TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
290 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
በጎርፍ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ!

በአምባሰል ወረዳ በ017 ቀበሌ እንዳሉት በትናንትናው ዕለት ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ የ25 ዓመት ወጣት ደረቅ ወንዝ ተብሎ የሚጠራውን ወንዝ  በዋና በመሻገር ላይ እያለ ወንዙ በሌላ አካባቢዎች በጣለ ዝናብ ምክንያት  ከመጠን በላይ  በመሙላቱ ህይወቱ ሊያልፍ መቻሉ ታውቋል። 

የሟች አስከሬን በግምት 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ያህል በወንዙ መወሰዱን ገልፀዋል።

ከዚህ በፊት ነሐሴ 2/2014 ዓ.ም  የጊጣ ወንዝ ሞልቶ የ25 አመት ወጣት መሞቱን አስታውሶ የዘገበው የአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
#ትኩረት 📣

የአልጌ ወንዝ በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላቱ ምክንያት ከአዲስ አበባ-ውጫሌ፣ከደሴ ወደ ወልዲያ እንድሁም ከወልዲያ ወደ ደሴ አቅጣጫ በሚወስደው የአስፓልት መንገድ ላይ የተሰራው የተሽከርካሪ ድልድይ በጎርፍ እየተሸረሸረ መሆኑ ታውቋል።

ተለዋጭ መንገድ የሌለ በመሆኑም አስቸኳይ ጥገና ሊደረግለት እንደሚገባ ተጠይቋል። ድልድዩ ይበልጥ እንዳይበላሻ በጊዜያዊነት በጋቢዮን የማሰር ስራ መጀመሩም ተገልጿል። ለዘላቂ መፍትሄውም ተለዋጭ መንገድ ግድ ይላል ተብሏል።

መረጃው የአምባሰል ወረዳ ኮሙኒኬሽን ነው

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
#የዛሬ (ለነሐሴ 17/2014 የተመረጡ የቲክቫህ መረጃዎች)

🇸🇩 ጎረቤት ሀገር ሱዳን በሀገሯ የሚገኙትን ዜጎቻችንን እያፈሰች እያሰረች ሲሆን በዛው ያሉ ዜጎቻችን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩን የያዘበትን መንገድ እየወቀሱ ይገኛሉ። ዜጎች የመኖሪያ ፍቃድ (ኢቃማ) ባለማውጣታቸው ምክንያት እየታሰሩና ገንዘብ እየተቀጡ እንደሚገኙም አመልክቷል።

🐄 በኦሮሚያ ፣ ቦረና በድርቅ ሳቢያ በርካታ ወገኖቻችን ዛሬም ችግር ላይ መሆናቸው ተገልጿል። እነዚህ ወገኖች በድርቁ ምክንያት ያላቸውን ከብቶች ስላጡ እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ ሁኔታ ውስጥ አየኖሩ ይገኛሉ።

📝 የ2014 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ድረስ በሁለት ዙር እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ፈተናው በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን ፈታኞቹም የዩኒቨርሲቲ መምህራን ናቸው ተብሏል። አሁን ላይ ፈተናው ተዘጋጅቶ እየታተመ ሲሆን ፈተናው እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ ተፈታኞች እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም ተገልጿል።

💐 ከነሐሴ 9 እስከ 15 2014 ዓመት ድረስ ባሉት ቀናቶች በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ፣ በ18 ሰዎች ላይ ከባድ እና በ17 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ በንብረት ላይም የደረሰዉ ዉድመት በገንዘብ ሲተመን ከ300 ሺ ብር በላይ እንደሚገመት ተጠቁሟል፡፡

↔️ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ መላኬ አለማየሁን ጨምሮ የክፍለ ከተማው የመሬት ልማት ማኔጅመንት ጽ/ቤት እና የግንባታ ፈቃድ ኃላፊዎችና ምክትል ኃላፊዎች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል። ክፍለ ከተማው አዲስ ዋና ሥራ አስፈጻሚና እንዲሁም ሌሎች አዳዲስ አመራሮች ተሾመውለታል።

👍 የትምህርት ሚኒስቴር "የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ፕሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ፣ ክለሳና ማፅደቂያ መመሪያ"ን አጽድቋል። መመሪያው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ፕሮግራሞችና ሥርዓተ ትምህርቶች ከዓለም አቀፍ፣ ከቀጠናዊ እና ከአካባቢያዊ የልማት አጀንዳዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሄዱ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

#ማስታወሻ: የዘንድሮው ክረምት ተጠንክሮ በመቀጠሉ በሁሉም አካባቢ ያላችሁ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ ማድረጋችሁን እንዳትዘነጉ።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
የወልዲያ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታን በሦስት ወር ውስጥ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።

የወልዲያ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ የሲቪል ስራ 94 በመቶ እንዲሁምየኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ተከላ 27 በመቶ መድረሱ ተገልጿል።

ለትራንስፎርመር ማጓጓዝ የሚያስፈልገው ጊዜ ከግምት ውስጥ ሳይገባ ቀሪ የኤሌክትሮ መካኒካል ሥራዎችን ለማጠናቀቅ እስከ ሁለት ወር  ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን አጠቃላይ ሥራውን ለማጠናቀቅ ከሦስት ወር ያልበለጠ ጊዜ አንደሚያስፈልግ ታውቋል።

ማከፋፈያ ጣቢያው ከተጠናቀቀ በኋላ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ከነባሩ ባለ 66 ኪሎ ቮልት መስመር ጋር የማገናኘት ሥራዎች እንደሚፈልጉና በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው አንግሯል።

የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታው ተጠናቆ አግልግሎት መስጠት ሲጀምር ቀደም ሲል ከነበረው አገልግሎት በተጨማሪ ከአላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ሲያገኙ ለነበሩ  የተወሰኑ አካባቢዎች ኃይል መስጠት ያስችላል ያለው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ነው።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
#ጤናረቡዕ

የአመጋገብ ስርዓት እና የአይምሮ ጤና

[ በ @ibdeth የቀረበ ]

- አካላዊ ጤና እና የአመጋገብ ስርዓት ዘርፈ ብዙ ተዛምዶ አላቸው።

- ደካማ የአመጋገብ ሥርዓት ለወረደ ስሜት አንደኛው ምክንያት ሊሆን ይችላል፤ በሌላ ጎኑ ተገቢ የአመጋገብ ሥርዓት ጉልህ በሚባል ደረጃ የአዕምሮን ጤና ያሻሽላል።

- የአመጋገብ ስርዓታችን በሆድ እቃችን ውስጥ በሚገኙ ረቂቅ ተህዋሳት ላይ በሚያመጣው ተፅዕኖ የአዕምሮን ጤና ላይ በተላያየ መንገድ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር የተለያዩ ጥናቶች አረጋግጠዋል።

- የዘወትር የማዕዳችን ሥርዓት፥ እንደ ትኩራት ማጣት እና በስሜት ግፊት ነገሮችን በማድረግ የሚገለጠውን Attention Deficit Hyperactivity Disorder/ADHD/ ያሉ የአዕምሮ ጤና ችግሮች ጋር ተያያዥነት አለው።

- ኦሜጋ-3 ፋቲ አሲድ በተላዩ ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን የተለያዩ የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ላይ እራሱን ችሎ ወይም እንደ አባሪ መድኃኒት መጠቀም ስኬታማ ውጤትን አሳይቷል።

- የአመጋገብ ሥርዓታችን በተለያየ መንገድ የአዕምሮ ጤና ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል። በአዕምሮ ምግቦች የበለጠጉ ምግቦችን መጠቀም ስኬታማ እና በእንፃራዊ መልኩ ደግሞ ቀላል በሆነ መንገድ የአይምሮ ጤናን ለማሻሻል እንዲሁም ከአይምሮ ህመም ለማገገም አይነተኛ መንገዶች ናቸው።

🔗 ተጨማሪ በ 👉 INSTANTVIEW ያንብቡ

@tikvahethmagazine @Writefortikvah_bot
በእንቅርት ላይ .....
#Opinion

የአንባቢያን ቁጥር አሽቆልቁሏል በሚባልበት በዚህ ወቅት የወረቀት ዋጋ ጭማሪ የህትመቱን ክፍያ ጣራ እያስነካው ይገኛል። በአንድ የፌስቡክ ገጽ ላይ "በቅርቡ ኢትዮጵያ ምንም አይነት መጽሐፍ እና መጽሔት የማይታተምባት ሀገር ትሆናለች" የሚል ሀሳብ ተነስቶ ባይ እውነት አለው አልኩኝ።

የወረቀትና የህትመት ዋጋ መናር በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በወር አንዴ ጋዜጣ ፣ መፅሔት የሚያወጡ መገናኛ ብዙሃንን ሕልውናቸውን እየተፈታተነው መሆኑ የአደባባይ ምሥጢር ከሆነ ሰነባበተ። አብዛኞቹ ጋዜጦች አሁን ላይ በኪሳራ እየታተሙ ይገኛሉ። ወጪያቸውን በሚሰሩት ማስታወቂያ ነው የሚያካክሱት።

ይህ ጉዳይ የሚያሳስባቸው ግለሰቦች በተለያየ ጊዜ መንግስት በተለይ በወረቀት ዋጋ ላይ ያለውን መናር በህግ ማዕቀፎችና ዘርፉን በመርዳት እንዲያረጋጋ ቢጠይቁም ሰሚ ያገኙ አይመስልም።

አንድ ደራሲ በስንት ልፋት ለህትመት የሚያበቃው መጽሐፍ በምን ያህል ብዛት የሚታተም ይመስላችኋል?

እንደው በብዙ ማስታወቂያ ተለፍፎ፤ ደራሲው በማኅበራዊ ሚዲያው ለወራት ቅስቀሳ (Campaign) ሰርቶ እንደው በመጀመሪያው ዙር የታተመው 3,000 ኮፒ ከተሸጠም ጥሩ ተሸጧል ማለት ነው።

የወረቀት ዋጋስ ምን ያህል የጨመረ ይመስላችኋል?

- ከዓመት በፊት 60 ግራም 1 ሪም ( 500 ቅጠል የሚይዝ A1 ወረቀት ማለት ነው) 1300 ብር የነበረ ሲሆን አሁን ከ3400-4000 ብር ሆኗል።

- 250 ግራም አርት ወረቀት (ለከበር ማተሚያ የሚያገለግል፤ 1 ሪም 100 ቅጠል የሚይዝ) ከ1100 ተምዘግዝጎ 6000 ብር ደርሷል።

- ትልቁ ማተሚያ ድርጅት ብርሃንና ሰላም ሰኔ ወር ላይ 80 በመቶ ጭማሪ ነው ያደረገው።

ይህ ጉዳይ የዋጋ ጭማሪ ወይም የደራሲያንና የህትመት ሚዲያ ባለቤቶችን ቢዝነስ ብቻ የሚመለከት አይደለም ትውልዱ የሚያነበው ምን ቁም ነገር ይኑረው በሚል ነው። አረ ለልጆቻችን!

መቼም መጽሐፍ በዚህ በዲጂታል ዘመን ማን ያነባል የሚል አይጠፋም! ይሄኔ አይደል በእንቅርት ላይ ..... ማለት። ለማንኛውም ጉዳዩን ላይ ተጽዕኖ መፍጠር ካልተቻለና ለውጥ ካላመጣን ብዙ ነገሮቻችን ይበላሻሉ። መልካም ጊዜ!

* በጹሑፍ መሳተፍ የምትፈልጉ @Writefortikvah_bot

@tikvahethmagazine
#Ambassel 📍

በአምባሰል ወረዳ በ23 ቀበሌዎች በደረሰ የጎርፍ፣ የበረዶና የመሬት መንሸራተት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 341 ሴቶችን ጨምሮ 665 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል።

ከ1ሺህ 697 ሄክታር  በላይ መሬት ላይ የተዘራ ሰብል ላይም 74 በመቶው ጉዳት ደርሶበታል። ተፈናቃዮቹ አሁን ላይ በትምህርት ቤቶችና በገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከላት ተጠልለው ይገኛሉ ተብሏል።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
የሀምሳ ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ ተደረገ።

የሞሮኮው የአፈር ማዳበሪያ አምራች ድርጅት ኦሲፒ (OCP) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለመደገፍ የሚያስችል የሀምሳ ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ ለኢትዮጵያ አድርጓል። የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ አለም ላይ የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ፈታኝ በሆነበት ጊዜ ላይ መሆኑ ለየት ያደርገዋል ሲሉ የግብርና ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
ኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን የሚሆኑት ጎልማሶቿ የፋይናንስ ተቋማትን አይጠቀሙም

በኢትዮጵያ 30 ሚሊዮን ገደማ የሚጠጋ ብዛት ያላቸው ጎልማሶች በፋይናንስ ተቋማት ምንም ዓይነት ሂሳብ እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።

ባንኩ በሚቀጥሉት 4 ዓመታት 70 በመቶ ጎልማሶችን ለማካተት እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ፋይናንስ አካታችነት ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ዘለቀ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በፋይናንስ ስርዓቱ ውስጥ የተካተቱ ወይም የባንክ ሂሳብ ያላቸው ጎልማሳ ዜጎች ከ45 በመቶ እንደማይበልጡ ገልጸው ይህም ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የፋይናንስ ተቋማት ቅርንጫፎች ፣ወኪሎች ፣ኤቲ ኤምን ጨምሮ ፖስ ማሽኖች በገጠሩ የአገሪቷ ክፍል በሚፈለገው ደረጃ አለመሰራጨታቸውን በምክንያትነት ተጠቅሰዋል። (ENA)

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
የክሪፕቶ ምርት፤ አገልግሎትና ዝውውርን ለሚሰሩ ምዝገባ ተጀመረ።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የክሪፕቶ ምርት፤ አገልግሎት፣ ዝውውርና ማይኒንግን በተመለከተ ስራዎችን ለሚያከናውኑ ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።

ምዝገባው፥  አስተዳደሩን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 808/06 አንቀጽ 6 (9) በተሰጠው ስልጣን መሰረት መሆኑ ተጠቅሷል።

አዋጁ  “የክሪፕቶ ምርትና ዝውውርን የመቆጣጠር እና አስፈላጊውን መስፈርት ማውጣትና የአጠቃቀም ስርዓት መዘርጋት” ሃላፊነት አለበት እንደሚል ይጠቁማል።

የክሪፕቶ ምርት፤ አገልግሎትና ዝውውርን ለሚያደርጉ የወጣው ማስታወቂያ መምዝገብ ለሚፈልጉ ወይም ለመመዝገብ ጠይቀው ሂደት ላይ ላሉ ሲሆን በአስተዳድሩ ድረ-ገጽ አማካኝነት መመዝገብ ይቻላል ተብሏል።

ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ምዝገባው የሚካሄድ ሲሆን ይህንን ተግባራዊ በማያደርጉ እና በዚህ ስራ ያለምዝገባ ተሰማርተው በሚገኙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
🗨️ "አንጎላችን በቀን ውስጥ ከምንጠቀመው ምግብ የምናገኘውን ጉልበት በአማካኝ ሃያ በመቶ ፍጆታን ይጠቀማል።"

ለውጥ ይፍጠሩ 👉 @Writefortikvah_bot

@tikvahethmagazine @ibdeth
ሥጋት ያንዣበበበት የዶሮ እርባታ .....

የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀናባባሪዎች ማኅበር መንግሥት ለዶሮ አርቢዎች አፋጣኝ ድጋፍ ካላደረገ በቀጣይ ወራት አንድ እንቁላል ከ20 እስከ 30 ብር ሊሸጥ እንደሚችል አስታውቋል፡፡

የኮቪድ ወረርሽኝ ተከትሎ የሆቴሎች መዘጋት፤ በቅርቡ ደግሞ 'ተከሰተ' የተባለው የዶሮ በሽታ ሳቢያ በዶሮ እና ዶሮ ምርቶች ላይ እገዳ መምጣቱ አርቢዎች ምርቶቻቸውን ለማስወገድ ተገደው እንደነበር የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ሚሊዮን አስታውሰዋል።

አብዛኛቹ የዶሮ አርቢዎች የባንክ ብድር ያለባቸው መሆኑን ያነሱት አቶ ብርሃኑ መንግሥት ጣልቃ ገብቶ ዘርፉን ከውድቀት ለማዳን የባንክ ብድር ማራዘሚያ እና የግብር እፎይታ እንዲሰጠን እየጠየቅን ነው ብለዋል፡፡

አርቢዎቹ ላሉበት ችግር አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጥ ከሆነ  በርካታ የዶሮ እርባታዎች ሊዘጉ እንደሚችሉ ጭምር ነው የጠቆሙት። ይህን ተትሎ በሚፈጠረው የምርት ዕጥረትም እንድ እንቁላል ከ 20 እና 30 ብር ድረስ ሊሸጥ እንደሚችል ሥጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ የተጠየቁት በግብርና ሚኒስቴር እንስሳት እና አሳ ሀብት ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ፅጌሬዳ ፍቃዱ ሚኒስቴሩ እስካሁን ከወራት በፊት ተከስቶ በነበረው የዶሮ በሽታ መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ ሲሠራ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አርቢዎች በመለየት ድጋፍ የሚያገኙበትን መንገድ አንደሚፈልግ ኃላፊዋ ጨምረው አንስተዋል፡፡ (Balageru Tv)

@tikvahethmagazine  @tikvahmagbot
ከሦስት መቶ በላይ ለሚሆን የማኅበረሰብ ክፍልን የንፁህ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ የቻሉት ኢትዮጵያዊ

ከኤፍራታና ግድም ወረዳ የተገኘው መረጃ ልብን ሞቅ ያደርጋል። በወረዳው ዱሉት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ዘውዴ ግዛው በግብርና ስራ እና በናፍጣ በሚሰራ የእህል ወፍጮ ሥራ በመስራት ይተዳደራሉ።

እኚህ በጎ ግለሰብ ህብረተሰቡ ለዘማናት በውሃ እጦት ሲንገላታ በማየታቸው ሌት ከቀን ያስጨንቃቸው ነበርና በራሳቸው ወጪ ከተራራ ሥር ውኃ በመጥለፍ ከሶስት መቶ (300) በላይ ለሚሆኑ ማኅበረሰቦች የንፁህ ውሃ መጠጥ ተጠቃሚ ማድረግ ችለዋል።

- ወጪውን ማን ሸፈነላቸው?

ይህንን ሀሳባቸውን ለማሳካትም የተለያዩ የቧንቧ ቁሳቁሶች߹ ከ2ሺህ ሜትር በላይ ቱቦ߹ ለታንከር የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በመግዛት ግንባታውን ያለ አንዳች አጋዥ እና ረዳት መስራታቸውን አቶ ዘውዴ ያስረዳሉ።

ለግንባታውም ሆነ ለቧንቧ ዝርጋታ የሚውሉ ቁሳቁሶች በጥቅል ግዥ የሚውል ከ363 ሺህ 400 ብር በላይ ወጪ ከራሳቸው ማድረጋቸውን ነው የሚናገሩት።

የፈጠራው ባለቤት አቶ ዘውዴ ግዛው ከ3ሺህ ሊትር በላይ የሚይዝ  ሦስት ታንከር መስራታቸውን በማንሳት በቂ የሆነ የውሃ አቅርቦት እንዲኖር ተጨማሪ ከ800 ሺህ ሊትር በላይ ውሃ የሚይዝ ታንከር ያስፈልጋል ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

- ከዚህ ቀደም ምን አይነት ሁኔታ ላይ ነበሩ?

በውሃ ዕጦት የተነሳ ለሚሰሩት ሥራ አንድ ባለ20 ሊትር ጀሪካን ውሃ 9 ብር ለመግዛት ይገደዱ ነበር። የአከባቢው ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ በሸዋ ናኑ እንደሚገልጹትም ቧንቧው ከመሰራቱ በፊት የኩሬ ውሃን ለመጠጥ እና ለመስሪያቸው እንደሚጠቀሙ አስታውሰው አሁን በአቶ ዘውዴ ጥረት እቤቴ  ደጃፍ ላይ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ሆኛለሁ ሲሉ ገልጸዋል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-MAGAZINE
በጎፋ ዞን በአራት ቀናት ውስጥ ምንነቱ ባልታወቀ በሽታ 60 አህዮች መሞታቸው ተነገረ በጎፋ ዞን በሶስት ወረዳዎች ምንነቱ ባልታወቀ ተላላፊ በሽታ በአራት ቀናት ውስጥ 60 አህዮች ሲሞቱ በርካታዎች በበሽታው እየተጠቁ እንደሚገኙ የጎፋ ዞን ግብርና መምሪያ አስታውቋል። ይህ ምንነቱ ያልታወቀውን ተላላፊ በሽታ እያጠቃ የሚገኘው አህዮችን ብቻ ሲሆን ምንነት ለማወቅ ወደ ወላይታ ሶዶ ላብራቶሪ ናሙና ተልዕኮ ውጤት…
#Update

በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን በተከሰተው በጥቂት ሰዓታት ውስጥ አህዮችን የሚገድለው ወረርሽኝ በዞኑ በደንባ ጎፋ ፣ ዛላ ፣ ኦይዳ ወረዳዎች ከባለፈው ሳምንት ወዲህ ብቻ ከ300 አህያዎች መሞታቸው ተነግሯል።

በዞኑ በሚገኙ የገጠር ቀበሌያት አህዮች ከመጓጓዣ አገልግሎት በተጨማሪ በሬን ተክተው እርሻ እንደሚያርሱ የሚናገሩት ዶቼ ቬለ ያናገራቸው አርሶአደሮች፥ ቀሪ አህያዎችን ከሞት ለማትረፍ መንግሥት የሕክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የዞኑ ግብርና መምሪያ አስተያየት፦

በመምሪያው የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ሙሉቀን ተመስገን ዞኑ የወረረሽኙን ምንነት በምርመራ ከማረጋገጥ ጎን ለጎን በበሽታው የተጠቁ አህዮችን ከጤነኞቹ ለይቶ የማቆየት ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ አስተያየት፦

የቢሮው የወላይታ ሶዶ ቀጠና የእንስሳት ጤና ጥበቃ ማዕከል ሃላፊ ዶክተር አለማየሁ አንደገለጹት ከሞቱ አህያዎች ላይ ናሙና ተወስዶ በሰበታ እንስሳት ላብራቶሪ ምርመራ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በምርመራ ውጤቱ መሠረትም በደም ናሙና ውስጥ የአፍሪካ የጋማ ከብቶች በሽታ እና የጋማ ከብቶች ሄርፔስ የተባሉ በሽታዎች አማጪ ተህዋስ መገኘታቸውን የተናገሩት ዶክተር አለማየሁ አነኝህም ለአህዮቹ ሞት ምክንያት ናቸው የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በምርመራ ከተገኙት ሁለት የበሽታው አይነቶች መካከል የአፍሪካ የጋማ ከብቶች በሽታ በአገር ደረጃ ክትባት ቢኖረውም ሌላኛው የጋማ ከብቶች ሄርፔስ ግን ምንም አይነት ክትባት የለውም ብለዋል፡፡ በመሆኑም፥ አህዮቹን መለየትና ለተወሰነ ጊዜ ከቤት እንዳይወጡ ማድረግ በአማራጭነት እየተተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። (DW)

@tikvahethmagazine
#የዛሬ (ለነሐሴ 18/2014 የተመረጡ የቲክቫህ መረጃዎች)

⭕️ የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት ዛሬ ፤ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ " ህወሓት " በምስራቅ ግንባር በቢሶበር ፣ ዞብል ፣ እና ተኩለሽ በኩል ከለሊት 11 ሰዓት አንስቶ ጥቃት መፈፀሙን ገልጿል። ቀደም ብሎ ህወሓት የፌዴራል መንግስት ከለሊት 11:00 ጀምሮ በጩቤ በር ፣ ጃኖራ ፣ ጉባጋላ እና በያሎው አቅጣጫ ወደ አላማጣ ፣ ባላና ብሶበር መጠነሰፊ ጥቃት ከፍቷል ሲል ክስ ቢያሰማም የፌደራል መንግስት ግን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ነው ብሎታል።

📣 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግና የመንግስትና የህወሓት የሰላም ድርድር እንዲቀጥል የጠየቁ ሲሆን የአፍሪካ ህብረት (AU) ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪም በአስቸኳይ ግጭት እንዲቆምና ድርድሩ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

🚚 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ፤ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች በሰጡት መግለጫ ዛሬ ነሀሴ 18 ቀን 2014 ዓ/ም ጥዋት በትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ ከተማ የሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) መጋዘን መዘረፉን ገልፀዋል። ዛሬ ማለዳ ላይ የትግራይ ኃይሎች መቐለ በሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን በኃይል በመግባት 12 የነዳጅ ታንከር ተሽከርካሪዎችን 570,000 ሊትር ነዳጅ መውሰዳቸውን ገልፀዋል።

በደቡብ ክልላዊ መንግስት ጉራጌ ዞን ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች እየተሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ይገኛሉ። እየታሰሩ ከሚገኙት መካከል በዞኑ  በኃላፊነት ቦታ ያሉ ጭምር መሆናቸው ተጠቁሟል።

🗓 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  የፌዴሬሽን ም/ቤት 6 ዞኖችን እና 5 ልዩ ወረዳዎችን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በ3 ወር ህዝበ ውሳኔ በማድረጃት ውጤቱን ለምክር/ቤቱ እንዲያሳውቅ ማለቱን ተከትሎ ለህዝበ ወሳኔ የሚወስደውን ጊዜ ምን ያህል እንደሆነ የመወሰን ፣ የመርሀ ግብር ሰሌዳ የማዘጋጀት የማፅደቅ እንደ አስፈላጊነቱ የማሻሻል እና የማስፈፀም ስርልጣን የቦርዱ መሆኑን አስገንዝቧል። የጊዜ ሰሌዳውንም አውጥቶ ለምክር ቤቱ እንደሚገልፅ ገልጿል።

💸 የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የክሪፕቶ ምርት፤ አገልግሎት፣ ዝውውርና ማይኒንግን በተመለከተ ስራዎችን ለሚያከናውኑ ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል። ምዝገባው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ድረ ገጽ እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው።

📌 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ፕሬዝዳንት አወዳድሮ ለመቅጠር የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቷል። የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ተቋሙን ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የሚመራ ኃላፊ ለማወዳደር ፍላጎቱን አሳውቋል፡፡

⚽️ ሀገራችንን ወክሎ በሴካፋ የአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ ተሳታፊ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እግር ኳስ ክለብ የዩጋንድ ሊግ ሻምፒዮን በሆነው ሺ ኮርፖሬት የ 2 ለ 1 ሽንፈት አስተናግዶ ለፍጻሜ ሳይደርስ ቀርቷል።

@tikvahethmagazine
በትራፊክ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ!

መነሻውን ከአዲስ አበባ አድርጎ ወደ መርሐቤቴ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 አ.ማ 02398 የጭነት አይሱዙ በፊጥራ ከተማ አካባቢ ልዩ ስሙ ኮረፍቲት በተባለ ቦታ ከለሊቱ 9:00 ሰዓት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የአሽከርካሪው ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በረዳቱ ላይ ቀላል የሚባል ጉዳት መድረሱን ከመርሐቤቴ ወረዳ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

@tikvahethmagazine