TIKVAH-SPORT
258K subscribers
51.3K photos
1.48K videos
5 files
3.38K links
Download Telegram
🏆CHAMPION 🏅

አስቀድሞ የኢትዮጵያ ሴቶች ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ መሆናቸውን ያረጋገጡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች እግር ኳስ ክለብ በዛሬው ዕለት ዋንጫውን በይፋ በመረከብ አንስተዋል ።

ሻምፒዮኖቹ ሀገራችንን በመወከል በሴካፋ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ ተሳታፊ ሲሆኑ በመጪው ቀናት ዝግጅታቸውን ይጀምራሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአፍሪካ ዋንጫው የጊዜ ለውጥ ተደረገበት ! በቀጣይ በኮትዲቯር አስተናጋጅነት የሚደረገው የ 2023 የአፍሪካ ዋንጫ የጊዜ ለውጥ መደረጉ ይፋ ተደርጓል ። በወርሀ ሰኔ እና ሐምሌ በሀገረ ኮትዲቯር ያለው ከባድ የዝናብ የአየር ሁኔታ ለቀኑ መለወጥ ምክንያት ሲሆን ቀጣዩ የአፍሪካ ዋንጫ ከጥር እስከ የካቲት 2016 ዓ.ም ውስጥ እንደሚደረግ ይፋ ሆኗል ። ሀገራችን ኢትዮጵያ ለኮትዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ…
የዋልያዎቹ ጨዋታ ሊራዘም ነው ?

የኮትዲቯር 2023 አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ወደፊት መራዘሙን ተከትሎ ለአፍሪካ ዋንጫው የሚደረጉት የምድቡ ሶስተኛ እና አራተኛ የማጣሪያ ጨዋታዎች ወደ ሌላ ጊዜ ሊዘዋወሩ እንደሆነ ተገልጿል ።

ምድብ አራትን እየመሩ የሚገኙት ዋልያዎቹ መስከረም ወር 2015 ዓ.ም ላይ ከጊኒ አቻቸው ጋር በሜዳቸው እና ከሜዳቸው ውጪ ሊያደርጓቸው የነበሩት መርሐ ግብሮች ወደ መጋቢት 2015 ዓ.ም የቀን ለውጥ ሊደረግበት መሆኑ ተዘግቧል ።

ጨዋታዎቹ ለሌላ ጊዜ እንዲዘዋወሩ የቀረበው ሀሳብ አህጉሪቱን በኳታሩ አለም ዋንጫ የሚወክሉ ብሔራዊ ቡድኖች በበቂ ሁኔታ እንዲዘጋጁ ታሳቢም ያደረገ ነው ተብሎ ተነግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ሽንፈትን አስተናግደዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በቅድመ ውድድር ዝግጅት የአቋም መፈተሻ ጨዋታ የመጀመሪያ ሽንፈት እንዳስተናገዱ ተገልጿል ።

በለንደን ኮሎኒ በዝግ በተካሄደ ጨዋታ ብሬንትፎርድን የገጠሙት አርሰናሎች 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መሸነፋቸው ተነግሯል ።

ለአርሰናል ኤዲ ኒኪታህ ግብ ሲያስቆጥር ብራያን ሙቤሞ እና ራያን ትሬቪት የብሬንትፎርድን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩናይትዶች ድል ቀንቷቸዋል !

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች ከደቂቃዎች በፊት ባደረጉት የወዳጅነት ጨዋታ ማሸነፋቸው ተገልጿል ።

በዩናይትድ የልምምድ ሜዳ ካሪንግተን በዝግ በተካሄደው ጨዋታ ሬክስሀምን የገጠሙት ቀያይ ሴጣኖቹ 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል ።

አዲሱ የክለቡ ፈራሚ ክርስቲያን ኤሪክሰን አንድ ግብ ማስቆጠር ሲችል ቀሪዎቹን አማድ ዲያሎ ፣ ቴሌስ እና ጋርናቾ ከመረብ አሳርፈዋል ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው ባይሰለፍም የሁለቱን ቡድኖች ጨዋታ በቦታው ተገኝቶ መከታተሉ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የአትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች የሮናልዶን ዝውውር ተቃወሙ ! የሰላሳ ሰባት አመቱ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ማንችስተር ዩናይትድን በመልቀቅ ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ክለብ ማቅናት እንደሚፈልግ መግለፁ ይታወሳል ። ፖርቹጋላዊው ሰሞኑን ወደ አትሌቲኮ ማድሪድ ሊዘዋወር ይችላል የሚሉ ዜናዎች ከወጡ በኋላ የክለቡ ደጋፊዎች ብስጭታቸውን እየገለፁ ይገኛሉ ። የአትሌቲኮ ደጋፊዎች በድህረ ገፅ አድማ መጀመራቸው ሲነገር…
" CR 7 NOT WELCOME "

የላሊጋው ክለብ አትሌቲኮ ማድሪድ ደጋፊዎች በክርስቲያኖ ሮናልዶ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በአሁን ሰዓት እያካሂዱት ባለው የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ገልፀዋል ።

ደጋፊዎቹ በፅሁፍ ይዘውት በገቡት ፅሁፍ " CR 7 NOT WELCOME " በማለት ወደ ክለባቸው እንዲመጣ እንደማይፈልጉ በመልዕክታቸው አሳይተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" በሰላም ገብተዋል "

በዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮናው ከዓለም 2ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።

ልዑካን ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቀባበል አድርገዋል።

ነገ በተመረጡ የመዲናችን አካባቢዎች ህዝቡ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያ ከፍ ላደረገው የአትሌቲክስ ቡድን አድናቆት በመግለፅ አቀባበል ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።

#ENA

@tikvahethiopia
ዋናው ትጥቅ አምራች ድርጅት

ምን አይነት ማልያ ፈልገው ይሆን ? ለእይታ ምቹ ለአይን ሳቢ በሆነው ቢሯችን መጥተው አማርጠው አዘው ያሰራሉ ።

በፈለጉት ምርጫ በተመጣጣኝ ዋጋ 500 ብር ብቻ ከፍለው የወደዱትን መለያ በፍጥነት እና በጥራት ያገኛሉ ።

የፈለጉትን ስፖርታዊ ትጥቆች ዋናው ጋር መጥተው አያጡም ይምጡ እና ይጎብኙን !

📞 ይደውሉ :- 📱0910 851 535
📱0913 586 742

ቻናላችን :- https://t.iss.one/wanawsportwear

📌 አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት
ዋልያዎቹ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ !

በሀገር ውስጥ የሚጫወቱ ተጫዋቾች ብቻ በሚካፈሉበት የቻን አፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ዋልያው የቅድመ ማጣርያ #የመልስ ጨዋታውን ከ ደቡብ ሱዳን ጋር ዛሬ ከቀኑ 10:00 ሰዓት ያከናውናል ።

በታንዛኒያ ቤንጃሚን ማክፓ በሚደረገው የመልስ መርሐ ግብር ዋልያው ድል የሚቀናው ከሆነ የመጨረሻ ጨዋታውን ከ ሩዋንዳ ጋር የሚያካሂድ ይሆናል ።

ድል ለብሔራዊ ቡድናችን 🇪🇹 🇪🇹 🇪🇹

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የኳታር ፍትህ ሚንስቴር ማስጠንቀቂያ አውጥቷል !

የኳታር ፍትህ ሚንስቴር በትላንትናው ዕለት ባወጣው መግለጫ የአለም ዋንጫውን ትኬቶች ያለ ፊፋ ፈቃድ መገበያየት እንደማይቻል ገልጿል ።

ሚንስቴሩ ትኬቶቹን በፊፋ ዕውቅና ከተሰጣቸው አካላት ውጪ የሚገዛ ፣ የሚሸጥ ወይም የሚለውጥ ማንኛውም ግለሰብ እስከ 250,000 የኳታር ሪያል ቅጣት እንደሚጣልበት አስታውቋል ።

የኳታሩ 2022 አለም ዋንጫ ሊጀመር 116 ቀናት ብቻ ሲቀሩት ብዙ ደጋፊዎች በቦታው ተገኝተው መከታተል እንደሚፈልጉ ይታወቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#ኢትዮጵያ 🇪🇹

የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድኑ ካረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል አንስቶ በማርሽ ባንድ የታጀበ ደማቅ አቀባበል እየተደረገለት ይገኛል ።

በአቀባበሉ ላይ የልዑካን ቡድኑ ቤተሰቦች ፣ ክለቦች እና ፌደሬሽኖች ባረፈበት ስካይ ላይት ሆቴል የአበባ ጉንጉን አበርክተዋል ።

ቡድኑ ከዚህ መርሃ ግብር ቀጥሎ ካረፈበት ስካይላይት ሆቴል ተነስቶ በእስጢፋኖስ ፣ 4 ኪሎ ፣ ፒያሳ ፣ ቸርችል አድርጎ በለገሀር ወደ መስቀል አደባባይ በመሄድ ደስታቸውን ከህዝቡ ጋር የሚገልፁ ይሆናል ።

አቀባበሉን በቀጥታ ለመከታተል :-

√ https://fb.watch/exU4uhyw7a/

√ https://fb.watch/exUa71b-kn/

√ https://fb.watch/exUpkNl3N0/

ምስል :- ከማህበራዊ ሚድያ እና #EPA የተወሰዱ

@tikvahethsport @kidusyoftahe