TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
41' ቼልሲ 1-1 ብራይተን

ጋላገር ዌልቤክ

41' ኤቨርተን 1-1 ፉልሀም

41 ' ሳውዝሀምፕተን 0-0 ክሪስታል ፓላስ

25' ቶተንሀም 1-0 በርንማውዝ

    ሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
እረፍት | ቼልሲ 1-1 ብራይተን

ጋላገር  ዌልቤክ

እረፍት | ኤቨርተን 1-1 ፉልሀም

ማክኔል ሪድ

እረፍት | ሳውዝሀምፕተን 0-0 ክሪስታል ፓላስ

40' ቶተንሀም 1-0 በርንማውዝ

    ሰን

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
50 ' ቼልሲ 1-1 ብራይተን

  ጋላገር         ዌልቤክ

50 ' ኤቨርተን 1-1 ፉልሀም

    ማክኔል          ሪድ

50 ' ሳውዝሀምፕተን 0-1 ክሪስታል ፓላስ

እረፍት | ቶተንሀም 1-1 በርንማውዝ

    ሰን ቪና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
68' ቼልሲ 1-2 ብራይተን

  ጋላገር         ዌልቤክ

68' ኤቨርተን 1-3 ፉልሀም

    ማክኔል          ሪድ

68 ' ሳውዝሀምፕተን 0-2 ክሪስታል ፓላስ

51' ቶተንሀም 1-2 በርንማውዝ

        ሰን            ቪና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባየር ሙኒክ እና ዶርትመንድ ነጥብ ጥለዋል !

የቡንደስሊጋው መሪ ባየር ሙኒክ ከሆፌንሄም ጋር ያደረጉትን የሀያ ስምንተኛ ሳምንት መርሐግብር 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችሏል።

የባየር ሙኒክን ግብ ፓቫርድ ሲያስቆጥር ለሆፌንሄም ክራማሪች የአቻነቷን ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ቦርስያ ዶርትመንድ ከስቱትጋርት ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐግብር በመጨረሻ ደቂቃ ግብ ተቆጥሮበት 3ለ3 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የቦርስያ ዶርትመንድን ግቦች ሰባስቲያን ሀለር ፣ ዶንየል ማለን እና ሬና ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ባየር ሙኒክ ቡንደስሊጋውን በሀምሳ ዘጠኝ ነጥብ ሲመራው ቦርስያ ዶርትመንድ በሀምሳ ሰባት ነጥብ ይከተላል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ ከ ሜንዝ እንዲሁም ቦርስያ ዶርትመንድ ከ ፍራንክፈርት የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታ አሰላለፍ !

1:30 ማንችስተር ሲቲ ከ ሌስተር ሲቲ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
78' ቼልሲ 1-2 ብራይተን

  ጋላገር         ዌልቤክ
ኢንሲሶ

78' ኤቨርተን 1-3 ፉልሀም

    ማክኔል          ሪድ

78 ' ሳውዝሀምፕተን 0-2 ክሪስታል ፓላስ

ኢዜ

65' ቶተንሀም 1-2 በርንማውዝ

        ሰን            ቪና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
88' ቼልሲ 1-2 ብራይተን

  ጋላገር         ዌልቤክ
                          ኢንሲሶ

88' ኤቨርተን 1-3 ፉልሀም

    ማክኔል          ሪድ

88 ' ሳውዝሀምፕተን 0-2 ክሪስታል ፓላስ

                              ኢዜ

71' ቶተንሀም 1-2 በርንማውዝ

        ሰን            ቪና

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ ሽንፈት አስተናግዷል !

በአሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ የሚመራው የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ከብራይተን ጋር የሊግ ጨዋታውን አድርጎ 2ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ዳኒ ዌልቤክ እና ኢንሲሶ ሲያስቆጥሩ የቼልሲን ብቸኛ ግብ ጋላገር ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ በተከታታይ ያደረጋቸውን ያለፉት አምስት የሊግ መርሐግብሮች ማሸነፍ አልቻለም።

ቼልሲ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ዘጠኝ ነጥቦችን በመሰብሰብ አስራ አንደኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ብራይተን በአርባ ዘጠኝ ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቼልሲ ከ ብሬንትፎርድ እንዲሁም ብራይተን ከ ኖቲንግሀም ፎረስት የሚጫወቱ ይሆናል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረጉ ሌሎች የሊጉ መርሐ ግብሮች ክሪስታል ፓላስ ፣ ዎልቭስ እና ፉልሀም ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ ችለዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ቶተንሀም 2-3 በርንማውዝ

        ሰን            ቪና
ዳንጁማ ሶላንኬ
ኦታር

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
5' ማንችስተር ሲቲ 1-0 ሌስተር ሲቲ

ስቶንስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
13' ማንችስተር ሲቲ 2-0 ሌስተር ሲቲ

      ስቶንስ
ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ፈረሰኞቹ ድል አድርገዋል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አስራ ዘጠነኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች አቤል ያለው እና እስማኤል ኦሮ አጎሮ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለአዳማ ከተማ ዳንኤል ደምሴ አስቆጥሯል።

የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር ተጨዋች እስማኤል ኦሮ አጎሮ በውድድር አመቱ አስራ ስምንተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን አርባ ሁለት በማድረስ መሪነቱን አጠናክሮ ሲቀጥል አዳማ ከተማ በሀያ አራት ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
  25 ' ማንችስተር ሲቲ 3-0 ሌስተር ሲቲ

      ስቶንስ
      ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" የተሻለው ቡድን አሸንፏል "

የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዋና አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ቡድናቸው በብራይተን ከደረሰበት ሽንፈት በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

ፍራንክ ላምፓርድ በአስተያየታቸውም " የተሻለው ቡድን አሸንፏል እነሱ ተጨማሪ ግቦችን ማስቆጠር ይችሉ ነበር ፣ ለተጨዋቾቹ በግል የምነግራቸው ነገር ይኖራል ፣ በጣም ተበሳጭቻለሁ።" ብለዋል።

አሰልጣኙ ቀጥለውም " እንደ ቡድን ጥሩ አልነበርንም በበቂ ሁኔታም አልተፋለምንም ፣ ማክሰኞ ትልቅ ጨዋታ አለብን ፣ መበሳጨት ፋይዳ የለውም ግን ለምን እንደተሸነፍን መረዳት አለብን ።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ናፖሊ 0-0 ሄላስ ቬሮና

- ናፖሊ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ ላዝዮ በአስራ አራት ነጥቦች ርቆ ሊጉን በበላይነት እየመራ ይገኛል።

- የአሰልጣኝ ሉሲያኖ ስፓሌቲው ስብስብ በውድድር አመቱ #ሶስተኛ የሊግ ጨዋታውን አቻ ወጥቷል።

- የሊጉ መሪ ናፖሊ በቀጣይ ከጁቬንቱስ ጋር ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብሩን አልያንዝ ስታዲየም ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
75' ማንችስተር ሲቲ 3-1 ሌስተር ሲቲ

      ስቶንስ ኢሂናቾ
      ሀላንድ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

ማንችስተር ሲቲ ከ ሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን ሰላሳ አንደኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ 2x እና ጆን ስቶንስ ሲያስቆጥሩ የሌስተር ሲቲን ግብ ኢሂናች ከመረብ አሳርፏል።

ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ ሁለተኛ የፕርሚየር ሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባ በማድረስ ከሊጉ መሪ አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #ሶስት ማጥበብ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከሊጉ መሪ አርሰናል ጋር ወሳኝ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ግራም ፖተርን አመሰግናለሁ " ዲ ዘርቢ

ቼልሲን በማሸነፍ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያስመዘገቡት ብራይተኖች አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ ከጨዋታው በኋላ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ሮቤርቶ ዲ ዘርቢ በንግግራቸውም " ግራም ፖተርን አመሰግናለሁ አሁን በጣም ጥሩ እና ጠንካራ ቡድን አግኝቻለሁ ፣ እዚህ የእኔን አሻራ ለማስቀመጥ እየሞከርኩ ነው።

በውጤቱ በጣም ተደስቻለሁ ፣ ነገር ግን አሁን ቀጣይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ስላለብን የኤፌ ካፕ ጨዋታ ማሰብ ጀምሬያለሁ ፣ የዛሬው አልፏል ትኩረታችን እሱ ነው።"ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe