ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !
9:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
10:00 ኤቨርተን ከ ማንችስተር ሲቲ
10:00 ሞንዛ ከ ናፖሊ
12:00 አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ
12:30 አርሰናል ከ ብራይተን
1:00 ቦሎኛ ከ ሮማ
3:45 ጁቬንቱስ ከ ክሪሞኔንሴ
4:00 እስፓኞል ከ ባርሴሎና
@tikvahethsport @kidusyoftahe
9:00 ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
10:00 ኤቨርተን ከ ማንችስተር ሲቲ
10:00 ሞንዛ ከ ናፖሊ
12:00 አዳማ ከተማ ከ ባህርዳር ከተማ
12:30 አርሰናል ከ ብራይተን
1:00 ቦሎኛ ከ ሮማ
3:45 ጁቬንቱስ ከ ክሪሞኔንሴ
4:00 እስፓኞል ከ ባርሴሎና
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሎዛ አበራ አለም አቀፍ እውቅናን አገኘች !
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሉሲዎቹ ኮከብ የፊት መስመር ተጫዋች ሎዛ አበራ አለም አቀፍ እውቅናን ማግኘቷ ይፋ ተደርጓል።
በሴቶች ላይ ብቻ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራው " Unstoppable 100 " የሚል መጠሪያን የያዘው መፅሄት ሎዛ አበራን ተፅዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ 100 ግለሰቦች መካከል አንዷ በማድረግ መርጧታል።
" እጅግ ኩራት ተሰምቶኛል " በማለት ለዝግጅት ክፍላችን የተናገረችው ሎዛ የምትሰራቸው ስራዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ሲሰጣቸው ማየቷ እንዳስደሰታት ገልፃለች።
አያይዛም " የምሰራው ስራ በዚህ ደረጃ ሲያስከብር በጣም ያኮራል ፣ በዚህ ትልቅ መፅሄት ላይ በመውጣቴ ኩራት ይሰማኛል ፣ በቀጣይ ለሚመጡ ስፖርተኞች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራል ብዬ አስባለሁ " በማለት ሎዛ አበራ ተናግራለች።

ባርሴሎና ዋንጫውን ዛሬ ይቀበላል ?
የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ዛሬ ምሽት ከእስፓኞል ጋር የሚያደርገውን የካታላን ደርቢ ጨዋታ የሚያሸንፍ ከሆነ ከወዲሁ የላሊጋው አሸናፊ መሆኑን ያረጋግጣል።
ባርሴሎና ዛሬ ምሽት የውድድሩ አሸናፊ የሚሆንበትን ውጤት የሚያስመዘግብ ከሆነ ዋንጫውን ከአወዳዳሪው አካል ላይቀበል እንደሚችል ተገልጿል።
ባርሴሎና የዋንጫ ድሉን ከደጋፊዎቻቸው ጋር ለማክበር ማሰባቸውን ተከትሎ የዋንጫ ስነ ስርዓቱ ቀጣይ ሳምንት ከሪያል ሶሴዳድ ጋር ካምፕ ኑ ላይ በሚያደርጉት ጨዋታ እንደሚሆን ተጠቁሟል።

" ሜሲ የዓለም ዋንጫ ሲያነሳ እንባ ተናንቆኛል "
ስፔናዊው እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጨዋች ራፋኤል ናዳል አርጀንቲናዊው የሰባት ጊዜ ባላን ዶር አሸናፊ ሊዮኔል ሜሲ የዓለም ዋንጫን ሲያነሳ እንባ ተናንቆት እንደነበር ገልጿል።
ራፋኤል ናዳል በንግግሩም " ሜሲ የዓለም ዋንጫን ሲያነሳ እንባ ተናንቆኝ ነበር በወቅቱ የአርጀንቲና ደጋፊ ባልሆንም አንድ ትልቅ ስኬታማ ሰው ከብዙ ልፋት በኋላ ያጣውን ነገር ሲያገኝ ስመለከት ስሜቴ ተነክቷል።"ሲል ተደምጧል።

የኢንተር እና ኤሲ ሚላንን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?
የፊታችን ማክሰኞ ኢንተር ሚላን ከ ኤሲ ሚላን ጋር የሚያደርጉትን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።
ማክሰኞ ምሽት ስታዲዮ ጂሴፔ ሜዛ ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ፈረንሳዊው ዳኛ ክሌመንት ቱርፒን በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።
ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ሳምንት ያደረጉትን የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ኢንተር ሚላን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወሳል።

ዋናው....... የታለ ማሊያው ?
ይኸው ማልያዎት 599 ብቻ
• እርጥበት በማይዝ
• ቀላልና ምቾት የሚሰጥ
• ቶሎ የሚደርቅ
•እንዲሁም አየር በሚያስወጣ ምርጥ ጨርቅ ተዘጋጅቶ ለእርስዎ ቀርቦልዎታል።
📞 ይደውሉን :- 📱0910 851 535
📱0901138283
ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

" ሜሲ ይመለሳል ብዬ አልጠብቅም "
የኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድንን በማሰልጠን ላይ የሚገኙት የቀድሞ የባርሴሎና አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን ሊዮኔል ሜሲ ወደ ባርሴሎና ይመለሳል ብለው እንደማይጠብቁ ተናግረዋል።
አሰልጣኝ ሮናልድ ኩማን በንግግራቸውም " ሊዮኔል ሜሲ ወደ ባርሴሎና ይመለሳል ብዬ አልጠብቅም ፣ ምክንያቱም የቀድሞ ጓደኞቹ ክለቡን ይለቃሉ ፣ ወደ ሳውዲ አረቢያ ወይም ኢንተር ሚያሚ ቢያመራ ብዙም አይገርመኝም።
ዩሀን ላፖርታ ሊዮኔል ሜሲን የለቀቀው ሰው እየተባለ ስለሚታወቅ ሜሲን በመመለስ የራሱን ገፅታ ማስተካከል ይፈልጋል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

" ለኤቨርተን ጥሩ ውጤት እመኛለሁ "
የመድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ኤቨርተን ዛሬ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ጥሩ ውጤት እንዲገጥመው እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
" እንደ ትልቅ የኤቨርተን ደጋፊነቴ ለእነሱ ጥሩውን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ " የሚሉት አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዛሬ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ይህ ላይቀየር ይችላል ሲሉም ተደምጠዋል።
አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቀጥለውም ኤቨርተን የተወሰኑ ጥሩ ውጤቶች እንዳስመዘገቡ እና ባለፉት ወራቶች ጥሩ ተፎካካሪ በመሆናቸው የተሻለ ነገር እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

" በራሳችን መተማመን አለብን "
የኤቨርተኑ ዋና አሰልጣኝ ሽያን ዳይክ ከደቂቃዎች በኋላ ከማንችስተር ሲቲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ቡድናቸው በራሱ መተማመን እንዳለበት ተናግረዋል ።
ሽያን ዳይክ በንግግራቸውም " በጥሩ አቋማችንን ላይ መሆን አለብን ፣ በተጨማሪም በራሳችን ላይ መተማመን አለብን ዛሬ ለማድረግ ያሰብነው ይህንኑ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

" አዚህ መጫወት ከባድ ነው "
የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከኤቨርተኑ ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት ጨዋታው ከባድ እንደሚሆን ተናግረዋል።
" አኬ በጥሩ መሻሻል ላይ ይገኛል ነገር ግን ለዛሬ አይሆንም ፣ እዚህ ስታዲየም መጫወት ሁልጊዜም ከባድ ነው ፣ ለተጨዋቾቼ ለምናገረው መልዕክት ኤቨርተንን እንዲያሸንፉ ነው ስለ ሶስት ዋንጫ አላስብም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ ቡና ድል አድርጓል !
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የቡናማዎቹን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሮቤል ተክለሚካኤል በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰላሳ አራት በማድረስ #አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮ ኤልክትሪክ በአስራ አንድ ነጥቦች አስራ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ለገጣፎ ለገዳዲ እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ መቻል የሚጫወቱ ይሆናል።

ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !
በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ኤቨርተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነታቸውን አጠናክረዋል።
የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኢካይ ጉንዶጋን 2x እና ኤርሊንግ ሀላንድ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
በጨዋታው ኖርዌያዊው አጥቂ ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ ስድስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመራው ማንችስተር ሲቲ በተከታታይ ያደረጋቸውን አስራ አንድ የሊግ ጨዋታዎች ማሸነፍ ችሏል።
ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰማንያ አምስት በማድረስ መሪነቱን ሲያጠናክር ኤቨርተን በሰላሳ ሁለት ነጥብ አስራ ሰባተኛ ደረጃን ይዘዋል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ቼልሲ እንዲሁም ኤቨርተን ከዎልቭስ የሚገናኙ ይሆናል።