TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
🟢 የ2015 ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ
📆 ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.
📍 ቦቆጂ፣ ኢትዮጵያ

የሯጮች ምድር በሆነችው ቦቆጂ ከተማ ኑ! እንሩጥ!

ቅዳሜ ግንቦት 5 ቀን 2015 ዓ.ም. ተራራ የመውጣት እና የካምፒንግ ምሽት ሲኖር፣ እንዲሁም እሁድ ግንቦት 6 ቀን 2015 ዓ.ም.  የ2ተኛው ዙር ታላቁ ቦቆጂ ሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡

የመመዝገቢያ ዋጋ: 350ብር
መመዝገቢያ ቅፅ👇
https://drive.google.com/file/d/1O_Y33f6mugB7zl_IDcK9mVsOna9co4Vm/view?usp=sharing

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን👇
☎️ +251116635757/+251116185841

📸Image: The Bekoji Track Classic

#2023GreatBokojiRun #EthioTelecom #LandofOrigins
ሻሸመኔ ከተማ 🤝 ዋናው የስፖርት አልባሳት

የሻምፒዮኖቹ እና የኮከቦቹ ምርጫ የሆነው ዋናው የስፖርት አልባሳት የንግድ ምልክት በ 2016ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ተሳታፊ ከሆነው የሻሸመኔ እግር ኳስ ክለብ ጋር ለቀጣዮቹ ዓመታት በጋራ ለመስራት ከስምምነት መድረሱን ሲያሳውቃችሁ በደስታ ነው።

በሁለቱ አጋር ድርጅቶች መካከል የሚደረገው ስምምነት በቀጣይ ሳምንት የሁለቱ ተቋማት አመራሮች እና ሚዲያዎች በተገኙበት ለስፖርት ቤተሰቡ ይፋ ይደረጋል።

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

ዋናው ወደ ፊት . . . . . .
ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !

12:30 ኒውካስትል ዩናይትድ ከ አርሰናል

3:00 ዌስትሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ

7:30 አታላንታ ከ ጁቬንቱስ

1:00 ናፖሊ ከ ፌዮሬንቲና

12:30 ዶርትመንድ ከ ዎልፍስበርግ

3:45 ትሮይስ ከ ፒኤስጂ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
🏆🏆CHAMPION 🏆🏆 ሪያል ማድሪድ ከኦሳሱና ጋር ያደረገውን የስፔን ኮፓ ዴላሬ ፍፃሜ ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የውድድሩ አሸናፊ መሆኑን አረጋግጧል። የሎስ ብላንኮዎቹን ሁለት የማሸነፊያ ግቦች ሮድሪጎ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል። ሪያል ማድሪድ ሀያኛ የስፔን ኮፓ ዴላሬ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል። @tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሻምፒዮኖቹ ምን አሉ ?

ትላንት ምሽት በ ኮፓ ዴ ላሬ የፍፃሜ ጨዋታ ኦሳሱናን በመርታታ ሻምፒዮን መሆን የቻሉት ሪያል ማድሪድ የቡድን አባላት ደስታቸውን ገልፀዋል።

የቡድን አባላቱ ምን አሉ ?

👉 ሉካ ሞድሪች :- " ይህ ክለብ ሪያል ማድሪድ ሙሉ ህይወቴ ነው ፣ ደጋፊዎች ስሜን እየጠሩ ሲዘምሩ ስሜታዊ እሆናለሁ ያስደስተኛል ፣ እቅዴ በቀጣይ በማድሪድ መቆየት ነው" ።

👉 ካርሎ አንቾሎቲ :- " ስለ ወደፊት ቆይታዬ ብዙ ጊዜ ተናግሬያለሁ ፣ እስከ 2024 የውድድር ዓመት በክለቡ የሚያቆየኝ ኮንትራት አለኝ " ።

👉 ቶኒ ክሮስ :- " እኔ ምንጊዜም ቢሆን ማድሪድስታ ነኝ ፣ ከሪያል ማድሪድ ጋር ሁሉንም ዋንጫዎች ማሸነፍ እፈልግ ነበር ይህም እውን ሆኖልኛል" ።

👉 ፍሎሬንቲኖ ፔሬዝ :- " ቪንሰስ ጁኒየር በሚጫወትበት ቦታ ላይ የአለማችን ቁጥር አንድ ምርጡ ተጫዋች ነው " ።

👉 ካሪም ቤንዜማ :- " ማክሰኞ ሌላ ትልቅ ፈተና ይጠብቀናል ፣ ደጋፊዎቻችንን ማድረግ እንደምንችል ልንነግራችሁ እንፈልጋለን " በማለት ተናግሯል " ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ሪያል ማድሪድን አንፈራውም "

የማንችስተር ሲቲው የመሀል ሜዳ ተጨዋች በርናንዶ ሲልቫ የሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ተጋጣሚያቸው ሪያል ማድሪድን እንደማይፈሯቸው ተናግሯል።

በርናንዶ ሲልቫ በንግግሩም " ለሪያል ማድሪድ ትልቅ ክብር አለን ፣ ነገር ግን ምንም አይነት ፍርሀት የለብንም ፣ ለምን እንፈራቸዋለን።"ሲል ተደምጧል።

ፖርቹጋላዊው ተጨዋች በርናንዶ ሲልቫ አያይዞም " የሶስትዮሽ ዋንጫውን ለማሳካት በጥሩ ቁመና ላይ እንገኛለን።" በማለት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" በካርሎ አንቾሎቲ ደስተኞች ነን "

የሪያል ማድሪዱ ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ ክለቡ ከአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ጋር ደስተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ፍሎረንቲኖ ፔሬዝ በንግግራቸውም " ካርሎ አንቾሎቲ ከክለቡ ይለቃሉ የሚል ወሬ መስማት አልፈልግም ፣ እሱ ገና ቀሪ አንድ አመት ኮንትራት አለው ፣ እኛም በእሱ በጣም ደስተኞች ነን።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለዩናይትድ ወሳኝ ጨዋታ ነው "

የቀድሞ እንግሊዛዊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ጄሚ ሬድናፕ ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ የሚያሸንፍ ከሆነ ለሻምፒየንስ ሊጉ ያልፋል ብሎ እንደሚያስብ ተናግሯል።

ጄሚ ሬድናፕ በንግግሩም " ማንችስተር ዩናይትድ ዛሬ ዌስትሀም ዩናይትድን የሚያሸንፍ ከሆነ ለአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ያልፋል ብዬ አስባለሁ።

ነገር ግን ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ አመት ከሜዳቸው ውጪ ጥሩ እንዳልሆኑ መዘንጋት የለብንም ፣ ይህ ለእነሱ ወሳኝ ጨዋታ ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የማድሪድ እና ሲቲን ጨዋታ ማን ይመራዋል ?

ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ ጋር የሚያደርጉትን የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ የሚመሩት ዳኛ ታውቀዋል።

የፊታችን ማክሰኞ ምሽት ሳንቲያጎ በርናቦው ላይ የሚደረገውን ተጠባቂ ጨዋታ ፖርቹጋላዊው ዳኛ አርተር ዲያዝ በመሀል ዳኝነት እንደሚመሩት ይፋ ተደርጓል።

ሪያል ማድሪድ ከዚህ በፊት በፖርቹጋላዊው ዳኛ አርተር ዲያዝ የመሩትን ሶስት ጨዋታዎች ያደረገ ሲሆን በአንዱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ ተለያይቶ ቀሪ አንዱን ማሸነፍ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
"መልካም ዕድል!
ከፍ የተደረጉ ኦዶችን አይተዋል ? እንግዲያውስ ተወራረዱባቸው! እንዳያመልጥዎ!
Newcastle-Arsenal
West Ham- Manchester United
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!"
ኢኔስታ ከጃፓኑ ክለብ ጋር ሊለያይ ነው !

የቀድሞ የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ተጨዋች የሆነው አንድሬስ ኢኔስታ የጃፓኑን ክለብ ቪሰል ኮቤ ለመልቀቅ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተገልጿል።

የ 38ዓመቱ ተጨዋች አንድሬስ ኢኔስታ እ.ኤ.አ 2018 የጃፓኑን ክለብ ቪሰል ኮቤ የተቀላቀለ ሲሆን በክለቡ እስከ 2024 የሚያቆይ ኮንትራት አለው።

በመጪዎቹ ቀናት 39ዓመት የሚሆነው የቀድሞ የባርሴሎና ተጨዋች ኢኔስታ በቀጣይ ጫማውን እንደሚሰቅል ወይም ኢዲስ ክለብ እንደሚቀላቀል ግልፅ አላደረገም።

ስፔናዊው ተጨዋች አንድሬስ ኢኔስታ ለጃፓኑ ክለብ ቪሰል ኮቤ አንድ መቶ ሀያ ስምንት ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን ሀያ ስድስት ግቦች ማስቆጠር ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በጣልያን ሴርያ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከአታላንታ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የጁቬንቱስን የማሸነፊያ ግቦች ሳሙኤል ሊንግ ጁኒየር እና ቪላሆቪች በመጨረሻ ደቂቃ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

እንግሊዛዊው የ 19ዓመት ተጨዋች ሳሙኤል ሊንግ ለጁቬንቱስ በተሰለፈበት የመጀመሪያ ጨዋታ ግብ ማስቆጠር ችሏል።

ጁቬንቱስ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ስድስት በማድረስ #ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችል አታላንታ በሀምሳ ስምንት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ጁቬንቱስ ከክሪሞኒስ እንዲሁም አታላንታ ከ ሳለርኒታና ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ከጨዋታ ውጪ ያደርጓቸዋል "

እንግሊዛዊው የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች ዋይን ሩኒ ማንችስተር ሲቲ ወደ ሪያል ማድሪድ የሚሄደው ከጨዋታ ውጪ ሊያደርገው መሆኑን ተናግሯል።

ዋይን ሩኒ በንግግሩም " ማንችስተር ሲቲ ሪያል ማድሪድን ለማሸነፍ ብቻ አይደለም የሚሄዱት ከጨዋታ ውጪ ሊያደርጓቸውም ጭምር ነው።"ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

12:30 ኒውካስል ዩናይትድ ከ አርሰናል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የተለየ ነገር ለማድረግ እንሞክራለን "

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከኒውካስል ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

" ጋብሬል ማግሀሌስ በጣም አስፈላጊ ተጨዋቻችን ነው ፣ ትላንት የነበረውን ልምምድ በብቃት መወጣት ችሏል ስለዚህ ለጨዋታው ብቁ ነው።

ዛሬ የተለየ ነገር ለማድረግ እንሞክራለን።"ሲሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ከጨዋታው በፊት በሰጡት አስተያየት ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
በርንሌይ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል !

ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን ያረጋገጠው በርንሌይ የአሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒን ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ በርንሌይን ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ለማሰልጠን ፊርማቸውን ማኖራቸው ተገልጿል።

በርንሌይን ወደ ፕርሚየር ሊጉ ማሳደግ የቻሉት አሰልጣኝ ቪንሴንት ኮምፓኒ ስማችው ከቼልሲ እና ቶተንሀም ጋር በስፋት ሲያያዝ መቆየቱ ይታወሳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ትኩረቴ የዛሬው ጨዋታ ላይ ነው "

የኒውካስል ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤዲ ሆው ከአርሰናል ጨዋታ በፊት በሰጡት አስተያየት በዛሬው ጨዋታ ላይ ትኩረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ ስለ ዝውውር ፣ ሻምፒየንስ ሊግ ወይም ሌሎች ነገሮች ግድ የለኝሞ ፣ አሁን ሁሉንም ትኩረቴን የዛሬው ጨዋታ ላይ ብቻ ማድረግ ነው የምፈልገው፣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አይታወቅም።"ሲሉ አሰልጣኝ ኤዲ ሆው ተናግረዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ለማሸነፍ ቆርጠናል " ቡካዮ ሳካ

የመድፈኞቹ የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዮ ሳካ የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ ቆርጠው መነሳታቸው በሰጠው አስተያየት ገልጿል።

ቡካዮ ሳካ በአስተያየቱም " እንደ ባለፈው የውድድር አመት ከዚህ ስታዲየም በብስጭት ላለመሄድ ቆርጠናል።"ሲል ከጨዋታው በፊት በሰጠው አስተያየት ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
13' ኒውካስል ዩናይትድ 0-1 አርሰናል

⚽ ኦዴጋርድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

3:00 ዌስትሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ.

@tikvahethsport     @kidusyoftahe