TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
TIKVAH-SPORT
የ ኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ለ አለም ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዎች እያደረገ ያለውን ዝግጅት እና በ ቀጣይ ስለሚያደርጋቸው የ ወዳጅነት ጨዋታዎች እንዲሁም የ አፍሪካ ዋንጫ የ ምድብ ድልድልን አስመልክቶ በነገው ዕለት ከ ቀኑ 7:00 ሰዓት ጀምሮ ወሎ ሰፈር በሚገኘው የ ኢ.እ.ፌ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል ። @tikvahethsport…
" በ ምድባችን የተለየ ነገር ለማሳየት እንሰራለን "

የ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ አለም ዋንጫ ማጣሪያ እያደረገ ያለውን ዝግጅት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል ።

ከተነሱ ነጥቦች መካከል :-

• በተለይ የ ወዳጅነት ጨዋታዎች ከ ሴራሊዮን እና ዩጋንዳ ጋር መጫወታችን ራሳችንን በደንብ እንድናይ ያደርገናል።

• " Off Season " በመሆኑ ምክንያት ለእነዚህ ጨዋታዎች አስፈላጊ የሆኑ ዝግጅቶችን በ ማድረግ ላይ እንገኛለን ።

• " Off Season " ላይ ብንሆንም ከ ልጆቹ ጋር የምንገናኝበት ክትትል የምናደርግበት አማራጭ ስለ ነበር ብዙ አልተቸገርንም ።

• ዝግጅቱ ትኩረት ያደረገው በ አካል ብቃት ፣ ስነ ልቦና እና ታክቲካል ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል ።

• ያለን የ ቡድን ስብስብ መጠን ትንሽ ነው ፣ ከ ሁለቱ ጨዋታዎች በኋላ የ መጨረሻ ተጫዋቾችን እናሳውቃለን ።

• ሽመልስ በቀለ የ ቡድኑ አካል ነው ሌላ ተጫዋቾችን አንጠራም ።

• የ አፍሪካ መድረክ ተሳታፊ ከሆኑት የ ፋሲል እና ቡና አሰልጣኞች ጋር እየተነጋገርን ነው ።

• የ ሴራሊዮን የወዳጅነት ጨዋታ ኢ.እ.ፌ ከ ስመጥር ስፖርት እና ኢንተርቴንመንት ጋር በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን ፤ የኡጋንዳ ጨዋታ በ ኢ.እ.ፌ የተመቻቸ ነው።

• የ አፍሪካ ዋንጫ ድልድልን አስመልክቶ የትኛውም ምድብ ላይ ልንሆን እንችል ነበር ፣ በደረሰን ምድብ ላይ የተለየ ምለው ነገር የለኝም ፣ በ ምድባችን የተለየ ነገር ለ ማሳየት እንሰራለን ።

መረጃው የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ተጫዋቼን አለቅም ብሏል !

የ መርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ለ ሀገራት የ አለም ዋንጫ ጨዋታ ማጣሪያ ግብፃዊውን ሞሀመድ ሳላህ ለ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት እንዲሄድ እንደማይፈቅዱ ተገልጿል ።

በ እንግሊዝ ያለውን የ ኳራንታይን ፕሮቶኮል ተከትሎ ሊቨርፑሎች ይህ ድምዳሜ ላይ ሲደርሱ የ ግብፅ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መፍትሔ በመፈለግ ከ ፊፋ ጋር በንግግር ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል ።

ግብፅ በ አለም ዋንጫ ማጣሪያው ከ አንጎላ እና ጋቦን ጋር ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጫዋቹን ለመሸጥ ተስማማ !

ተከታታይ ድል ያስመዘገቡት ቼልሲዎች የ ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቻቸውን ለ ዌስትሀም ለመሸጥ የ ቃል ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል ።

የ 26 ዓመቱ የመሐል ተከላካይ ከርት ዙማ ከ ቼልሲ ወደ ዌስትሀም በ 25.8 ሚልዮን ዩሮ እንደሚዘዋወር ይጠበቃል ።

ዝውውሩ እንዲሳካ ክለቦቹ በ ንግግር ላይ ሲገኙ ዙማ ከ ቼልሲ ከሚያገኘው ሳምንታዊ ደሞዞ የተሻለ ክፍያን መጠየቁ ተሰምቷል ።

ይህም ዝውውር ይፋ እንዳይሆን ሲያጓትተው ዌስትሀም ከ ስምምነት ላይ የሚደርሱ ከሆነ ዙማ የ ክለቡ ከፍተኛ ተከፋይ እንደሚሆን ይጠበቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
" ስራዬ ተጫዋቾች በ ክለቡ እንዲቆዩ ማሳመን አይደለም "

የ ሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሀም በ ሊጉ ያደረጓቸውን ጨዋታዎች በማሸነፍ በድል ጉዞ ላይ ቢገኙም ከ ተጫዋቾች ጋር በተያዘ ስማቸው በስፋት ሲያያዝ ቆይቷል ።

በተለይም ሀሪ ኬን እና ታንጎይ ንዶምብሌ ከ ክለቡ ጋር ይወጣሉ የሚሉ መረጃዎች መበራከታቸውን ተከትሎ ኑኖ ኤስፒርቶ ሳንቶ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

" የ ክለቡ ተጫዋቾች ለ ቶተንሀም እንዲጫወቱ ማሳመን የ እኔ ስራ አይደለም " ሲሉ ከ ጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሴናል ከ ተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ነው !

በ አዲሱ የውድድር ዓመት ውጤት የራቃቸው አርሴናሎች ከ መሐል ሜዳ ተጫዋቻቸው ጋር ሊለያዩ መቃረባቸው ተገልጿል ።

ዩራጋዊው የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ሉካስ ቶሬራ ወደ ጣልያን መዳረሻውን በማድረግ ፊዮሬንቲናን ሊቀላቀል መሆኑ ተነግሯል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቼልሲ ተጫዋቾቹን ለመሸጥ አቅዷል !

የ ቶማስ ቱሄሉ ስብስብ ቼልሲ ፈረንሳዊውን የ መሐል ተከላካይ ጁሌስ ኩንዴ ለ ማስፈረም ውስን ተጫዋቾቹን ለመሸጥ ተዘጋጅተዋል ።

በዚህም መሰረት :-

1. ኢኬ ኡግቦን ወደ ጌንክ በ 7.5 ሚልዮን ዩሮ

2. ዴቪድ ዛፓ ኮስታ ወደ አታላንታ በ 10 ሚልዮን ዩሮ

3. ከርት ዙማ ወደ ዌስትሀም የሚያደርጓቸው ዝውውር ጁሌስ ኩንዴ ለማስፈረም ለሚደረገው ሂደት መሆኑ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሴናል እና ሌስተር ሲቲ !

አርሴናል የ ሌስተር ሲቲው የ 24 አመት የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ጄምስ ማዲሰን ፈላጊ መሆናቸው በ ስፋት ሲነገር ቢቆይም ከ እውነት የራቀ መሆኑን ብሬንዳን ሮጀርስ ተናግረዋል ።

የ ሌስተር ሲቲው ዋና አሰልጣኝ ብሬንዳን ሮጀርስ እንደተናገሩት ማዲሰንን ለማስፈረም ለ ክለቡ ምንም አይነት ይፋዊ ጥያቄ አለመቅረቡን ገልፀዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሊቨርፑል ተጫዋቹን ለመሸጥ ተስማማ ! የ መርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ስዊዘርላንዳዊውን ተጫዋቹን ዠርዳን ሻኪሪ ለ ሊዮን በ 9.5 ሚልዮን ዩሮ ለ መሸጥ ከ ስምምነት ላይ መድረሱ ተገልጿል ። ሻኪሪ ከ ፈረንሳዩ ክለብ ጋር የ ህክምና ምርመራውን እንዲያካሂድ ፈቃድ ሲሰጠው በ ግል ጥቅማጥቅሞች ላይ ከ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተጠቁሟል ። @tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ከ ተጫዋቹ ጋር በይፋ ተለያየ !

በ ሊጉ ተከታታይ ድል ማስመዝገብ የቻሉት ሊቨርፑሎች ከ መስመር ተጫዋቻቸው ጋር መለያየታቸው እውን ሆኗል ።

ስዊዘርላንዳዊው የ 29 ዓመቱ ዠርዳን ሻኪሪ ለ ቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ለ ሊዮን ለመጫወት መስማማቱን ክለቡ ይፋ አድርጓል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አርሴናል ከ ተጫዋቹ ጋር ሊለያይ ይሆን ?

የ ሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሴናል ብራዚላዊውን የ መስመር ተጫዋቹ ዊሊያን ወደ ኮረንቲያስ ሊያመራ መቃረቡ ተገልጿል ።

የ 33 ዓመቱ ዊሊያን በ መድፈኞቹ ቤት ቀሪ ሁለት ዓመት ኮንትራት ሲኖረው ኮረንቲያስ ፍላጎታቸው በ ነፃ ማስፈረም መሆኑ ተዘግቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ጆርዲ አልባ እና ባርሴሎና !

የ 32 ዓመቱ የ ባርሴሎና የ ግራ መስመር ተጫዋች ጆርዲ አልባ ክለቡ የገባበትን የ ገንዘብ ቀውስ ተከትሎ የ ቡድን አጋሩን ጄራርድ ፒኬ በመከተል ደሞዙን ለ መቀነስ መስማማቱ ተገልጿል ።

በ ባርሴሎና እስከ 2024 የሚያቆይ ኮንትራት ያለው ጆርዲ አልባ ከ ደሞዙ ሀያ አምስት በመቶ የሚሆነውን ለመቀነስ መስማማቱ ተዘግቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ሚኬል አርቴታ ቀጣይነት ?

የ መድፈኞቹ ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አርሴናልን ወደ ሀያልነቱ ለመመለስ አምስት ጨዋታዎች ሲሰጡት ካልሆነ ግን ቦታውን ሊያጣ እንደሚችል ተገልጿል ።

አርቴታ የ ውጤት መሻሻሎችን ካላመጣ ጣልያናዊው አንቶኒዮ ኮንቴ የ ክለቡ ተቀዳሚ ምርጫ መሆኑ ተዘግቧል ።

አርሴናል በ ክለቡ ታሪክ በ ሊጉ የ መክፈቻ ጨዋታዎች ተሸንፈው #አንድም ግብ ሳያስቆጥሩ ሲወጡ ለመጀመሪያ መሆኑ ይታወቃል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ባርሴሎና ተጫዋቹ ከ ጉዳት ተመለሰ !

ከ ሜዳ ርቆ ከ ቆየ በርካታ ጊዜያት የተቆጠሩት ተስፈኛው የመስመር ተጫዋች አንሱ ፋቲ ወደ ልምምድ መመለሱ ይፋ ሆኗል ።

አንሱ ፋቲ በ ዛሬው ዕለት ወደ ልምምድ ሜዳ በመመለስ ከ ቡድኑ ጋር በ ጋራ መስራቱ ሲገለፅ ከ ሀገራት ጨዋታ በኋላ ወደ ሜዳ በመመለስ ከ ረጅም ጊዜ በኋላ እንደሚጫወት ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢንተር ሚላን አጥቂ ሊያስፈርሙ ነው !

የ ሴርያው ሻምፒዮኖች ኢንተር ሚላን በ ዝውውር መስኮቱ ተጨማሪ አጥቂ ሊያስፈርሙ መሆኑ ተገልጿል ።

ኢንተሮች በ ሴርያው ልምድ ያካበተውን የ ቶሪኖ የ ፊት መስመር አጥቂ አንድርያ ቤሎቲን ለማስፈረም ከ ክለቡ ጋር ንግግር መጀመራቸው ይፋ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ጨዋታ ጊዜ የተነፈገው ዶኒ ቫን ዴቢክ !

ኔዘርላንዳዊው የ ማንችስተር ዩናይትድ የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ ከ ብሄራዊ ቡድን ስብስብ ውጪ የ መሆን እድሉ ሰፊ መሆን ተነገረ ።

በ ማንችስተር ዩናይትድ በቂ የ መሰለፍ እድል አለማግኘቱን ተከትሎ አዲሱ የ ኔዘርላንድ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሉዊስ ቫን ሀል ስር ቦታውን እንደሚያጣ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ የሚሳተፉበት የ አፍሪካ ዋንጫ !

በ ካሜሩን አስተናጋጅነት በሚካሄደው እና ሀገራችን ኢትዮጵያ በምትሳተፍበት የ አፍሪካ ዋንጫ ለ አሸናፊው ሀገር የሚበረከተው የ ገንዘብ ሽልማት ተገልጿል ።

በዚህም መሰረት የ 2021 የ አፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ሰባት ሚልዮን የ አሜሪካ ዶላር እንደሚበረከትለት ታውቋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ የተጫዋቻቸውን ውል አራዝመዋል !

ሎስ ብላንኮዎች የ ዩራጋዊውን የ መሐል ሜዳ ተጫዋቻቸውን ኮንትራት ማራዘማቸው ይፋ ሆኗል ።

ፌዴ ቫልቬርዴ በ ሎስ ብላንኮዎቹ ቤት እስከ 2027 የ ውድድር ዓመት ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ውል ተፈራርሟል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል የ ተጫዋቹን ውል አራዘመ !

የነባር ተጫዋቾቻቸውን ውል በ ማራዘም የተጠመዱት ሊቨርፑሎች የ ግራ መስመር ተጫዋቻቸውን ውል ማራዘማቸው ይፋ ሆኗል ።

ስኮትላንዳዊው አንዲ ሮበርትሰን በ አንፊልድ ሮድ እስከ 2026 የ ውድድር ዓመት ድረስ የሚያቆየውን አዲስ ኮንትራት መፈራረሙ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋልያዎቹን በ ወዳጅነት ጨዋታ ለመግጠም ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ የደረሱት የ ሊዮን ኮከቦች መዳረሻቸውን ውድድሩ በሚካሄድበት ባሕር ዳር ከተማ በማድረግ የ መጀመሪያ ልምምዳቸውን ከቀኑ 10:30 ጀምሮ በመስራት ላይ ይገኛሉ።

መረጃው የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#Update

ዋልያዎቹ ወደ ባሕር ዳር በ ማቅናት ማረፊያቸውን አቫንቲ ብሉ ናይል ሆቴል በ ማድረግ ከ10:00 ሰዓት ጀምሮ ልምምዳቸውን በ ባህር ዳር ስታዲየም በመስራት ላይ መሆናቸውን የ ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስነብቧል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe