TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
በ ትላንትናው ዕለት ከተካሄዱ የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች የተወሰዱ ምስሎች ከላይ ተያይዟል ።

ተጨማሪ ምስሎችን በ ኢንስታግራም :- https://www.instagram.com/p/CVPXf9KoQHk/?utm_medium=copy_link መመልከት ይችላሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሉሲዎቹ ወሳኝ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ !

የ ኢትዮጵያ ሴት ብሔራዊ ቡድናችን ለ ሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ወሳኝ የማጣርያ ጨዋታቸውን ዛሬ 10:00 ሰዓት ያካሂዳሉ ።

የ ዩጋንዳ አቻቸውን በ ሴንት ሜሪ ስታዲየም የሚገጥሙት ሉሲዎቹ የማሸነፍ ትልቅ ግምትን አግኝተዋል ።

ሉሲዎቹ በደርሶ መልስ ዩጋንዳን የሚያሸንፉ ከሆነ ለ አፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከ ደቡቡ ሱዳን እና ኬንያ አሸናፊ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል ።

መልካም ዕድል ለ ሉሲዎቹ 🇪🇹

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አይነኬው የ ቼልሲ ተጫዋች !

የ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ለ ድርድር ከማያቀርቧቸው ተጫዋቾች እና አይነኬ ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል ቀዳሚው ግብ ጠባቂያቸው መሆኑ ተገልጿል ።

ለ ክለቡ ቅርበት ያላቸው ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንደዘገቡት ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ ኤድዋርድ ሜንዲ በ ቼልሲ አይነኬ ከሚባሉ ቀዳሚ ተጫዋቾች መካከል ዋነኛው መሆኑ ተነግሮለታል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኑሪ ሳሂን ጫማውን ሰቀለ !

የቀድሞ የቱርክ ብሔራዊ ቡድን እና ቦርስያ ዶርትመንድ ተጫዋች ኑሪ ሳሂን በ 33 ዓመቱ ጫማውን መስቀሉን ይፋ አድርጓል ።

ኑሪ ሳሂን " ካሁን በኋላ እግር ኳስን አልጫወትም " ሲል ሲናገር በቀጣይ በ እግር ኳስ አሰልጣኝነት እንደምንመለከተው ተናግሯል ።

ኑሪ ሳሂን በ ሪያል ማድሪድ እና በ እንግሊዝ ለ ሊቨርፑል ተጫውቶ ማሳለፉ የሚታወስ ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድን ተሸለመች !

“ አብሮነት መሻል ነው ” በሚል መሪ ቃል ጥቅምት 6 ቀን 2014 ዓ.ም በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና በዚያው የሚኖሩ አፍሪካውያንንም ማቀራረብን ግቡ ያደረገው የታላቁ አፍሪካ ሩጫ ለሦስተኛ ጊዜ ተካሂዷል ፡፡

ከሩጫው ጎን ለጎን የአፍሪካ ኢምፓክት ሽልማት የተከናወነ ሲሆን ሽልማቱ የሚከናወነው ተሸላሚዎቹ በሚኖሩበት ማህበረሰብ ወይም ለትውልድ ሃገራቸው በስፖርት፣ በኪነጥበብ እና በፈጠራ ስራ የላቀ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አፍሪካውያን የሚበረከት ሲሆን በዘንድሮም ዓመት በስፖርት ዘርፍ በ ኦሎምፒክ ፣ በዓለም ሻምፒዮና ፣ በሃገር አቋራጭ ፣ በሌሎችም ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች የሃገሯን ሰንደቅ ዓላማ በተደጋጋሚ ጊዜ ከፍ ላደረገቸው እንቁዋ አትሌታችን ጥሩነሽ ዲባባ ተበርክቷል፡፡

#EAF

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ እንኳን ደስ አለሽ!

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኒውካስትል ከ አሰልጣኙ ጋር ተለያየ !

ኒውካስትል ዩናይትድ አሰልጣኝ ስቲቭ ብሩስ ጋር በ ስምምነት መለያየታቸውን አሳውቋል ።

ክለቡ በ ፕርሚየር ሊጉ አስራ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ በቀጣይ ግራም ጆንስ ቡድኑን በ ጊዜያዊነት እንደሚረከቡ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዩጋንዳ ከ ኢትዮጵያ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ የሴካፋ ተጋጣሚዋን አወቀች !

የ ሴቶች ከ 20 ዓመት በታች የ ሴካፋ ውድድር በ ዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከ ጥቅምት 18 - ህዳር 9 ድረስ የሚካሄድ ይሆናል ።

በዘንድሮ የ ሴካፋ ከ 20 ዓመት በታች ውድድር ላይ ሀገራችን ኢትዮጵያ ጨምሮ አምስት ሀገራት ሲሳተፉ በዙር በሚደረጉ ጨዋታዎች ከፍተኛ ነጥብ የሚያመጡ ሀገራት ወደ ቀጣዩ ዙር የሚያልፉ ይሆናል ።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከ ጅቡቲ ጋር ስታካሄድ በመቀጠል ከ ኤርትራ ፣ ታንዛኒያ ፣ ቡሩንዲ እና ዩጋንዳ ጋር የምትጫወት ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
#ዋንጫችን የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አዲሱን ዋንጫ የ ሊጉ አክስዮን ማህበር በ ይፋዊ ገፁ ላይ አስተዋውቋል ። " ዋንጫችን ፣ ኢትዮጵያዊነትን የመሰለ " @tikvahethsport @kidusyoftahe
" ዋንጫችን ኢትዮጵያዊ የመሰለ "

የ 2013 የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊው ፋሲል ከነማ ከመክፈቻ ጨዋታቸው በፊት ዋንጫቸውን ይረከባሉ ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
2 ' ፋሲል ከነማ ከ ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport @kidusyoftahe
17 ' ፋሲል ከነማ 0 - 0 ሀድያ ሆሳዕና

@tikvahethsport @kidusyoftahe
እረፍት | ፋሲል ከነማ 2 - 0 ሀድያ ሆሳዕና

ፍቃዱ አለሙ

@tikvahethsport @kidusyoftahe
72 ' ፋሲል ከነማ 2 - 1 ሀድያ ሆሳዕና

ፍቃዱ አለሙ ባዬ ገዛኸኝ

@tikvahethsport @kidusyoftahe