ፈረሰኞቹ ድል አድርገዋል !
በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአዳማ ከተማ ዳንኤል ደምሴ አስቆጥሯል።
የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ኦሮ አጎሮ በውድድር አመቱ አስራ ስምንተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን አርባ ሁለት በማድረስ መሪነቱን አጠናክሮ ሲቀጥል አዳማ ከተማ በሀያ አራት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚገናኙ ይሆናል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe

" የተሻለው ቡድን አሸንፏል "
የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ቡድናቸው በብራይተን ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ፍራንክ ላምፓርድ በአስተያየታቸውም " የተሻለው ቡድን አሸንፏል እነሱ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር ይችሉ ነበር ፣ ለተጨዋቾቹ በግል የምነግራቸው ነገር ይኖራል ፣ በጣም ተበሳጭቻለሁ።" ብለዋል።
አሰልጣኙ ቀጥለውም " እንደ ቡድን ጥሩ አልነበርንም በበቂ ሁኔታም አልተፋለምንም ፣ ማክሰኞ ትልቅ ጨዋታ አለብን ፣ መበሳጨት ፋይዳ የለውም ግን ለምን እንደተሸነፍን መረዳት አለብን ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ተጠናቀቀ | ናፖሊ 0-0 ሄላስ ቬሮና
- ናፖሊ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ ላዝዮ በአስራ አራት ነጥቦች ርቆ ሊጉን በበላይነት እየመራ ይገኛል።
- የአሰልጣኝ ሉሲያኖ ስፓሌቲው ስብስብ በውድድር አመቱ #ሶስተኛ የሊግ ጨዋታውን አቻ ወጥቷል።
- የሊጉ መሪ ናፖሊ በቀጣይ ከጁቬንቱስ ጋር ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብሩን አልያንዝ ስታዲየም ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !
ማንችስተር ሲቲ ከ ሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ሰላሳ አንደኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x እና ጆን ስቶንስ ሲያስቆጥሩ የሌስተር ሲቲን ግብ ኢሂናች ከመረብ አሳርፏል።
ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ ሁለተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባ በማድረስ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #ሶስት ማጥበብ ችሏል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ወሳኝ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

" ግራም ፖተርን አመሰግናለሁ " ዲ ዘርቢ
ቼልሲን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያስመዘገቡት ብራይተኖች አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በንግግራቸውም " ግራም ፖተርን አመሰግናለሁ አሁን በጣም ጥሩ እና ጠንካራ ቡድን አግኝቻለሁ ፣ እዚህ የእኔን አሻራ ለማስቀመጥ እየሞከርኩ ነው።
በውጤቱ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ነገር ግን አሁን ቀጣይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ስላለብን የኤፌ ካፕ ጨዋታ ማሰብ ጀምሬያለሁ ፣ የዛሬው አልፏል ትኩረታችን እሱ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

" ባየር ሙኒክም ተሸንፏል "
የሌስተር ሲቲው አሰልጣኝ ዲን ስሚዝ በማንችስተር ሲቲ ከደረሰባቸው ሽንፈት በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
" ባየር ሙኒክም ወደዚህ መጥቶ 3ለ0 ተሸንፏል " የሚሉት አሰልጣኙ " ከእረፍት በኋላ ጥሩ ነበርን በውጤቱ ቅር ብሎኛል ነገር ግን በአለም ምርጥ ቡድን መሸነፍ መጨረሻው አይደለም።"ሲሉ ተደምጠዋል።

" ለአርሰናሉ የፍፃሜ ጨዋታ ይጠቅመናል "
የማንችስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ፔፕ ጋርድዮላ ቡድናቸው ሌስተር ሲቲን ካሸነፈበት የሊግ ጨዋታ በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ፔፕ ጋርድዮላ በንግግራቸውም " አርሰናል እስካሁን ባለው የውድድር አመት የማይታመን ጉዞ አድርጓል ፣ ከዚህ በኋላ ብዙ ነጥብ የሚጥል አይመስለኝም።
በሚቀጥለው መርሐግብር ከእነሱ ጋር ለምናደርገው የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ማሸነፋችን አስፈላጊ ነው ፣ ያንን ጨዋታ ከተሸነፍን ሁሉም ሊያበቃ ይችላል።
ሀላንድ ሁሉንም ሪኮርዶች እንዲሰብር እፈልጋለሁ ፣ እሱ ሁሉንም ግቦች ሲያስቆጥር እኛንም ያግዘናል እኔ እንደማስበው እሱ ዋንጫዎችን ማሸነፍም ይፈልጋል።"ሲሉ ተደምጠዋል።

ፒኤስጂ ድል አድርጓል !
በፈረንሳይ ሊግ የሰላሳ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፒኤስጂ ከ ሌንስ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ ፣ ሊዮኔል ሜሲ እና ቪቲንሀ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
የፒኤስጂው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በውድድር አመቱ #ሀያኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
አርጀንቲናዊው የፒኤስጂ የፊት መስመር ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በውድድር አመቱ አስራ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ አሳርፏል።
ፒኤስጂ ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን ሰባ ሁለት በማድረስ መሪነቱን ሲያጠናክር ሌንስ በስልሳ ሶስት ነጥቦች #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ፒኤስጂ ከ አንገርስ እንዲሁም ሌንስ ከሞናኮ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

ሪያል ማድሪድ አሸንፏል !
ሪያል ማድሪድ ካዲዝ ጋር ያደረገውን የሀያ ዘጠነኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
ለሪያል ማድሪድ ግቦችን ማርኮ አሴንስዮ እና ናቾ ፈርናንዴዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።
ሎስ ብላንኮዎቹ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይ ከ ሴልታቪጐ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

ዋናው የስፖርት አልባሳት የንግድ ምልክት እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን ይላል።
በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የደስታ ፣ የጤና እና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።
ዋናው ወደ ፊት . . . . .
ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

#ትንሳኤ
እንኳን አደረሳችሁ !
ውድ የክርስትና እምነት ተከታይ የቲክቫህ አባላት በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
በዓሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ይሆን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስናከብር ፤ የተቸገሩ ወገኖቻንን አለንላችሁ በማለት ፣ የወደቁትን በማንሳት ፣ በሀዘን ላይ ያሉ ወገኖችን በማፅናናት፣ ከክፉ ድርጊትና ሀሳብ ርቀን ሊሆን ይገባል።
የሰላም፣ የመተሳሰብና የበረከት በዓል ያድርግልን !
ፈጣሪ ሀገራችን ሰላም ያድርግልን !
መልካም በዓል !
#TikvahFamily❤️
@tikvahethiopia

ተጠባቂ የዛሬ መርሐ ግብሮች !
9:00 ኢትዮጵያ መድን ከ ወላይታ ድቻ
10:00 ዌስትሀም ከ አርሰናል
12:00 መቻል ከ ፋሲል ከነማ
12:30 ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ማንችስተር ዩናይትድ
11:15 ሄታፌ ከ ባርሴሎና
1:00 ሳሱሎ ከ ጁቬንቱስ
3:45 ሮማ ከ ዩዲኒዜ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
9:00 ኢትዮጵያ መድን ከ ወላይታ ድቻ
10:00 ዌስትሀም ከ አርሰናል
12:00 መቻል ከ ፋሲል ከነማ
12:30 ኖቲንግሀም ፎረስት ከ ማንችስተር ዩናይትድ
11:15 ሄታፌ ከ ባርሴሎና
1:00 ሳሱሎ ከ ጁቬንቱስ
3:45 ሮማ ከ ዩዲኒዜ
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የኢንተር ሚላን አስከፊ ጉዞ ቀጥሏል !
በጣልያን ሴርያ ደካማ " ወቅታዊ አቋም " ላይ የሚገኙት ኢንተር ሚላኖች ተከታታይ ያደረጓቸውን የሴርያው ጨዋታዎች ማሸነፍ ሳይችሉ ቀርተዋል።
ኢንተሮች በሜዳቸው ያደረጓቸውን ሶስት ተከታታይ ጨዋታ ተሸንፈው ግብ ማስቆጠር ሳይችሉ ሲቀርም በክለቡ ታሪክ #ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።
ኢንተር ሚላን በጣልያን ሴርያ የደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ አምስተኛ ደረጃን ይዘው ይገኛሉ።

ሳድዮ ማኔ መቼ ይመለሳል ?
ሴኔጋላዊው የባየር ሙኒክ የፊት መስመር ተጫዋች ሳድዮ ማኔ ከቡድን አጋሩ ሊሮይ ሳኔ ጋር በፈጠረው አለመግባባት በክለቡ ቅጣት ተላልፎበት ይገኛል።
የሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ለሻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ከዛሬ ጀምሮ ልምምዳቸውን ሲያከናውኑ ሳድዮ ማኔ ወደ ቡድን ስብስብ እንደሚመለስ ተገልጿል።
በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ የሰጡት አሰልጣኙ ቶማስ ቱሄል " ሳድዮ ማኔ ይቅርታ ጠይቋል ፣ ከቡድኑ ጋር በዛሬው ዕለት ልምምድ ይሰራል " ሲሉ ተደምጠዋል።

#PremierLeague 🇬🇬
የተወዳጁ የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ 2023/24 የውድድር ዘመን የመካሄጃ ጊዜያት አስመልክቶ አወዳዳሪው አካል ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት :-
ሰኔ 8/2015 :- የውድድር ዓመቱ መርሐ ግብር ይፋ ይደረጋል።
ነሐሴ 6/2015 :- የአዲሱ ውድድር ዓመት ይጀምራል።
ጥር 4-11/2016 :- የአዲሱ የውድድር ዓመት የመጀመሪያ ዙር እረፍት
ግንቦት 11/2016 :- የ 2023/24 የውድድር ዘመን በገባደጃ ቀን መሆኑ ታውቋል።

" የአርሰናል ቀጣይ ጨዋታዎች ወሳኝ ናቸው "
የመድፈኞቹ የቀድሞ ኮትዲቯራዊው የመሐል ተከላካይ ኮሎ ቱሬ ቀጣዮቹ ሁለት ጨዋታዎች ለአርሰናል ወሳኝ መርሐ ግብሮች መሆናቸውን ገልጿል።
" አርሰናል ከማንችስተር ሲቲ ጋር ጨዋታቸውን ከማድረጋቸው በፊት ዌስትሀም እና ሳውዝሀምፕተን ያገኛሉ ፣ እነዚህ ሁለት ጨዋታች እንደ ሲቲ ጨዋታ ሁሉ ወሳኝ ናቸው።
አርሰናል ዋንጫውን ባያሸንፍ እንኳ ሚኬል አርቴታ አስደናቂ ስራን ሰርቷል ፣ ማንም ሰው አሁን የደረሰበትን ደረጃ ይደርሳል ብሎ ያሰበ የለም " በማለት ተናግሯል።