TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
" ለሊቨርፑል የመጫወት ህልም ነበረው "

ሊቨርፑልን ለመቀላቀል የተቃረበው ጃፓናዊ አማካይ ዋታሩ ኢንዱ ለሊቨርፑል የመጫወት ህልም እንደነበረው የክለቡ ስቱትጋርት አሰልጣኝ ሰባስትያን ሆኔስ ተናግረዋል።

" እሱ በሰላሳ አመቱ ፕርሚየር ሊግ ውስጥ ለሊቨርፑል የመጫወት ዕድል አግኝቷል " ያሉት የስቱትጋርት አሰልጣኝ ሰባስትያን ሆኔስ " ይህ የእሱ ህልሙ ነበር።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኔይማር እንዲቀላቀለኝ አልፈልግም " ጄራርድ

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትፋቅ ዋና አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድ ብራዚላዊው ተጨዋች ኔይማር ቡድኑን እንዲቀላቀል እንደማይፈልግ ተናግሯል።

" ኔይማርን አልፈልገውም እሱም የእኔን ቡድን መቀላቀል አይፈልግም " ያለው የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ስቴቨን ጄራርድ " ይህ የሚሆን ከሆነ ስራዬን የበለጠ ከባድ ያደርግብኛል።"ብሏል።

ስቴቨን ጄራርድ አያይዞም ኔይማር ጥሩ ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች መሆኑን እና በእግርኳስ ህይወቱ የሚገባውን ያህል እውቅና አለማግኘቱን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፒኤስጂን በመልቀቄ ደስተኛ ነኝ " ሜሲ

የአሜሪካውን ክለብ ኢንተር ሚያሚ ይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሊግ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ መድረስ የቻለው አርጀንቲናዊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከፍፃሜ ጨዋታው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን አድርጓል።

ሊዮኔል ሜሲ ምን አለ ?

- " የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ለእኔ ትልቁ ህልሜ ነበር በጣም አስፈላጊ የሆነውን ዋንጫ አሳክቻለሁ አሁን ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም።

- ወደዚህ እንድመጣ ያደረገኝ የቤተሰብ ፍላጎት ነው እዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ በስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ሚያሚ ውስጥ በእለትተእለት ህይወቴ ደስተኛ ነኝ።

- ከባርሴሎና ወደ ፒኤስጂ ስሄድ በጣም ከባድ ውሳኔ ነበር ከፒኤስጂ ወደ ኢንተር ሚያሚ ግን የተለየ ነው እዚህ በመምጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

- የአለም ዋንጫን ካሳካሁ በኋላ ለሌሎች ሽልማቶች ግድ የለኝም ስምንተኛ ባሎን ዶር የማሸነፍ ከሆነ እደሰታለሁ ነገርግን የሚቀይረው ነገር አይኖርም።

- የእኛን ልምምዶች ያላየ ሰው ለሊግ ካፕ ፍፃሜ መድረሳችን ሊገርመው ይችላል ፣ ለፍፃሜው ተዘጋጅተናል ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማራኪ እና ልዩ ልዩ ልብ አንጠልጣይ ጨዋታዎች ከቤቲካ ፋስታ!
የመቻል ስፖርት ክለብ አመራሮች እና ባለሙያዎች የዋናዉ ስፖርት ትጥቆች ፋብሪካን ጎበኙ፡፡

በኢትዮጵያ ያለዉን የስፖርት ትጥቆች ችግር ለመቅረፍ የተመሰረተዉ ዋናዉ ስፖርት በአጭር ጊዜ በገበያዉ ያለዉን ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል፡፡

በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለዉ ምርት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ቅሬታ ሲያሰሙ የነበሩት የስፖርት ቡድኖች በዋናዉ ስፖርት የስፖርት ትጥቅ ምርቶች መፍትሄ እንዳገኙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ላይ ያሉትን ተመሳሳይ ችግሮችን መፍትሄ እየሰጠ ይገኛል፡፡ የአቅርቦት ችግር ሳያጋጥም በፍጥነት ምርቶችንም እያደረሰ ይገኛል፡፡

በቅርቡም የተለያዩ የስፖርት ቤተሰቦች በኃብቴ ጋርመንት እና ፕሪንቲንግ ስር ያለዉ ዋናዉ የስፖርት ትጥቆች ብራንድን ጎብኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ዉስጥ አንጋፋዉ እና ዉጤታማዉ መቻል ስፖርት ክለብ አመራሮች እና ባለሙያዎች ትናንት ነሀሴ 11/2015ዓ.ም ገርጂ አካባቢ የሚገኘዉን የድርጅቱን የምርት ሂደት እና የፋብሪካ አቅም ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የኃብቴ ጋርመንት እና ፕሪንቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኃ/ስላሴ ገ/ክርስቶስ የኢትዮጵያ ስፖርት ባለዉለታ የሆነዉ መቻል ስፖርት ክለብ አመራሮች እና ባለሙያዎች በተቋማችን በመገኘት ድርጅታችንን ስለጎበኙልን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል፡፡

መቻል ስፖርት ክለብ በእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን በአትሌቲክስ ፣ እጅ ኳስ እና ቮሊ ቮልን ጨምሮ በበርካታ ስፖርቶች ቡድኖችን መስርቶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ስፖርት ክለብ ነዉ፡፡

ቻናላችን :-https://t.iss.one/wanawsportwear
የአለም ሻምፒዮናው ነገ ይጀምራል !

ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትካፈልበት አስራ ዘጠነኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በነገው ዕለት በቡዳፔሽት አትሌቲክስ ሴንተር በደማቅ ሁኔታ መደረጉን ይጀምራል።

የመክፈቻው መርሐ ግብር ምን ይመስላል ?

ከቀኑ 6:35 :- 3000ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣርያ

ከቀኑ 8:15 :- 1500ሜትር ሴቶች ማጣርያ

ምሽት 2:02 :- 1500ሜትር ወንዶች ማጣርያ

ምሽት 3:55 :- 10,000ሜትር ሴቶች #ፍፃሜ

🇪🇹 የ 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሙሉ መርሐ ግብር ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

መልካም እድል ለአትሌቶቻችን !

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልኮት ጫማውን ሰቅሏል !

እንግሊዛዊው የቀድሞ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቲኦ ዋልኮት በ 34ዓመቱ ከፕሮፌሽናል እግርኳስ ራሱን ማግለሉን ይፋ አድርጓል።

በቅርቡ ከሳውዝሀምፕተን ጋር የተለያየው ቲኦ ዋልኮት ለአርሰናል ሶስት መቶ ዘጠና ሰባት ጨዋታዎች ማድረግ የቻለ ሲሆን አንድ መቶ ስምንት ግቦች አስቆጥሮ ሰማንያ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

ዋልኮት በመድፈኞቹ ቤት ሶስት የኤፌ ካፕ እና ሁለት የኮምዩኒቲ ሺልድ ዋንጫንም ማሳካት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሮቤርቶ ማንሲኒ የጣልያን ብሔራዊ ቡድንን ለቀቁ ! ጣልያናዊው የ 58ዓመት አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንሲኒ ከጣልያን ብሔራዊ ቡድን ሀላፊነታቸው መነሳታቸው ይፋ ተደርጓል። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንሲኒ ከጣልያን እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በጋራ ስምምነት ብሔራዊ ቡድኑን ለመልቀቅ መወሰናቸው ይፋ ሆኗል። የጣሊያን ብሔራዊ ቡድን የ2024 አውሮፓ ዋንጫ ውድድር ሊጀመር አስር ወራቶች ሲቀሩት ከዋና አሰልጣኙ ጋር ተለያይቷል።…
አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ ወደ ጣልያን ?

ከአሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንሲኒ ጋር የተለያየው የጣልያን ብሔራዊ ቡድን በምትኩ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲን በሀላፊነት ለመሾም እንደሚፈልግ ተገልጿል።

ጣልያናዊው የቀድሞ የሴርያው ሻምፒዮን ናፖሊ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ በበኩላቸው ከሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን የቀረበላቸውን ሀላፊነት ለመቀበል ፍቃደኛ መሆናቸው ተነግሯል።

አሰልጣኙ በሀላፊነት የሚሾሙ ከሆነ በቀጣዩ የ ዩሮ 2024 እና በ 2026ቱ የዓለም ዋንጫ ውድድር የጣልያን ብሔራዊ ቡድንን የሚመሩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሮሚዮ ላቪያ ሳውዝሀምፕተንን ተሰናብቷል !

የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲን ለመቀላቀል ከጫፍ የደረሰው ቤልጂየማዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮሚዮ ላቪያ ሳውዝሀምፕተንን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ተሰናብቷል።

ሮሚዮ ላቪያ በስንብት መልዕክቱም " እዚህ በነበረኝ ቆይታ ላደረጋችሁልኝ ነገር ሁሉ በጣም አመሰግናለሁ ፣ ጥሩ ተጨዋች እንድሆን እገዛ ያደረጋችሁልኝን ሁሉ አመስጋኝ ነኝ።

ሳውዝሀምፕተን ሁሌም በውስጤ ይቀመጣል ጥሩ የውድድር አመት እንዲገጥማችሁ እመኛለሁ ክለቡ በቅርቡ ወደ ፕርሚየር ሊግ ተመልሶ ለመመልከት እጓጓለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ በይፋ ተጨዋች አስፈርሟል !

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ቤልጂየማዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮሚዮ ላቪያ ከሳውዝሀምፕተን በረጅም ጊዜ ኮንትራት ማስፈረማቸውን በይፋ አስታውቀዋል።

ሰማያዊዎቹ ለ 19ዓመቱ ቤልጂየማዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮሚዮ ላቪያ ዝውውር 58 ሚልዮን ፓውንድ የሚደርስ ሒሳብ ወጪ በማድረግ በሰባት አመት ኮንትራት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

ሮሚዮ ላቪያ ፊርማውን ካኖረ በኋላ " ቼልሲን በመቀላቀሌ እና የቡድኑ አካል በመሆኔ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ቼልሲ ትልቅ ታሪክ ያለው ድንቅ ክለብ ነው ፣ እዚህ ለመጀመር ጓጉቻለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ትልቅ ቡድን መሆን እንፈልጋለን " ኤዲ ሆው

የኒውካስል ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድናቸው በነገው ተጋጣሚያቸው ማንችስተር ሲቲ ጥንካሬ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ አሳስበዋል።

አሰልጣኝ ኤዲ ሆው በንግግራቸውም " በማንችስተር ሲቲ ጥንካሬዎች ላይ ማተኮር እና እነሱን ለማስቆም መሞከር አለብን ፣ ራሳችንን ሆነን መገኘት ይኖርብናል።

ትልቅ ቡድን መሆን እንፈልጋለን የራሳችን የሆነ የምንታወቅበት ማንነት እንዲኖረን እንፈልጋለን ያንንም ሁሉም ክለቦች ላይ መተግበር አለብን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ራፋኤል ቫራን ወደ ሳውዲ አረቢያ ?

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትሀድ ተወካዮች የፈረንሳዊውን የማንችስተር ዩናይትድ ተከላካይ ራፋኤል ቫራን ወኪል በዝውውር ዙሪያ ማነጋገራቸው ተገልጿል።

ፈረንሳዊዎቹ የአል ኢትሀድ ተጨዋቾች ካሪም ቤንዜማ እና ንጎሎ ካንቴ ራፋኤል ቫራን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እንዲቀላቀላቸው ለማሳመን መሞከራቸው ተዘግቧል።

ይሁን እንጂ ራፋኤል ቫራን አሁን ላይ አውሮፓ ውስጥ መቆየት መፈለጉን ተከትሎ ከሳውዲ አረቢያ የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ ማድረጉ ተነግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" መልቀቁ ለሁሉም ጥሩ ነው " ሉዊስ ኤንሪኬ

የፈረንሳዩ ክለብ ፒኤስጂ ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኔይማር ክለቡን መልቀቁ ሁሉንም የሚበጅ ውሳኔ መሆኑን ተናግረዋል።

" እዚህ ከመጣሁ ጀምሮ ላሳየው ጥሩ ባህሪ አመሰግነዋለሁ " ያሉት አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ " ክለቡን መልቀቁ ለሁሉም ሰው ጥሩ ይመስለኛል ፣ እሱ ትልቅ ተጨዋች ነው መልካሙን እመኝለታለሁ።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ህልሜ እውን ሆኗል " ዋታሩ ኢንዱ

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጃፓናዊውን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዋታሩ ኢንዱ ከስቱትጋርት ማስፈረማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 30ዓመቱ ተጨዋች ዋታሩ ኢንዱ በሊቨርፑል ቤት የአራት አመት ኮንትራት መፈረሙ ሲገለፅ ሊቨርፑል ለተጨዋቹ ዝውውር 19 ሚልዮን ዩሮ ወጪ ማድረጉ ተነግሯል።

ዋታሩ ኢንዱ ፊርማውን ካኖረ በኋላ " ሊቨርፑልን የሚያክል ትልቅ ክለብ በመቀላቀሌ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ህልሜ እውን ሆኖልኛል።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe