TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ራፋኤል ቫራን ወደ ሳውዲ አረቢያ ?

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ተወካዮች የፈረንሳዊውን የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ወኪል በዝውውር ዙሪያ ማነጋገራቸው ተገልጿል።

ፈረንሳዊዎቹ የአል ኢትሀድ ተጨዋቾች ካሪም ቤንዜማ እና ንጎሎ ካንቴ ራፋኤል ቫራን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እንዲቀላቀላቸው ለማሳመን መሞከራቸው ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ራፋኤል ቫራን አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ መቆየት መፈለጉን ተከትሎ ከሳውዲ አረቢያ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መልቀቁ ለሁሉም ጥሩ ነው " ሉዊስ ኤንሪኬ

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ክለቡን መልቀቁ ሁሉንም የሚበጅ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።

" እዚህ ከመጣሁ ጀምሮ ላሳየው ጥሩ ባህሪ አመሰግነዋለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ " ክለቡን መልቀቁ ለሁሉም ሰው ጥሩ ይመስለኛል ፣ እሱ ትልቅ ተጨዋች ነው መልካሙን እመኝለታለሁ።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ህልሜ እውን ሆኗል " ዋታሩ ኢንዱ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጃፓናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዋታሩ ኢንዱ ከስቱትጋርት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 30ዓመቱ ተጨዋች ዋታሩ ኢንዱ በሊቨርፑል ቤት የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ ሊቨርፑል ለተጨዋቹ ዝውውር 19 ሚልዮን ዩሮ ወጪ ማድረጉ ተነግሯል።

ዋታሩ ኢንዱ ፊርማውን ካኖረ በኋላ " ሊቨርፑልን የሚያክል ትልቅ ክለብ በመቀላቀሌ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ህልሜ እውን ሆኖልኛል።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሲቲ ተጨዋች ለማስፈረም ተስማማ ! ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ፓኩዌታ ከዌስትሀም ዩናይትድ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው ተገልጿል። በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ ለዌስትሀም ያቀረቡት 70 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ ውድቅ መሆኑን ተከትሎ አዲስ ሒሳብ ለማቅረብ መዘጋጀታቸው ተነግሯል። @tikvahethsport    …
ሉካስ ፓኩዌታ ወደ ማንችስተር ሲቲ ?

ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ፓኩዌታ ከዌስትሀም ዩናይትድ ለማስፈረም እያደረገ የሚገኘው ንግግር አሁን ላይ መቋረጡ ተገልጿል።

በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ ከሉካስ ፓኩዌታ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ተጨዋቾቹን በጉዳት ያጣል !

ማንችስተር ሲቲ በነገው ዕለት ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር በሚያደርገው የሊጉ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር የወሳኝ ተጨዋቾቹን ግልጋሎት እንደማያገኝ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

እንደ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገለፃ በነገው ተጠባቂ ጨዋታ ሩበን ዲያስ እና ጆን ስቶንስ ከጨዋታው ውጪ ሲሆኑ በርናርዶ ሲልቫ በበኩሉ የመሰለፍ ዕድሉ አጠራጣሪ ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጆኒ ኢቫንስ በዩናይትድ ቤት ይቆያል ?

ጆኒ ኢቫንስ በቅርቡ የአጭር ጊዜ ኮንትራት በቀድሞ ክለቡ ማንችስተር ዩናይትድ ቤት በመፈረም የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ከቀያይ ሴጣኖቹ ጋር ማሳለፉ ይታወሳል።

ጆኒ ኢቫንስ አሁን ላይ በማንችስተር ዩናይትድ ቤት ለአንድ የውድድር አመት ለመቆየት የሚያስችለውን ውል ለመፈረም ንግግር ላይ እንደሚገኝ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ አስታውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሳውዲ ገበያውን አስቸጋሪ አድርጋዋለች " ክሎፕ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሳውዲ አረቢያ የዝውውር ገበያው አስቸጋሪ እንዲሆን እያደረገችው እንደምትገኝ ገልፀዋል።

" ሳውዲ አረቢያ የዝውውር ገበያው ላይ ነገሮችን ከባድ እያደረገች ነው ፣ በጣም ከባድ ሆኗል ፣ አውሮፓን ጨምሮ በሁሉም ትልልቅ ሊጎች ነገሮች ጥሩ አይደሉም ፣ ማለቂያ የሌለው የሳውዲ አረቢያ ገንዘብ ችግር ሆኗል።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ምርጡ አቋማችን ላይ አንገኝም " ጋርዲዮላ

በነገው ዕለት ተጠባቂ የሊግ ጨዋታቸውን ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ማንችስተር ሲቲዎች አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከጨዋታው በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ፔፕ ጋርዲዮላ ምን አሉ ?

- " ኒውካስል ዩናይትድን ለመግጠም ዝግጁ ነን ፣ የምንገጥመው የተለየ ቡድን ነው የሻምፒየንስ ሊግ ተሳታፊ ቡድን ነው ለእኛ ራሳችንን ለመፈተሽ ጥሩ ፈተና ነው።

- ስታዲየሙ ሙሉ እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን ፣ ደጋፊዎቻችን ከእኛ ጋር እንድትሆኑ እንፈልጋለን በተለይ ጥሩ ባልሆንበት ሰዓት የእናንተ ማበረታቻ ያስፈልገናል።

- ምርጡ አቋማችን ላይ አንገኝም ፣ ነገር ግን ምንም ማለት አይደለም አንዳንድ ነገሮችን ማስተካከል ብቻ ያስፈልጋል መንፈሳችን አሁንም አለ።

- ኒውካስል ዩናይትድ የሊጉ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ለረጅም ጊዜ እንደሚቆይ ይሰማኛል።"ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማጓየር እዚህ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ "

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሀግ የዝውውር መስኮት ከመዘጋቱ በፊት ጥሩ አማራጭ ካገኘ ቡድናቸው ተጨማሪ ተጨዋች ለማስፈረም ሊሞከር እንደሚችል ጠቁመዋል።

ኤሪክ ቴን ሀግ ምን ጉዳዮችን አነሱ ?

- "ጥሩ የቡድን ስብስብ አለን ሁሉም ቦታዎች ላይ አማራጭ ተጨዋቾችን አካተናል ፣ ነገር ግን እኛ ዩናይትዶች ነን ሁልጊዜ ቡድኑን ስለማጠናከር እናስባለን ፣ በቀጣይ ጥሩ እድል ካገኘን እንመለከታለን።

- ጂኒ ኢቫንስ ማንችስተር ዩናይትድ ውስጥ ቢቆይ እመርጣለሁ በዚህ ጉዳይ ላይ ንግግር ላይ ነን።

- ሀሪ ማጓየር የኛ ተጨዋች ነው እሱ እዚህ በመሆኑ ደስተኛ ነኝ ፣ ጥሩ የቡድን ስብስብ እንዲኖረን እንፈልጋለን አራት ጥሩ የመሐል ተከላካዮች አሉን።

ማርቲኔዝ ለቶተንሀም ለጨዋታው ብቁ ነው ?

" ሊያንድሮ ማርቲኔዝ ከቡድኑ ጋር ልምምዱን ሰርቷል ለጨዋታው ዝግጁ የሚሆን ይመስለኛል።" ቴን ሀግ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
" ሳውዲ ገበያውን አስቸጋሪ አድርጋዋለች " ክሎፕ የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሳውዲ አረቢያ የዝውውር ገበያው አስቸጋሪ እንዲሆን እያደረገችው እንደምትገኝ ገልፀዋል። " ሳውዲ አረቢያ የዝውውር ገበያው ላይ ነገሮችን ከባድ እያደረገች ነው ፣ በጣም ከባድ ሆኗል ፣ አውሮፓን ጨምሮ በሁሉም ትልልቅ ሊጎች ነገሮች ጥሩ አይደሉም ፣ ማለቂያ የሌለው የሳውዲ አረቢያ ገንዘብ ችግር…
" ችግሬ ከሳውዲ ሳይሆን ከገንዘቧ ነው " ክሎፕ

የሊቨርፑል ዋና አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ሳውዲ አረቢያ እያደረገች የምትገኘው የዝውውር እንቅስቃሴ ህግ ሊበጅለት እንደሚገባ አሳስበዋል።

" እኔ ከሳውዲ አረቢያ ጋር ምንም ችግር የለብኝም " ያሉት አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ " እኔ ችግሬ ማለቂያ ከሌለው ገንዘባቸው ጋር ነው ፣ እሱ ለእኛ ችግር ሆኖብናል የሆነ ህግ ሊበጅለት ይገባል።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ ወሳኝ ድል አስመዝግበዋል !

የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ውድድር የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ከዛንዚባሩ " KMKM " ክለብ ጋር ያደረገው የሀገራችን ተወካይ ቅዱስ ጊዮርጊስ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ቢኒያም በላይ እና ናትናኤል ዘለቀ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ የመልስ ጨዋታውን አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ነሐሴ 21/2015 ዓ.ም የሚያደርግ ይሆናል።

ፈረሰኞቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ የዛንዚባሩን " KMKM " ክለብ የሚያሸንፉ ከሆነ በሁለተኛው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከግብፁ አል አህሊ ጋር ይገናኛሉ።

👉 የፈረሰኞቹን የማሸነፊያ ግቦች በጎል ቻናላችን ያገኛሉ :- https://t.iss.one/+rbdEU4UaEdQxYWFk

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ንግድ ባንክ ነጥብ ተጋርቷል !

ሀገራችንን በሴካፋ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ወክሎ እየተወዳደረ የሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን የማጣርያ ሶስተኛ ጨዋታውን ከካምፓላ ክዊንስ ጋር አድርጎ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቀዳሚ ያደረገች ግብ የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ ከመረብ ማሳረፍ ችላለች።

ተከታታይ ሁለት የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎቹን ያሸነፈው ንግድ ባንክ የምድብ የመጨረሻ ጨዋታውን ከቀናት በኋላ ከደቡብ ሱዳኑ ዬይ ጆይንት ስታርስ ጋር የሚያደርግ ይሆናል

በዩጋንዳ አዘጋጅነት እየተደረገ የሚገኘውን የሴካፋ ሴቶች ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚያሸንፈው ክለብ የሴካፋ ዞንን ወክሎ በካፍ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ላይ የሚሳተፍ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሉካስ ፓኩዌታ ወደ ማንችስተር ሲቲ ? ማንችስተር ሲቲ ብራዚላዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ፓኩዌታ ከዌስትሀም ዩናይትድ ለማስፈረም እያደረገ የሚገኘው ንግግር አሁን ላይ መቋረጡ ተገልጿል። በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲዎች በቅርቡ ከሉካስ ፓኩዌታ ጋር በግል ከስምምነት መድረሳቸው መገለፁ ይታወሳል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሉካስ ፓኩዌታ ምርመራ ላይ መሆኑ ተገለፀ !

ማንችስተር ሲቲን ለመቀላቀል ተቃርቦ የነበረው የዌስትሀም የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካስ ፓኩዌታ በእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ ተገልጿል።

የእንግሊዝ እግር ኳስ ማህበር በተጨዋቹ ላይ ምርመራ የከፈተው የስፖርት ውርርድ ህጎችን ጥሷል በሚል መሆኑ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በቅርቡ ወደ ሜዳ ለመመለስ ዝግጁ ነኝ "

የማንችስተር ሲቲው ቤልጂየማዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ኬቨን ዴብሮይን ያጋጠመውን ጉዳት ተከትሎ የተሳካ ቀዶ ጥገና ማድረጉን አስታውቋል።

ኬቨን ዴብሮይን ስለ ጉዳቱ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት " ከበርንሌይ ጨዋታ በኋላ ያለው የጉዳት ዜና በአካል እና አእምሮ ትልቅ ጉዳት ነበረው።

አሁን ቀዶ ጥገናው ተጠናቋል ከጉዳቴ ለማገገም እና በቅርቡ ወደ ሜዳ ለመመለስ ዝግጁ ነኝ ድጋፍ ያደረጋችሁልኝን ሁሉ አመሰግናለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ወደ ጣልያን ? ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንሲኒ ጋር የተለያየው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በምትኩ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲን በሀላፊነት ለመሾም እንደሚፈልግ ተገልጿል። ጣልያናዊው የቀድሞ የሴርያው ሻምፒዮን ናፖሊ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በበኩላቸው ከሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቀረበላቸውን ሀላፊነት ለመቀበል ፍቃደኛ መሆናቸው ተነግሯል። አሰልጣኙ በሀላፊነት የሚሾሙ ከሆነ በቀጣዩ የ…
የጣልያን ብሔራዊ ቡድን አዲስ አሰልጣኝ ሾሟል !

በቅርቡ ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንሲኒ ጋር የተለያየው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በምትኩ የቀድሞ የናፖሊ አሰልጣኝ የነበሩትን ሉቺያኖ ስፓሌቲ በሀላፊነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

ጣልያናዊው የቀድሞ የሴርያው ሻምፒዮን ናፖሊ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ብሔራዊ ቡድኑን እስከ 2026 ለማሰልጠን በሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን ተሾመዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለሀገሬ 🇪🇹 ክብር ስል ሪከርዱን አስመልሳለሁ " አትሌት ለተሰንበት ግደይ 

አትሌት ለተሰንበት ግደይ የ 5000ሜትር ሪከርድ በኬንያዊቷ አትሌት ፌዝ ኪፕዬጎን ከሀገራችን ስለተወሰደበት መንገድ ስትናገር ቁጭት ውስጥ ሆና ነው።

የ 1500ሜትር የገንዘቤ ዲባባ ሪከርድ ከዛም በቀናት ልዩነት የራሷ የ 5000ሜ ሪከርድ በፌዝ ኪፕዬጎን ሲሰበር መመልከት " የሀገር ክብር " እንደመነካት ነው ትላለች።

" የሚፈለገው ብር አይደለም ሁለቱ ሪከርድ ከሀገራችን ሲወጣ በጣም ተበሳጭቻለሁ " የምትለው ለተሰንበት ግደይ " ይህን ሪከርድ እንደማስመልስ ቃል እገባለሁ ለራሴ #ሳይሆን ለሀገሬ #ኢትዮጵያ ክብር ስል " ትላለች።

በስተመጨረሻም " ኢትዮጵያ ሀገራችን ሁሌም የወርቅ ሀገር እንድትሆንልኝ እመኛለሁ " ስትል ንግግሯን ትቋጫለች።

የአለም ሻምፒዮናው በነገው ዕለት ሲጀምር በ 10,000ሜትር ፍፃሜ የምትወዳደረው ለተሰንበት ግደይ እንደ ኦሪገን ውድድር ሁሉ ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ ለማምጣት ብርቱ ፉክክር ይጠብቃታል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
🥇WANAW  ወደ ፊት...👉

✔️አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት 
                   ወረቀት ፊትለፊት

👇🏽wanaw
  https://t.iss.one/wanawsportwear

    🤳0901 138 283
    🤳0910 851 535
    🤳0913 586 742
ኢትዮጵያ ዛሬ በማን ትወከላለች ?

1⃣ - 3000ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣርያ 

👉 ጌትነህ ዋለ ( ምድብ አንድ ) ፣ አብርሀም ስሜ ( ምድብ ሁለት ) እና ለሜቻ ግርማ ( ምድብ አራት )

🇪🇹 አትሌት ለሜቻ ግርማ የወቅቱ የአለም እና የኦሎምፒክ ( ቶኪዮ ) የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን በዚህ ርቀት አዲስ ታሪክ ይፅፋል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህ የማጣርያ ውድድር ከምድቡ ቀዳሚውን #አምስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ።

2⃣ - 1500ሜትር የሴቶች ማጣርያ

👉 ድርቤ ወልተጂ ( ምድብ ሁለት ) ፣ ብርቄ ሀየሎም ( ምድብ ሶስት ) እና ሂሩት መሸሻ ( ምድብ አራት )

በዚህ የማጣርያ ውድድር ከምድቡ ቀዳሚውን #ስድስት ደረጃዎች ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ።

የውድድር ዓመቱ የ1500ሜትር ምርጥ ሰዓት የማን ነው ?

1ኛ :- ፌዝ ኪፕዬጎን ( ኬንያ ) የአለም ሪከርድ ባለቤት ስትሆን በዚህ ርቀት በማጣርያ በምድብ #ሁለት ትገኛለች።

ጎዳፍ ፀጋይ ፣  ሂሩት መሸሻ ፣ ብርቄ ሀየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ተከታዩን አራት ደረጃዎች በመያዝ የአመቱ ምርጥ ሰዓት ባለቤት ናቸው።

3⃣ - የ10,000ሜትር ሴቶች ፍፃሜ

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ ፣ ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ እና ለምለም ሀይሉ

የውድድር መካሄጃ ሰዓት ለመመልከት :- https://t.iss.one/tikvahethsport/44027

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዛሬ ተጠባቂ መርሐ ግብሮች !

11:00 ሊቨርፑል ከ በርንማውዝ

1:30 ቶተንተም ከ ማንችስተር ዩናይትድ

1:30 ፍሮሲኖን ከ ናፖሊ

2:30 አል ሜርያ ከ ሪያል ማድሪድ

3:45 ኢንተር ሚላን ከ ሞንዛ

4:00 ማንችስተር ሲቲ ከ ኒውካስል ዩናይትድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ ሰራተኞች የግሪንውድን መመለስ ተቃወሙ !

ማንችስተር ዩናይትድ ለአመታት ከሜዳ ርቆ የቆየውን እንግሊዛዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሜሰን ግሪንውድ ወደ ቡድኑ ለመመለስ ማሰባቸው መገለፁ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ ጥቂት የማንችስተር ዩናይትድ ሰራተኞች ሜሰን ግሪንውድ ወደ ቡድኑ የሚመለስ ከሆነ ስራ እንደሚለቁ ማስታወቃቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም ሌሎች የክለቡ ሰራተኞች ተጨዋቹ የሚመለስ ከሆነ የስራ ማቆም አድማ ለማድረግ በማሰብ ላይ እንደሚገኙ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሳውዲ በራቸውን ስታንኳኳ ሁሉም ይከፍታሉ "

የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ሁሉም ሳውዲ አረቢያ ላይ ተቃውሞ እያቀረበ ቢገኝም በራቸውን ስታንኳኳ ግን በቀይ ምንጣፍ ነው የተቀበሏት በማለት ተናግረዋል።

" ሁሉም ሰው ስለ ሳውዲ አረቢያ ተቃውሞ እያቀረበ ነው " ያሉት አሰልጣኙ " ነገር ግን ሳውዲ በራቸውን ስታንኳኳ ሁሉም ከፍተው ' ምን ትፈልጊያለሽ ? ሁሉንም ነገር እሸጣለሁ ' ብለው በደስታ ነው የሚናገሩት።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe