካዊ የፊት መስመር ተጨዋች ማርታ የመጨረሻ ጨዋታዋን ተቀይራ በመግባት አድርጋለች።

ማርታ ከብራዚል ብሔራዊ ቡድን ጋር ኢንተርናሽናል ዋንጫ ማሸነፍ ሳትችል የእግርኳስ ህይወቷን አጠናቃለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe