TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ኢንተር ሚላን ድል አድርጓል !

በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ኢንተር ሚላን ኤስ ሚላንን በሜዳው 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የኢንተር ሚላንን የማሸነፊያ ግቦች ኤዲን ዤኮ እና ሄንሪክ ሚኪታሪያን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ሁለቱ ክለቦች የመልስ ጨዋታቸውን ቀጣይ ሳምንት በማድረግ ለፍፃሜ የሚያልፈው ክለብ የሚለይ ይሆናል።

#CheersToPassion
#CheersToAllFans
#Heineken

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
🟢 የ2015 ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ
📆 ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.
📍 ቦቆጂ፣ ኢትዮጵያ

የሯጮች ምድር በሆነችው ቦቆጂ ከተማ ኑ! እንሩጥ!

ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ተራራ የመውጣት እና የካምፒንግ ምሽት ሲኖር፣ እንዲሁም እሁድ ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.  የ2ተኛው ዙር ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡

የመመዝገቢያ ዋጋ: 350ብር
መመዝገቢያ ቅፅ👇
https://drive.google.com/file/d/1O_Y33f6mugB7zl_IDcK9mVsOna9co4Vm/view?usp=sharing

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን👇
☎️ +251116635757/+251116185841

📸Image: The Bekoji Track Classic

#2023GreatBokojiRun #EthioTelecom #LandofOrigins
"ታማኝ የቤቲካ ደጋፊዎች የመጫወቻ ነጥቦችን ይሸለማሉ! አሁኑኑ betika.et ላይ ይወራረዱ!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ!
የዛሬውን ዕለታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/dailyjackpot)
የዛሬው የተመረጡ ዕለታዊ ጨዋታዎች ላይ ለመወራረድ - (betika.et)
የሳምንታዊ ጃክፖት ላይ ለመወራረድ - (betika.et/weeklyjackpot)"
መድፈኞቹ የተጫዋቻቸውን ውል ለማራዘም ተቃርበዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወሳኝ የፊት መስመር ተጫዋች ቡካዮ ሳካ በክለቡ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚፈራረም ተገልጿል።

ከሁለት ወራት በፊት ከስምምነት መደረሱ ሲገለፅ ቡካዮ ሳካ እስከ 2028 የውድድር ዘመን በኤምሬትስ የሚያቆየውን ኮንትራ ሯት በቅርቡ በይፋ ይፈራረማል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሻምፒየንስ ሊጉን ማን ያሸንፋል ?

የዘንድሮው የውድድር ዓመት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሊጠናቀቅ አጓጊ ምዕራፍ ላይ ሲገኝ የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂ ፒተር ሸማይክል ማን አሸናፊ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል።

" የሪያል ማድሪድ እና ማንችስተር ሲቲ ጨዋታ አሸናፊ የዘንድሮው የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ በፍፃሜው እንደሚያሸንፍ እርግጠኛ ነኝ " በማለት ቅድመ ግምቱን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አርሰናል የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የቁጥር አንድ ግብ ጠባቂው አሮን ራምስዴልን ኮንትራት ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ከስምምነት መድረሱ ተገልጿል።

እንግሊዛዊው ግብ ጠባቂ አሮን ራምስዴል አርሰናል ያቀረበለትን ተጨማሪ ክፍያ የሚያስገኝ አዲስ ውል መቀበሉ የተገለፀ ሲሆን በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ተነግሯል።

መድፈኞቹ በተጨማሪም የቡካዩ ሳካን ውል ለማራዘም ከስምምነት የደረሱ ሲሆን የተከላካዩ ዊሊያም ሳሊባን ኮንትራት ለማራዘም በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምርጡ ተጫዋች ነበር "

ክሮሽያዊው የባሎን ዶር አሸናፊው ሉካ ሞድሪች በትላንትናው ዕለት ከባርሴሎና ጋር እንደሚለያይ ላሳወቀው ሰርጅዮ ቡስኬት ያለውን አድናቆት እና ክብር በማህበራዊ ገፁ አጋርቷል።

" በተቃራኒ ከገጠምኳቸው ተጫዋቾች መካከል ቡስኬት ምርጡ ነው "  የሚለው ሉካ ሞድሪች ከእርሱ ጋር በተቃራኒው መጫወት በመቻሉ ደስተኛ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ስኬታማ እንደሆንኩ ይሰማኛል "

እንግሊዛዊው የቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሀሪ ኬን በእግር ኳስ ህይወቱ ብዙ ስኬቶችን እንዳሳካ እንደሚሰማው ተናግሯል።

ሀሪ ኬን በንግግሩም " ምንም እንኳን ለእይታ የምናቀርባቸው ዋንጫዎች ባይኖሩንም በእግር ኳስ ህይወቴ ብዙ ስኬቶችን እንዳሳካሁ ይሰማኛል።

በእግርኳስ ህይወቴ ማሳካት ካልቻልኳቸው ነገሮች አንዱ ዋንጫ ነው እሱን ለማሳካት እዚህ ሁልጊዜም እፋለማለሁ ፣ እዚህ ጥሩ ስሜት ይሰማኛል።

አልቸኩልም ገና ብዙ አመት ይቀረኛል ይህ ደግሞ እንድነሳሳ ያደርገኛል በእያንዳንዱ የውድድር አመት ማሳካት እፈልጋለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from WANAW SPORT
ነገ የሚደርስ ማልያዎን ዛሬ ይዘዙ !

የተዘጋጁ ማሊያዎችን በ 499 ብር ብቻ በእጅዎ ያስገቡ።

ዋናው ወደ ፊት . . . . .

📞 ይደውሉን :- 📱0910 851 535   
                      📱0901138283

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

ነገ የሚደርስ ማልያዎን ዛሬ ይዘዙ !
የሻምፒየንስ ሊግ ፍፃሜን ማን ሊመራው ይችላል ?

የዘንድሮውን የውድድር አመት አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ፍፃሜ ጨዋታን ፖላንዳዊው ዳኛ ሲሞን ማርሲንያክ በመሀል ዳኝነት ሊመሩ እንደሚችሉ ተገምቷል።

የ 42ዓመቱ ፖላንዳዊ ዳኛ ሲሞን ማርሲንያክ በአርጀንቲና እና ፈረንሳይ መካከል የተደረገውን የ2022ቱ የኳታር ዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ መምራታቸው ይታወሳል።

የዘንድሮው የውድድር አመት አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ግማሽ ፍፃሜው ላይ ሲገኝ ቀጣይ ሳምንት በሚደረጉ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች የፍፃሜ ተፋላሚ ክለቦች የሚለዩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫን ካሳካ ስንት ያገኛል ?

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ በዘንድሮው የውድድር አመት የሶስትዮሽ ዋንጫን የሚያሳኩ ከሆነ የሚሸለሙት የገንዘብ መጠን ታውቋል።

ማንችስተር ሲቲ በዘንድሮው የውድድር አመት የፕርሚየር ሊግ ፣ የኤፌ ካፕ እና ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን የሚያሳካ ከሆነ 300 ሚልዮን ፓውንድ የሚጠጋ ገንዘብ እንደሚያገኝ ተነግሯል።

ሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫውን ያሳካ ይሆን ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሪያል ማድሪድ አይገባኝም "

አርጀንቲናዊው የቀድሞ የማንችስተር ሲቲ የፊት መስመር ተጨዋች ሰርጅዮ ኩን አጉዌሮ ሪያል ማድሪድ በሁሉም አመታት የሚዘጋጀው ለሻምፒየንስ ሊግ እንደሆነ ተናግሯል።

" የሪያል ማድሪድ ነገር አይገባኝም ፣ እነሱ በእያንዳንዱ የውድድር አመት ዝግጅት የሚያደርጉት የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን እያሰቡ ይመስለኛል።" ሲል ሰርጅዮ አጉዌሮ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የምንጫወተው ለሶስት ዋንጫ ነው "

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ጃክ ግሪሊሽ ቡድናቸው በዚህ አመት ሶስቱንም ዋንጫዎች እንደሚያነሳ እርግጠኛ መሆናቸውን ተናግሯል።

ጃክ ግሪሊሽ በንግግሩም " የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ማሸነፍ እንፈልጋለን ፣ ከዚህ በፊት አሸንፈን የማናውቀው ውድድር ነው ፣ እየተጫወትን የምንገኘው ሻምፒዮንስ ሊግን ለማሸነፍ ብቻ አይደለም።

የፕርሚየር ሊግ እና የኤፌ ካፕ ዋንጫዎችንም ለማሸነፍ ነው የምንጫወተው በዚህ ደግሞ በጣም እርግጠኞች ነን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በቀጣይ የምንፋለመው ለዋንጫ ነው "

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ተጨዋች ጆርዳን ሄንደርሰን ሊቨርፑል በቀጣዩ የውድድር አመት እግር ኳስ ለመጫወት ብቻ እንደማይቀርብ ተናግሯል።

ጆርዳን ሄንደርሰን በንግግሩም " በሚቀጥለው የውድድር አመት የምንፋለመው አግር ኳስ ለመጫወት ብቻ አይደለም ፣ ዋንጫዎችን ለማሸነፍም ጭምር ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማድሪድ ዋንጫውን ያሸንፋል "

አርጀንቲናዊው የቀድሞ የሎስ ብላንኮዎቹ የፊት መስመር ተጨዋች አንግል ዲማሪያ ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን እንደሚያሸንፍ ተናግሯል።

አንግል ዲማሪያ በንግግሩም " እኔ እንደማስበው ሪያል ማድሪድ ማንችስተር ሲቲን አሸንፎ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫን ያነሳል።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ ሽንፈት አስተናግደዋል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መቻል ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል።

የመቻልን የማሸነፊያ ግብ የቀድሞ የፈረሰኞቹ ተጨዋች ከነዓን ማርክነህ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ፈረሰኞቹ በውድድር አመቱ ሁለተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

መቻል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰላሳ ሶስት በማድረስ አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሽንፈት ያስተናገደው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀምሳ አንድ ነጥብ ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል።

የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ ከተከታዩ ባህርዳር ከተማ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ #አራት ጠቧል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀዋሳ ከተማ እንዲሁም መቻል ከ ሲዳማ ቡና የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኤርሊንግ ሀላንድ ከፍተኛ ጉርሻ ሊያገኝ ይችላል !

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር አጥቂ ኤርሊንግ ሆላንድ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከክለቡ የሚያገኘው ጉርሻ እስከ 5.6 ሚልዮን ዩሮ ሊደርስ እንደሚችል ተገልጿል።

ኖርዌያዊው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ እና የሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን የሚያሸንፍ ከሆነ ለእያንዳንዱ አንድ ሚልዮን ዩሮ ጉርሻ እንደሚያገኝ ተነግሯል።

በተጨማሪም ኤርሊንግ ሀላንድ የባሎን ዶር አሸናፊ የሚሆን ከሆን ሌላ አንድ ሚልዮን ዩሮ እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ የኤፌ ካፕ ዋንጫን ካሸነፍ 350,000 ዩሮ ጉርሻ ይጠብቀዋል።

እንዲሁም የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃ እየመራ የሚገኘው ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ የሚያገኛቸው የግል ክብሮች የጉርሻ መጠኑን ከፍ እንደሚያደርጉለት ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሊቨርፑል መረጋጋት አለበት "

የኒውካስል ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ካሉም ዊልሰን በአርሰናል የገጠማቸው ሽንፈት ወደ ሻምፒየንስ ሊግ ሳያመሩ ሊያሻሽሏቸው የሚገቡ ነገሮች መኖራቸውን እንዳሳያቸው ተናግሯል።

" የአርሰናል ሽንፈት ለሻምፒየንስ ሊጉ ከማለፋችን በፊት መሄድ ያለብን ርቀት እንዳለ አሳይቶናል ፣ ከሊድስ እና ሌስተር ጋር የምናደርገው ጨዋታ ከባድ ነው ከአራቱ ጨዋታዎች ሶስቱን ማሸነፍ ይጠበቅብናል።

ሊቨርፑል ትንሽ መረጋጋት አለበት ፣ ከሁለት ሳምንት በፊት የሻምፒየንስ ሊግ ጠረን እየሸተተኝ እንደሆነ ተናግሬ ነበር አሁን ግን ሽታው ጠፍቷል የት እንደደረሰ አላውቅም።"ሲል ካሉም ዊልሰን ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የሊቨርፑል የወሩ ምርጥ ተጨዋች ታውቋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት እንግሊዛዊው የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር አርኖልድ የሊቨርፑል የወርሀ ሚያዝያ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe