TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
" ተጨማሪ ተጨዋቾችን እንመለከታለን "

የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ከክሪስትያል ፓላስ ጋር ከሚያደርገው የሁለተኛ ሳምንት የሊግ መርሐግብር በፊት በሰጡት አስተያየት ተጨማሪ ተጨዋቾች ለማስፈረም እንደሚሞክሩ ጠቁመዋል።

ሚኬል አርቴታ ምን አሉ ?

- " ካይ ሀቨርትስ ከማንችስተር ሲቲ ጋር ጥሩ ተጫውቷል ብዬ አስባለሁ ጥሩ የግብ እድሎችንም አግኝቶ ነበር ነገር ግን መጠቀም አልቻለም ከዛ ውጪ ጥሩ ስራ ሰርቷል።

- ጁሪየን ቲምበርን ያስፈረምንበት ግልጽ አላማ ነበረን ለቡድኑ መስጠት የሚችለው ነገር የሚታይ ነው ፣ በዚህ አመት ይህንን ማድረግ አልቻለም ፣ እንዳለመታደል ሆኖ እንደዚህ አይነት ነገር ተከስቷል።

- በሁሉም የሜዳ ክፍሎች ላይ ሁለት ተጨዋቾች እንዲኖሩን እንፈልጋለን በጉዳቱ ምክንያት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ተጨዋቾችን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እናደርጋለን።

አርሰናል እነማንን በጉዳት ያጣል ?

- አሌክሳንደር ዚንቼንኮ ( ልምምድ ጀምሯል በቅርቡ ወደ ሜዳ ይመለሳል )

- ጋብሬል ጄሱስ ( ለቀጣይ ጨዋታ ዝግጁ አይደለም በቅርቡ ወደ ሜዳ የመመለስ ዕድል አለው )

- ጁሪየን ቲምበር ( ለረጅም ጊዜ ከሜዳ ይርቃል )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የ 2023 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ስድስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል። በዚህም መሰረት ኬቨን ዴብሮይን ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ሀሪ ኬን ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ ፣ ቡካዩ ሳካ እና ጆን ስቶንስ በእጩነት የቀረቡ ተጨዋቾች ናቸው። የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ? @tikvahethsport    …
የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የ 2023 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች ስድስት እጩዎችን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ሞይሰስ ካይሴዶ ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ኢቫን ፈርጉሰን ፣ ጋብሬል ማርቲኔሊ ፣ ራምሴይ እና ቡካዩ ሳካ በእጩነት የቀረቡ ተጨዋቾች ናቸው።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የእንሰሳት ሀኪም መሆን እፈልግ ነበር " ፈርናንዴዝ

ፖርቹጋላዊው የማንችስተር ዩናይትድ አምበል ብሩኖ ፈርናንዴዝ እግር ኳስ ተጨዋች ባይሆን ምናልባት የእንሰሳት ሀኪም ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል።

እግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን አሁን ምን ልትሆን ትችል ነበር ተብሎ የተጠየቀው ፈርናንዴዝ " ከባድ ጥያቄ ነው ልጅ እያለሁ እንሰሳቶችን በጣም ስለምወድ የእንሰሳት ሀኪም መሆን እፈልግ ነበር።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሳውዲ የስፔን ላሊጋን ስፖንሰር አድርጋለች !

የስፔን ላሊጋ ከሳውዲ አረቢያው " Visit Saudi " ጋር በአጋርነት ለመስራት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት መፈፀማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የስፖንሰር ሺፕ ስምምነቱ ሳውዲ አረቢያን በመላው አለም ለሚገኘው የስፖርቱ ማህበረሰብ ማስተዋወቅን አላማ ያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ቼልሲ ተጨዋች ሊያስፈርም ነው ! በአሰልጣኝ ማውሪስዮ ፖቼቲኖ የሚመራው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የክሪስታል ፓላሱን ፈረንሳዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሚካኤል ኦሊሴ በረጅም ጊዜ ኮንትራት ሊያስፈርሙ መሆኑ ተገልጿል። ሰማያዊዎቹ የተጫዋቹን የውል ማፍረሻ ለክሪስትያል ፓላስ 35 ሚልዮን ፓውንድ በመክፈል ሚካኤል ኦሊሴን በቅርቡ የግላቸው እንደሚያደርጉ ይጠበቃል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሚካኤል ኦሊሴ ውሉን ማራዘሙ ተገለፀ !

በምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ እየተፈለገ የሚገኘው ፈረንሳዊ የፊት መስመር ተጨዋች ሚካኤል ኦሊሴ በክሪስታል ፓላስ ቤት ያለውን ውል ማራዘሙ ይፋ ተደርጓል።

ተጨዋቹ በክሪስትያል ፓላስ ቤት ለተጨማሪ አራት አመታት ለመቆየት ውሉን ማራዘሙን የክለቡ ፕሬዝዳንት በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ?

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የዩኤፋ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ሊዮኔል ሜሲ ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ እና ኬቨን ዴብሮይን በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው።

የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ይሆናል ? የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የዩኤፋ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ ተጨዋች #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል። በዚህም መሰረት ሊዮኔል ሜሲ ፣ ኤርሊንግ ሀላንድ እና ኬቨን ዴብሮይን በእጩነት መቅረብ የቻሉ ተጨዋቾች ናቸው። የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ማን ነው ? @tikvahethsport     @kidusyoftahe
የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ይሆናል ?

የአውሮፓ እግርኳስ ማህበር የዩኤፋ የ2023/24 የውድድር አመት የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ #ሶስት እጩዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ፣ አሰልጣኝ ሉቺያኖ ስፓሌቲ እና አሰልጣኝ ሲሞን ኢንዛጊ በእጩነት መቅረብ የቻሉ አሰልጣኞች ናቸው።

የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ ማን ነው ?

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሳውዲ መሄድ አልፈልግም " ሲዝኒ

ፖላንዳዊው የጣልያኑ ክለብ ጁቬንቱስ ግብ ጠባቂ ሲዝኒ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊግ አምርቶ የመጫወት ፍላጎት እንደሌለው ተናግሯል።

" ሳውዲ አረቢያ ሄዶ የመጫወት ፍላጎቱ የለኝም " ያለው የቀድሞ የአርሰናል ግብ ጠባቂ ሲዝኒ " እኔ አሁንም ብዙ ገንዘብ አለኝ ፣ ጁቬንቱስ ውስጥ እንዳለው አይነት አስደሳች ፈተናዎች እወዳለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጫዋቹን በጉዳት ሊያጣ ይችላል !

እንግሊዛዊው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ የመስመር ተጨዋች ሬስ ጄምስ አዲስ የጡንቻ ጉዳት ማስተናገዱ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎ የሰማያዊዎቹ አምበል ሬስ ጄምስ ለሚቀጥሉት አራት ሳምንታት ለቡድኑ ግልጋሎት #ላይሰጥ እንደሚችል ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለሊቨርፑል የመጫወት ህልም ነበረው "

ሊቨርፑልን ለመቀላቀል የተቃረበው ጃፓናዊ አማካይ ዋታሩ ኢንዱ ለሊቨርፑል የመጫወት ህልም እንደነበረው የክለቡ ስቱትጋርት አሰልጣኝ ሰባስትያን ሆኔስ ተናግረዋል።

" እሱ በሰላሳ አመቱ ፕርሚየር ሊግ ውስጥ ለሊቨርፑል የመጫወት ዕድል አግኝቷል " ያሉት የስቱትጋርት አሰልጣኝ ሰባስትያን ሆኔስ " ይህ የእሱ ህልሙ ነበር።"ብለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ኔይማር እንዲቀላቀለኝ አልፈልግም " ጄራርድ

የሳውዲ አረቢያው ክለብ አል ኢትፋቅ ዋና አሰልጣኝ ስቴቨን ጄራርድ ብራዚላዊው ተጨዋች ኔይማር ቡድኑን እንዲቀላቀል እንደማይፈልግ ተናግሯል።

" ኔይማርን አልፈልገውም እሱም የእኔን ቡድን መቀላቀል አይፈልግም " ያለው የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ስቴቨን ጄራርድ " ይህ የሚሆን ከሆነ ስራዬን የበለጠ ከባድ ያደርግብኛል።"ብሏል።

ስቴቨን ጄራርድ አያይዞም ኔይማር ጥሩ ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች መሆኑን እና በእግርኳስ ህይወቱ የሚገባውን ያህል እውቅና አለማግኘቱን ገልጿል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ፒኤስጂን በመልቀቄ ደስተኛ ነኝ " ሜሲ

የአሜሪካውን ክለብ ኢንተር ሚያሚ ይዞ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሊግ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ መድረስ የቻለው አርጀንቲናዊ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ከፍፃሜ ጨዋታው በፊት ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን አድርጓል።

ሊዮኔል ሜሲ ምን አለ ?

- " የአለም ዋንጫን ማሸነፍ ለእኔ ትልቁ ህልሜ ነበር በጣም አስፈላጊ የሆነውን ዋንጫ አሳክቻለሁ አሁን ለምንም ነገር ግድ አይሰጠኝም።

- ወደዚህ እንድመጣ ያደረገኝ የቤተሰብ ፍላጎት ነው እዚህ በጣም ደስተኛ ነኝ በስፖርቱ ብቻ ሳይሆን ሚያሚ ውስጥ በእለትተእለት ህይወቴ ደስተኛ ነኝ።

- ከባርሴሎና ወደ ፒኤስጂ ስሄድ በጣም ከባድ ውሳኔ ነበር ከፒኤስጂ ወደ ኢንተር ሚያሚ ግን የተለየ ነው እዚህ በመምጣቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

- የአለም ዋንጫን ካሳካሁ በኋላ ለሌሎች ሽልማቶች ግድ የለኝም ስምንተኛ ባሎን ዶር የማሸነፍ ከሆነ እደሰታለሁ ነገርግን የሚቀይረው ነገር አይኖርም።

- የእኛን ልምምዶች ያላየ ሰው ለሊግ ካፕ ፍፃሜ መድረሳችን ሊገርመው ይችላል ፣ ለፍፃሜው ተዘጋጅተናል ዋንጫውን ማሸነፍ እንፈልጋለን።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማራኪ እና ልዩ ልዩ ልብ አንጠልጣይ ጨዋታዎች ከቤቲካ ፋስታ!
የመቻል ስፖርት ክለብ አመራሮች እና ባለሙያዎች የዋናዉ ስፖርት ትጥቆች ፋብሪካን ጎበኙ፡፡

በኢትዮጵያ ያለዉን የስፖርት ትጥቆች ችግር ለመቅረፍ የተመሰረተዉ ዋናዉ ስፖርት በአጭር ጊዜ በገበያዉ ያለዉን ተቀባይነት እያገኘ መጥቷል፡፡

በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለዉ ምርት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ቅሬታ ሲያሰሙ የነበሩት የስፖርት ቡድኖች በዋናዉ ስፖርት የስፖርት ትጥቅ ምርቶች መፍትሄ እንዳገኙ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ላይ ያሉትን ተመሳሳይ ችግሮችን መፍትሄ እየሰጠ ይገኛል፡፡ የአቅርቦት ችግር ሳያጋጥም በፍጥነት ምርቶችንም እያደረሰ ይገኛል፡፡

በቅርቡም የተለያዩ የስፖርት ቤተሰቦች በኃብቴ ጋርመንት እና ፕሪንቲንግ ስር ያለዉ ዋናዉ የስፖርት ትጥቆች ብራንድን ጎብኝተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ ዉስጥ አንጋፋዉ እና ዉጤታማዉ መቻል ስፖርት ክለብ አመራሮች እና ባለሙያዎች ትናንት ነሀሴ 11/2015ዓ.ም ገርጂ አካባቢ የሚገኘዉን የድርጅቱን የምርት ሂደት እና የፋብሪካ አቅም ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የኃብቴ ጋርመንት እና ፕሪንቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኃ/ስላሴ ገ/ክርስቶስ የኢትዮጵያ ስፖርት ባለዉለታ የሆነዉ መቻል ስፖርት ክለብ አመራሮች እና ባለሙያዎች በተቋማችን በመገኘት ድርጅታችንን ስለጎበኙልን ኩራት ተሰምቶናል ብለዋል፡፡

መቻል ስፖርት ክለብ በእግር ኳስ ብቻ ሳይሆን በአትሌቲክስ ፣ እጅ ኳስ እና ቮሊ ቮልን ጨምሮ በበርካታ ስፖርቶች ቡድኖችን መስርቶ እየተንቀሳቀሰ ያለ ስፖርት ክለብ ነዉ፡፡

ቻናላችን :-https://t.iss.one/wanawsportwear