TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
#Ethiopia  🇪🇹

በጋና አክራ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ላይ እየተሳተፈ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በተለያዩ ርቀቶች ባደረጓቸው ውድድሮች ድሎችን አሳክቷል።

ዛሬ ከተደረጉ ውድድሮች መካከል ፡-

በ 800ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ አንደኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገራችን የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።

በ10,000ሜ ወንዶች ፍፃሜ አትሌት ንብረት መላክ ውድድሩን በበላይነት በማጠናቀቅ የወርቅ እንዲሁም አትሌት ገመቹ ዲዳ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳልያዎች አስመዝግበዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በውድድሩ እስከ አሁን #በአትሌቲክስ

- አራት የወርቅ ፣

- ሁለት የብር እና

- አንድ የነሀስ ሜዳልያዎችን በማስመዝገብ የአትሌቲክስ የሜዳልያ ሰንጠረዡን በአንደኝነት እየመራች ትገኛለች።

በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ከአትሌቲክስ በተጨማሪም በነጠላ የብስክሌት ውድድር ኪያ ጀማል የብር ሜዳሊያ ማስገኘት ችሏል።

#አጠቃላይ የሜዳሊያ ሰንጠረዡ ምን ይመስላል ?

1ኛ ግብፅ ፡- 165 ሜዳሊያዎች
2ኛ ናይጄርያ ፡- 84 ሜዳሊያዎች
3ኛ ደቡብ አፍሪካ ፡- 95 ሜዳሊያዎች

10ኛ ኢትዮጵያ ፡- ስምንት ሜዳሊያዎች

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
Forwarded from HEY Online Market
55 inches = 110,000 Birr
65 inches = 145,000 Birr

75 inches = 245,000 Birr
85 inches = 375,000 Birr

LG Home Theatre = 59,000 Birr
Sony Home Theatre = 59,000 Birr

Contact us :
0953964175 @heymobile

@Heyonlinemarket
ማኔ ክለብ የገዛው ለሀገሩ ታዳጊዎች መሆኑን ገለፀ !

ሴኔጋላዊው የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ናስር የፊት መስመር ተጨዋች ሳዲዮ ማኔ በፈረንሳይ አራተኛ ሊግ የሚወዳደረውን ቡርዥ ፉት ክለብ መግዛቱ ይታወቃል።

ሳድዮ ማኔ መቀመጫውን በፈረንሳይ ቡርዥ ከተማ ያደረገውን ክለብ ከፍተኛ ድርሻ በመግዛት ክለቡን የተቆጣጠረው ለሀገሩ ታዳጊ ተጨዋቾች በማሰብ መሆኑን ተናግሯል።

የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ሳድዮ ማኔ ሲናገርም " ሴኔጋል ውስጥ የእግርኳስ አካዳሚ አለኝ ታዳጊዎችን እዛ እያሰለጠንኩ ወደ ቡርዥ እንዲመጡ አደርጋለሁ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" እንግሊዝ ዋንጫ ካነሳች ከብራዚል የበለጠ ቆይታለች "

ብራዚላዊው ተጨዋች አንድሬስ ፔሬራ ብሔራዊ ቡድናቸው ከእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያደርገውን የወዳጅነት ጨዋታ አሸናፊ እንደሚሆን ተናግሯል።

" ለእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ክብር አለን " ያለው ፔሬራ ነገርግን እንደ ሁልጊዜው የማሸነፍ ግምቱ የብራዚል ነው ፣ እንግሊዝ ለመጨረሻ ጊዜ ዋንጫ ያሸነፈችበት አመት ከብራዚል የበለጠ ነው።"ብሏል።

የብራዚል ብሔራዊ ቡድን ከእንግሊዝ አቻቸው ጋር ቅዳሜ ምሽት 4:00 በዌምብሌይ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል የተጫዋቹን ውል ሊያራዝም ነው ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የጃፓናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋ ታኬሂሮ ቶሚያሱ ኮንትራት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። ጃፓናዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ በመድፈኞቹ ቤት የረጅም ጊዜ ኮንትራት ይፈርማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተዘግቧል። በአሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ የሚሰለጥነው አርሰናል በቅርቡ የተጫዋቹን ውል ማራዘም ይፋ እንደሚያደርግ…
አርሰናል የተጫዋቹን ውል በይፋ አራዘመ !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የጃፓናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋ ታኬሂሮ ቶሚያሱ ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 25ዓመቱ ጃፓናዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ በመድፈኞቹ ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ተገልጿል።

ከሶስት አመታት በፊት ከቦሎኛ አርሰናልን የተቀላቀለው ተጨዋቹ በቆይታቸውም በሁሉም ውድድሮች ለመድፈኞቹ ሰባ ስምንት ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አርሰናል የተጫዋቹን ውል በይፋ አራዘመ ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የጃፓናዊውን የተከላካይ ስፍራ ተጨዋ ታኬሂሮ ቶሚያሱ ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል። የ 25ዓመቱ ጃፓናዊ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ታኬሂሮ ቶሚያሱ በመድፈኞቹ ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን ውል መፈረሙ ተገልጿል። ከሶስት አመታት በፊት ከቦሎኛ አርሰናልን የተቀላቀለው ተጨዋቹ በቆይታቸውም በሁሉም ውድድሮች…
" ለአርሰናል መጫወት ህልሜ ነው " ቶሚያሱ

በመድፈኞቹ ቤት ለተጨማሪ አመታት ለመቆየት ውሉን ያራዘመው ጃፓናዊው ተከላካይ ታኬሂሮ ቶሚያሱ ለአርሰናል መጫወት ህልሙ መሆኑን ከፊርማው በኋላ ተናግሯል።

" እዚህ ለመቆየት ውሌን በማራዘሜ በጣም ደስተኛ ነኝ " ሲል የተደመጠው ታኬሂሮ ቶሚያሱ አርሰናል ከአለማችን ምርጥ ክለቦች አንዱ ነው እዚ መጫወት ህልሜ ነው ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ የመጨረሻ ልምምዳቸውን ሰርተዋል !

በቀጣይ የወዳጅነት ጨዋታዎች ያሉበት የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ረፋድ ጨዋታውን በሚያደርግበት አዲስ አበባ ስታዲየም መስራት ችሏል።

ብሔራዊ ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ከ3:00 እስከ 4:30 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሰራ ሲሆን በልምምድ ወቅት ሁሉም ተጨዋቾች በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸው ታውቋል።

በልምምዱ ላይ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ፣ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳኛቸው ንገሩ እንዲሁም ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ባህሩ ጥላሁን ተገኝተው ቡድኑን አበረታተዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የስነ ልቦና ባለሞያ ማግኘቴ ጠቅሞኛል " ሪቻርልሰን

ብራዚላዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም የፊት መስመር ተጨዋች ሪቻርልሰን የስነ ልቦና ባለሞያ እርዳታ ማግኘቱ ትልቅ ጥቅም እያስገኘለት እንደሚገኝ ገልጿል።

ሪቻርልሰን ከወራቶች በፊት የስነ ልቦና ባለሞያ ማግኘት እንደሚፈልግ ገልፆ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ጥቅም እንዳገኘበት እና ሌሎች ተጨዋቾች እገዛ ቢያገኙ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ መክሯል።

" አሁን ላይ የስነ ልቦና ባለሞያ አለኝ ለተጨዋቾች አስፈላጊ ነገር ነው " የሚለው ሪቻርልሰን በየሳምንቱ ከባለሞያ ጋር ቀጠሮ አለኝ በጣም ጠቅሞኛል ብሏል።

ሌሎች ተጨዋቾች የስነ ልቦና ባለሞያ ጠቃሚ መሆኑን መረዳት እንዳለባቸው የጠቆመው ሪቻርልሰን " አንድ ጊዜ ቢጀምሩ ምን እንደምል ይገባቸዋል ሜዳ ውስጥ ትልቅ ጥቅም አለው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምርጥ ተጨዋች ለማድሪድ መጫወት አለበት " ካርቫል

ስፔናዊው የሎስ ብላንኮዎቹ የመስመር ተጨዋች ዳኒ ካርቫል ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ወደ ሪያል ማድሪድ መዘዋወር እንዳለበት ተናግሯል።

" ምርጥ ተጨዋቾች ሀሉ ለሪያል ማድሪድ ግዴታ መጫወት አለባቸው " የሚለው ዳኒ ካርቫል ኪሊያን ምባፔ ደግሞ ከእነሱ አንዱ ነው ስለዚህ በአመቱ መጨረሻ የሚመጣበት እድል አለ።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በመዲናችን አይን ቦታ ከቦሌ á‰ 7ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ለቡ መብራት በተንጣለለው 65,395ካሬ ላይ ያረፈ ሠፊ መንደር፤ 5  የመዋኛ ገንዳወች፣ የከርሰምድር ውሀ፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ስፍራወችን áŠĽá‹ŤáŠ•á‹łáŠ•á‹ą ህንጻወች 5 ቤዝመንት፣ ሠፊ ሰገነት፣ 5 ሊፍቶች ያላቸው፣ 50% ባንክ የተመቻቸለት፤

እጅግ ዘመናዊ በሆነው የግንባታ መሳሪያ በኮንካል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከእስቱዲዎ እስከ ባለ 4መኝታ ድረስ እንዲሁም የንግድ ሱቆችን በማራኪ ዲዛይንና በላቀ ጥራት የተዘጋጁ፤

እስከ 25% የዋጋ ቅናሽ (6,000,000ብር)
10% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም  ስትድዮ 👉56.6ካሬ=605,000ብር
    
አንድ መኝታ
    👉77.7ካሬ,=831,000ብር
ሁለት መኝታ
     👉123.3ካሬ=1,318,000ብር
ሶስት መኝታ
    👉146.8ካሬ=1,570,000ብር
አራት መኝታ
      👉186.9ካሬ=1,998,000ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ልብ ይበሉ አንድ ቤት ሲገዙ አንድ ቤት በነፃ አለው።

ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251988887999
       +251918642895
     ሀሎ      ይበሉ።
https://t.iss.one/Engineergashaw
🇪🇹 Sport, Peace, Unity, and Partnership! 🇪🇹

WANAW SPORT - Proud Partner of the 2024 AAU Sport Festival!

💪🏾 When there's competition, there's #WANAW! 💪🏾

Instagram | Facebook | TikTok

🏅 ዋናው ወደፊት...

@wanawsportwear
ሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ቀጥሯል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የቀድሞ የበርንማውዝ ሀላፊ ሪቻርድ ሂውዝን የክለቡ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የቀድሞ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ማይክል ኤድዋርድስ ወደ ሊቨርፑል በከፍተኛ ሀላፊነት መመለሱን ተከትሎ ክለቡን የተቀላቀለው ሪቻርድ ሂውዝ በአመቱ መጨረሻ ስራውን እንደሚጀመር ተገልጿል።

" ይህንን እድል በማግኘቴ ትልቅ ኩራት ይሰማኛል ሊቨርፑል ልዩ የሆነ ክለብ ነው በዚህ ሀላፊነት እንዳገለግል እድሉ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ።"ሲል ሪቻርድ ሂውዝ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሁሉም ጋርዲዮላን መሆን ይፈልጋል " ብሩኖ ፈርናንዴዝ

የማንችስተር ዩናይትዱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአለምን እግር ኳስ መቀየር መቻሉን ገልጿል።

" አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የአለምን እግር ኳስ ቀይሯል " የሚለው ብሩኖ ፈርናንዴዝ አሁን ላይ ሁሉም ፔፕ ጋርዲዮላን መሆን ይፈልጋል መደበቅ አያስፈልግም።"ብሏል።

ማንችስተር ሲቲ ባለው ውጤት እና ስኬት ምክንያት ሁሉም ክለቦች እንደ እነሱ ለመጫወት ይሞክራሉ ሲል ብሩኖ ፈርናንዴዝ ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe