TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
35' ማንችስተር ሲቲ 2-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ

√ ጀዳን ሳንቾ ባለፉት አምስት የ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በአራት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ አድርጓል ።

ሳንቾ ሁለት ጎሎችን ከመረብ ሲያሳርፍ በተቃራኒው ሁለት ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝተዋል !

የ ስፔን ላሊጋ የ ሀያ ሰባተኛው ሳምንት ጨዋታ በ ስታዲዮ ማኑኤል ማርቲኔዝ ቫልቬርዶ ቀጥሎ ሲካሄድ ባርሴሎና ከ ኤልቼ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

የ ባርሴሎናን የማሸነፊያ ግቦች ፌራን ቶሬስ እና ሜምፊስ ዴፓይ ሲያስቆጥሩ የ ኤልቼን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ፊደል ቻቬስ አስቆጥሯል ።

ኒኮ ጎንዛሌዝ ዛሬ ቢጫ ካርድ መመልከቱን ተከትሎ ከ ኦሳሱና ጋር የሚደረገው የ ላሊጋ ጨዋታ ላይ የማይሰለፍ ይሆናል ።

ጆርዲ አልባ ለ ሀምሳ አምስተኛ ጊዜ ለ ባርሴሎና ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል ።

ከ 2012/13 የውድድር አመት በኋላ ጆርዲ አልባ ብዙ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በ አውሮፓ ታላላቅ አምስት ሊጎች ላይ ያቀበለ ቀዳሚው ተከላካይ ነው ።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ባርሴሎና በ 48 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኤልቼ በ 29 ነጥብ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።

@tikvahethsport @solomonayalew9
እረፍት | ማንችስተር ሲቲ 2-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
50 ' ማንችስተር ሲቲ 2-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
62 ' ማንችስተር ሲቲ 2-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
68 ' ማንችስተር ሲቲ 3-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ
ማህሬዝ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
78 ' ማንችስተር ሲቲ 3-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ
ማህሬዝ

√ ሪያድ ማህሬዝ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ #ሀያ አድርሷል ።

√ ማህሬዝ በ ፕርሚየር ሊጉ ዘጠነኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
92 ' ማንችስተር ሲቲ 4-1 ማንችስተር ዩናይትድ

⚽️ ዴ ብሩይን ሳንቾ
ማህሬዝ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ማንችስተር ሲቲዎች መሪነታቸውን አጠናክረዋል !

የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ ሀያ ስምንተኛው ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ በ ኢትሀድ ቀጥሎ ሲካሄድ ማንችስተር ሲቲ ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል ።

የ ማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ሪያድ ማህሬዝ እና ኬቨን ዴ ብሩይን አስቆጥረዋል ።

የ ማንችስተር ዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ ጄዳን ሳንቾ ከመረብ አሳርፏል ።

ብራዚላዊው የ ማንችስተር ዩናይትድ አማካይ ፍሬድ 150ኛ ጨዋታውን ለ ቀያዮቹ ሴጣኖች አከናውኗል ።

ፖል ፖግባ ለ ዘጠነኛ ጊዜ በዘንድሮ የውድድር አመት በ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል ።

ኬቨን ዴ ብሩይን በ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከ ሀምሳ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ አራተኛ ቤልጅዬማዊ ተጫዋች ሆኗል ።

ኬቨን ዴ ብሩይን ለ ማንችስተር ሲቲ በ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ከ ሀምሳ በላይ ግቦችን ያስቆጠረ ስምተኛው ተጫዋች መሆን ችሏል ።

ፖል ፖግባ በድምሩ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ላይ ለ ሰላሳ ስምንተኛ ጊዜ ለግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ አቀብሏል ።

ኢልካይ ጉንዶጋን ለ ማንችስተር ሲቲ ዛሬ አንድ መቶ ሀምሳኛ ጨዋታውን አከናውኗል ።

ሪያድ ማህሬዝ በ ማንችስተር ዩናይትድ ላይ የመጀመሪያ የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግቡን አስቆጥሯል ።

በርናንዶ ሲልቫ ለ ማንችስተር ሲቲ ባደረጋችው የመጨረሻ ስምንት የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ላይ በ አምስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን አድርጓል ።

የዛሬውን ውጤት ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ በ 69 ነጥብ ሊጉን መምራቱን ሲቀጥል ማንችስተር ዩናይትድ በ 47 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ለማንችስተር ዩናይትድ መጫወት የማይገባቸው ተጫዋቾች አሉ "

የቀድሞ የ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋች ሮይ ኪን ቡድኑ ያጋጠመውን ሽንፈት ተከትሎ በ ቡድኑ ተጫዋቾች ላይ ያለውን ብስጭት ገልጿል ።

ሮይ ኪን ሲናገር " ከዚህ በኋላ ለማንቸስተር ዩናይትድ መጫወት #የማይገባቸው አምስት ወይም ስድስት ተጫዋቾች አሉ " ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አያክስ በአስደናቂ ጉዟቸው ቀጥለዋል !

በ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመሩት የ ሆላንድ ሊግ መሪ አያክሶች አስደናቂ የሆነ ጉዟቸውን ቀጥለዋል ።

አያክስ በዘንድሮ የውድድር ዓመት በሊጉ ባደረጓቸው ሀያ አምስት ጨዋታዎች ሰባ አራት ጎሎችን በተጋጣሚዎቻቸው መረብ ላይ ሲያሳርፉ በተቃራኒው #ዘጠኝ ግቦች ብቻ ተቆጥሮባቸዋል ።

አያክስ ከተቀናቃኛቸው ፒኤስቪ በ #ሁለት ነጥቦች ርቀው ሊጉን በ #ስልሳ ነጥቦች እየመሩ ይገኛሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ፖርቹጋል ይገኛል !

ፖርቹጋላዊው የ ማንችስተር ዩናይትድ ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ትላንት ምሽት ማንችስተር ሲቲን ከገጠመው የ ቀያይ ሴጣኖቹ ስብስብ ውጪ መደረጉ ይታወሳል ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ካጋጠመው ጉዳት በኋላ በቀጥታ ከጨዋታ ቀን አስቀድሞ ወደ ፖርቹጋላል ማቅናቱ የተገለፀ ሲሆን በሞቃታማ የአየር ሁኔታ ከጉዳቱ በፍጥነት ለማገገም እንደሚረዳው ወደ ስፍራው ለማቅናቱ በምክንያትነት ቀርቧል ።

የ ፖርቹጋላዊው ኮከብ ወደ ሀገሩ ማቅናት ግን በ ቀያዮቹ ሴጣኖች መልበሻ ክፍል ውስጥ ማነጋገሩ እና አንዳንድ የክለቡ ተጫዋችን ደስተኛ #አለማድረጉ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ባሳለፈው ከባድ ጊዜ ከጎኑ መሆናችን ቡካዮ ሳካን አጠንክሮታል "

የ ሰሜን ለንደን ክለቡ አርሰናል ዋትፎርድን ባሸነፈበት ጨዋታ ላይ ቡካዮ ሳካ ድንቅ እንቅስቃሴን ካደረገ በኋላ ሚኬል አርቴታ ያሳለፋቸው ከባድ ጊዜያት ለ እንግሊዛዊው ኮከብ እንደጠቀመው ገልፀዋል ።

ሜኪል አርቴታ ሲናገር " እንደማስበው በ አውሮፓ ዋንጫ ላይ የመለያያ ፍፁም ቅጣት ምት መሳቱ ለ ቡካዮ ሳካ ያጠነከረው ይመስለኛል ፤ ባሳለፈው ከባድ ጊዜ ከጎኑ መሆናችን ቡካዮ ሳካን አጠንክሮታል " ሲል ተደምጧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ጆርዲ ክራይፍ የ ባርሴሎና ቆይታ ?

የ ባርሴሎናው ሆላንዳዊው የዝውውር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጆርዲ ክራይፍ ከ አዲሱ ከ ካታላኑ ክለብ አሰልጣኝ ዣቪ ጋር በጥር የዝውውር መስኮት ስኬታማ ዝውውሮችን ፈፅመዋል ።

አያክስ ከ ማርክ ኦቨር ማርስ ጋር መለያየቱን ተከትሎ ጆርዲ ክራይፍን አዲሱ የስፖርቲንግ ዳይሬክተራቸው አድርገው ለመሾም እንቅስቃሴን ቢያደርጉም ጆርዲ ክራይፍ በ ባርሴሎና የመቆየት ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሀላንድ ወደ ማንችስተር ሲቲ ወይስ ሪያል ማድሪድ ?

የ ቦርሲያ ዶርትሙንዱ የፊት መስመር ተጫዋች ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ በታላላቆቹ ክለቦች ማንችስተር ሲቲ እና ሪያል ማድሪድ መፈለጉን ቀጥሏል ።

ሪያል ማድሪድ በ ክረምቱ የዝውውር መስኮት ኪሊያን ምባፔን ካስፈረሙ በኋላ #በቀጣዩ የውድድር አመት ሀላንድን የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተዘግቧል ።

ማንችስተር ሲቲዎች በተቃራኒው በክረምቱ የዝውውር መስኮት የ ሀያ አንድ አመቱን የ ፊት መስመር ተጫዋች ማስፈረም ሲፈልጉ ሪያል ማድሪድን ጫና ውስጥ መክተቱ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ዩሀን ማታ የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ ?

የ ማንችስተር ዩናይትዱ ስፔናዊው የአጥቂ አማካይ ዩሀን ማታ በውድድር አመቱ መጨረሻ ከ ቀያዮቹ ሴጣኖች ጋር ያለው ኮንትራት ይጠናቀቃል ።

ስፔናዊው የ ሰላሳ ሶስት አመቱ ተጫዋቾች ከ ቀያዮቹ ሴጣኖች ጋር ያለው ኮንትራት ሲጠናቀቅ ከ እንግሊዝ ውጪ ላለ ክለብ የመጫወት ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል ።

ይሄ ተከትሎ የተለያዩ የ ስፔን ላሊጋ ተወዳዳሪ ክለቦች የ ሰላሳ ሶስት አመቱን የ ማንችስተር ዩናይትድ ተጫዋቾችን የማስፈረም ፍላጎት አሳይተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋናው ትጥቅ አምራች ድርጅት

👔 ከትላልቅ የስፖርት ክለቦች ጀርባ ያለ የትጥቅ አምራች ድርጅት 👚

ለጤና ክለቦች እና ለክለቦች

ከ 20 ብዛት ጀምሮ ሙሉ ማሊያ (ማሊያ በ ቁምጣ) በ 400 መቶ ብር በ ጥራት እና በ ፍጥነት እናቀርባለን !

WANAW ወደ ፊት.......
በቅርብ ቀን

📍አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት ወረቀት ፊትለፊት

☎️ 0910 851 535 ☎️0913 586 742
የ ማርከስ ራሽፎርድ ቆይታ !

የ ማንችስተር ዩናይትዱ እንግሊዛዊው የፊት መስመር ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድ ከ ቀያዮቹ ሴጣኖች ጋር ያለው ኮንትራት በ 2023 የሚጠናቀቅ ይሆናል ።

ማርከስ ራሽፎርድ በ ማንችስተር ዩናይትድ በቂ የመሰለፍ እድልን አለመግኘቱን ተከትሎ ከ ቀያዮቹ ሴጣኖቹ ጋር ስለ መለያየት እያሰበ መሆኑ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ከ ፒኤስጂ !

የፊታችን ዕሮብ በጉጉት የሚጠበቀው የሁለቱ ቡድኖች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የመልስ ጨዋታ ኔዘርላንዳዊው የመሐል ዳኛ እንደሚመሩት ይፋ ሆኗል ።

ኔዘርላንዳዊው ዳኒ ማኪሌ ይህን ተጠባቂ ጨዋታ እንደሚመሩ ሲገለፅ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳንቲያጎ በርናቦ የሚያጨውቱት መርሐ ግብር ይሆናል ።

ከዚህ ቀደም ዳኒ ማኪሌ በሁለት አጋጣሚዎች የ ሪያል ማድሪድን ጨዋታ የመሩ ሲሆን ሎስ ብላንኮዎቹ አንዱን አሸንፈው በአንዱ አቻ ወጥተዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አዲሱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ?

የ አለም አቀፉ የእግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ በ ዩክሬን እና ራሺያ መካከል በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በሁለቱ ሀገር የሚገኙ የውጪ ሀገር ተጫዋቾች ኮንትራታቸውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲያቋርጡ የሚያስችሉ ፍቃድ ለመስጠት መዘጋጀቱ ተገልጿል ።

በ ሁለቱ ሀገራት ይጫወቱ የነበሩ ተጫዋቾችን ከክረምቱ የዝውውር መስኮት አስቀድሞ ፊፋ በ አውሮፓ የሚገኙ ክለቦች ተጫዋቾቹን ማስፈረም የሚችሉበትን ፍቃድ ሊሰጥ መሆኑ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @solomonayalew9
ሊቨርፑል ወሳኝ ተጫዋቾቹን ከጉዳት መልስ አጊኝቷል !

የ መርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ጀርመናዊ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ በሳምንቱ አጋማሽ ላይ ከሚያደርጉት የ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ አስቀድሞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ከጉዳት መልስ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል ።

የርገን ክሎፕ እንዳረጋገጡት ሮቤርቶ ፊርሚኒሆ ፣ ጆኤል ማቲፕ እና ቲያጎ አልካንትራ ልምምድ መጀመራቸውን ገልፀዋል ።

@tikvahethsport @solomonayalew9