TIKVAH-MAGAZINE
199K subscribers
18.9K photos
290 videos
70 files
2.48K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

#ኢትዮጵያ

ያግኙን +251913134524
Download Telegram
TIKVAH-MAGAZINE
ኢትዮጵያና ናይጄሪያ በሚቀጥለው ወር በሚኒስቴር ደረጃ የጋራ ስብሰባ በአዲስ አበባ ያደርጋሉ። ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በማዕድን ሥራ እና በሌሎችም ዓለም ዐቀፍ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመምከር ለመምከር በሚቀጥለው ወር በአዲስ አበባ የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ሊያደርጉ መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት በናይጄሪያ ያደረጉትን…
#Update: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በናይጄሪያ ያደረጉኑትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተከትሎ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የተገለጸው የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ዛሬ ጀምሯል።

ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይም ቀደም ሲል በማዕድ እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የተስሟሙባቸውን ነጥቦች ጨምሮ አብሮ መስራት የሚችሉባቸው ሌሎች ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል ፋብኮ ዘግቧል።

አዲስ አበባ እና አቡጃ ቀደም ሲል የአየር ፣ የንግድ ፣ የባህል ሳይንስ እና ትምህርት፣ በባህልና ቱሪዝም እንዲሁም በግብርናው መስክ በጋራ ለመስራት ትብብር ፈፅመው እየተንቀሳቀሱ ሲሆን ይህ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባም ሦስተኛው ነው ተብሏል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
ሁለት ህጻናትን በጩቤ አስፈራርቶ የግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመ ግለሰብ በ17 አመት ጽኑ እስራት ተቀጣ።

በአዊ ብሄ/አስ እንጅባራ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 04 ልዩ ቦታው መናኸሪያ መግቢያ አካባቢ ሁለት ኑሯቸውን በጎዳና ያደረጉ ወንድ ህጻናትን የተመሳሳይ ጾታ ግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ።

ጌትነት ጨቅሌ (ሻራቴው) የተባለው ግለሰብ ድርጊቱን የፈጸመው መጋቢት 20/2014 ዓ.ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ሲሆን የ15 እና የ10 አመት ህጻናትን ከሌሊቱ ከተኙበት በረንዳ የግብረሰዶም መፈጸሙን የእንጅባራ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማው ፓሊስ ጽ/ቤት የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ውቢት አየነው እንደገለፁት ህጻናቱ መጋቢት 21/2014 ለእንጅባራ ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በሰጡት ጥቆማ መሠረት ተከሳሹን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የባንጃ ወረዳ ፍ/ቤት በህክምናና በሰው ማስረጃ ግብረሰዶም መፈጸሙን በማረጋገጥ ግንቦት 15/2014 በዋለው ችሎት ግለሰቡ በ17 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ሀላፊዋ አያይዘውም ግብረሰዶም በአካባቢው ተፈጽሞ እንደማይታወቅ ጠቅሰው በሀገራችን ህግና በማንኛውም ሀይማኖት የተከለከለና የማይደገፍ ድርጊት በመሆኑ መከላከል ላይ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይም ወላጆች ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ጎዳና እንዳይወጡ መከላከል እና የት እንደሚውሉ ክትትል ማድረግ ከቤተሰብ የሚጠበቅ ግዴታ መሆኑን በአጽንኦት አሳስበዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
አማራ ባንክ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ ይጀምራል።

በምስረታ ላይ የቆየው የአማራ ባንክ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል። እስከ ሰኔ ሰላሳ ሰራ የሚጀምሩት ቅርንጫፎች ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚያሳድግም የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ባንኩ በተለያዩ የተግባቦት ስርአት የመጣ ሲሆን በዋነኝነትም "ከጎንዎ ማን አለ" የሚለው ማስታወቂያ እንደሚገኝበትም ገልፀዋል።

ሰኔ 11 ስራውን በይፋ የሚጀምረው ባንኩ በእለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ እንደሚከፍል ተገልጿል።

በእለቱ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም የእንኳን ደስ ያላችሁ ስጦታም ይበረከትላቸዋል መባሉን የዘገበው ኢፕድ ነው።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#ELiDAEthiopia

“የማህበረሰብ ውይይት እና ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ሴቶች እና ወጣቶች ለረጅም ጊዜ የቆዩ እና እየጠፉ የሚገኙ የማህበረሰባችን የሰላምን እና እርቅን መገንቢያ እሴቶችን በማጎልበት ረገድ ሰፊ ድርሻ እንዲኖራቸው ያግዛሉ፡፡ በተጨማሪም እንደ ሀገር ከገጠሙን አለመግባባቶች እና ችግሮች ለመውጣት ሴቶች እና ወጣቶችን የሰላም ግንባታ እና ግጭት አፈታት ላይ ማሳተፍ እና ሰፊ ድርሻ እንዲኖራቸው እድል መስጠት ተገቢ ነው፡፡”

ወ/ሮ ዘሪቱ ሁሴን (የኮምቦልቻ ሪጂዮ ፖሊታን ከተማ አስተዳደር በህልና ቱሪዝም ተጠሪ ጽ/ቤት ሀላፊ)

➡️ For English

° Website ° Facebook ° Twitter ° Telegram
ምዕራብ ጎጃም ዞን በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ከ1400 በላይ መኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወደመ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን በሰሜን ሜጫ ወረዳ በአምስት ቀበሌዎች ላይ በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ ከ1400 በላይ የአርሶአደር መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ማውደሙን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ኮሚኒኬሽን አስታውቋል።

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ በሰው ላይ ጉዳት ባይደርስም በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል። በዚህም የ1,409 የአርሶአደር መኖሪያ ቤቶች ውድመት፣ የ144 እንስሳት ሞት፣ በአትክልት እንዲሁም በሰብል ላይ ውድመት አድርሷል።

በተጨማሪ 11,200 ኩንታል የተቀመጠ እህል ፣ ለዘር የተዘጋጀ 1,500 ማዳበሪያ፣ 45 ኩንታል ምርጥ ዘር ከጥቅ ውጭ ሆኗል በማለት የሰሜን ሜጫ ወረዳ የኮሚኒኬሽን ሀላፊ አ/ቶ መዝገቡ ስመኘው ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።

እንደ ሀላፊ ማብራሪያ ከሆነ ጉዳቱን የሚያጠና ግብረሀይል ተቋቁሞ ጉዳት ለደረሰባቸው አርሶአደሮች አስቸኳይ ድጋፍ ሊደረግላቸው የሚገባውን ነገር በዝርዝር መለየቱን ገልፀዋል።

ከሚያስፈልገው አስቸኳይ ድጋፍ ውስጥ 89 ሺ ቆርቆሮን ጨምሮ ሌሌች ድጋፍች እንዲደረግላቸው ለሚመለከተው አካል መተላለፉን ተናግረዋል። በተጨማሪም አቅሙ የፈቀደ ማንኛውም አካል ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
ተመራቂ ነዎት ወይስ የተሻለ ስራ ማግኘት አስበዋል? እንግዲያውስ የሽያጭ እና ማርኬቲንግ፣ ዲጂታል ማርኬቲንግ እና ማይንድሴት ልዩ የ 2 ወር ስልጠናን በከፍተኛ ልምድ እና እውቀት ባላቸው አሰልጣኞች ብቃትዎንና ንቃትዎን ለመጨመር መልኅቅ ማርኬቲንግ እና ሊደርሺፕ ኢንስቲትዩት ተዘጋጅቶ እየጠበቀዎ ነው።

ምን ይለየናል? በተግባር ማሰልጠናችን፣ የተረጋገጠ የስራ ዕድል እና የምክክር አገልግሎት (Mentorship) መስጠታችን!

አሁኑኑ በ0967280828 ደውለው የመልኅቅ ቤተሰብ ይሁኑ!
በ11 ወራት ውስጥ የተሰበሰበው 313 ሺህ ዩኒት ደም ብቻ መሆኑን ተገለጸ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም እና ቲሹ ባንክ አገልግሎት እንደ ሀገር በተያዘው ዓመት በ11 ወር ውስጥ 313 ሺህ ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉን ገልጿል።

ይህም ካለው የህዝብ ቁጥር አንፃር ሲታይም 0 .03 ፐርሰንት ብቻ መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ሐብታሙ ታዩ የተናገሩ ሲሆን እንደ እንደ ሀገር በቂ እንዳልሆነ ተናግረዋል ።

የኢትዮጵያ የደም እና ቲሹ አገልግሎት የ2014 በጀት አመት 10ኛው የደም ባንክ ዓመታዊ ጉባኤና 18ኛው የአለም አቀፍ ደም ለጋሾች ቀን" ደም መለገስ የአብሮነት ተግባር ነው " ! በሚል መሪ መልዕክት ጉባኤው ዛሬ በጅግጅጋ እየተከበረ ይገኛል። (SRTV)

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
ኢትዮጵያና ጣሊያን የ22 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።

ኢትዮጵያና ጣሊያን ለተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚውል የ22 ሚሊየን ዩሮ የብድር ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴና የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ተፈራርመዋል።

ብድሩ የቡልቡላ፣ ቡሬ፣ይርጋለምና ባአከር የተቀናጀ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ማጠናከሪያና በፓርኮቹ ዙሪያ ለሚቋቋሙ የገጠር ሽግግር ማዕከላት ግንባታ የሚውል ነው ተብሏል።

የብድር ስምምነቱ ኢትዮጵያና ጣሊያን ያላቸውን የኢኮኖሚ ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ነው የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ ያስታወቁት።

የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ በበኩላቸው፥ ስምምነቱ ጣሊያን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር እንደምትሻ የሚያሳይ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#ELiDAEthiopia

በሰላማዊው ጊዜ በሴቶች ላይ የሚኖረው ሀላፊነት አና ጫና ከፍ ሲልም ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችና እና ጉዳቶች እንዳሉ ሆኖ በግጭት እና ሰላም እጦት ወቅት በእጥፍ ይጨምራሉ፡፡ ስለሆነም፣ ከግጭት በሗላ ስርአተ ፆታን መሰረት ያደረገ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥበት ስርአት መዘርጋት እና በግጭት የተጎዱ ሴቶችን በአግባቡ ተደራሽ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ አንገብጋቢ ጉዳይ እና ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን ይገባል፡፡

➡️ For English

° Website ° Facebook ° Twitter ° Telegram
#የዛሬ (ሰኔ 6/2014)

መምህርት መስከረም አበራ በ30,000 (30 ሺ ብር) ዋስትና ከእስር እንድትለቀቅ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ውሳኔ ቢያስተላልፍም መርማሪ ፖሊስ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መምህርት መስከረም አበራ በ30 ሺህ ብር ዋስትና እንድትፈታ በሰጠው ውሳኔ ላይ ይግባኝ መጠየቁ ተሰምታል።

የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ላይ ተጨማሪ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። ችሎቱ 7 ቀን የምርመራ ጊዜ የፈቀደው ፖሊስ " በምርመራው የሚያጠናቅቃቸው ነገሮች ካሉ " በሚል ምክንያት ነው።

ጋዜጠኛ ተመስገን ፍርድ ቤት ነገ እንዲቀርብ ዛሬ መጥሪያ ደርሶታል። ነገ ሰኔ 7/2014 ዓ.ም ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ቻሎት እንደሚቀርብ ጠበቃው አቶ ሄኖክ አክሊሉ ተናግረዋል።

📢 የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች 6ኛው ምክር ቤት በ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመኑ በሚያካሂደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ፤ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቃል የሚሰጡትን ምላሽ ያዳምጣል። ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚካሄደው በዚህ መደበኛ ጉባዔ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

🎉 ዓለም አቀፍ የቁርአን ውድድር በአዲስአበባ ስታዲየም ተካሂዷል። ዚያድ ፈሪጃ ከሉብናን በአዛን ውድድር 1ኛ ደረጃ በመያዝ አሸናፊ ሆኗል። ሙሀመድ ኑር ከኦርዶን በሂፍዝ ውድድር አንደኛ ደረጃ በመውጣት 10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር አሸናፊ ሆኗል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስአበባ ስታዲየም የተካሄደው አለምአቀፍ የቁርአን ሒፍዝ እና አዛን ውድድርም በሰላም ተጠናቋል።

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የቀብር ስነስርዓት ነገ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 8 ሰዓት በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስትያን እንደሚፈፀም ታውቋል። ( አርቲስት ዳዊት ነጋ ማን ነው ? )

🏦 በምስረታ ላይ የቆየው የአማራ ባንክ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል። እስከ ሰኔ ሰላሳ ሰራ የሚጀምሩት ቅርንጫፎች ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚያሳድግም የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ዛሬ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
Register at https://www.effsaa.org/short-term-training-program-registration-form/ after the settlement of the training fee.
Venue
At the training hall of Ethiopian Freight Forwarders and Shipping Agents Association (EFFSAA) which is located at Kazanchis, Nigist Towers Hotel & Apartments 4th Floor (In front of Elilly International Hotel)
For More Information,
Call us at +251 115 589045 / +251 903 182525
OR
Visit our telegram channel
https://t.iss.one/EFFSAAOfficial
የሰኔ ወር የመጨረሻው ድንቅ ጉዞ ወደ አዋሽ ብሔራዊ ፖርክ እና ድሆ ሎጅ

የጉዞ ቀን:-ሰኔ 11 /2014 | መመለሻ :-ሰኔ 12 /2014
👉 ከሃገር ውጪ ያላችሁ ሃገር ቤት ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ይህን ምርጥ ጉዞ በመጋበዝ ሰፕራይዝ ያድርጉ

የምንጎበኛቸው፦ |በተፈጥሮ የታደለውን የአዋሽ ፓርክ| አዋሽ ፏፏቴ| ተፈጥሯዊ ፍልውሃ ከ 40-50c በሚደርስ ውሃ መታጠብ| ዋና በድሆ ሎጅ|

ክፍያ የሚያጠቃልለው፦ | የድንኳን አዳር ፓርኩ ውስር | አንድ ምሽት ካምፕፋየር 🚎 ትራንስፖርት | 🍽 ምግብ,( ቁርስ ምሳ እራት ) ሻይ ቡና | 💧 የታሸገ ዉሃ |🚶አስጎብኚ ስካውት | የፓርክ መግቢያ | ፎቶ ያጠቃልላል|

መነሻ ቦታ ሜክሲኮ ሸበሌ ሆቴል ፊት ለፊት መገኛ ሰዓት 11:30 መነሻ 12:00 ሰዓት

ዋጋ በአንድ በሰው :- 3500
ለበለጠ መረጃ 👉 የቴሌግራም ግሩፖችንን ከታች ያለዉን ሊንክ በመጫን ይቀላቀሉ https://t.iss.one/mirt_haikinhg
📞0962 26 78 20 or @yeneneh
አዘጋጅ፦ የኔነህ ፊልም ፕሮዳክሽን
#አፋልጉኝ

ንብረትነቱ የሀብታሙ ታረቀኝ የሆነ 3L ሚኒባስ መኪና በቀን 6/17/14 በትላንትናው እለት ከይርጋለም ከተማ 05 ቀበሌ ከመኖሪያ ቤት የተሰረቀ ስለሆነ እባካችሁን በያላችሁበት አካባቢ ክትትል እንድታደርጉ እና የሚኖረውን መረጃ በሚከተሉት ስልኮች እንድትሰደጡን በፈጣሪ ስም እንማጸናለን።

የሰሌዳ ቁጥር SD 02582
ባለ 5 ኮለኔት
3L ሚኒባስ

መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ Share በማድረግ ይተባበሩ
ስልክ ቁጥር
0911729084
0926040906
092 708 6768

Via መላኩ ዘፍኔ

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
TIKVAH-MAGAZINE
#Update: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በናይጄሪያ ያደረጉኑትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ተከትሎ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የተገለጸው የሚኒስቴሮች የጋራ ስብሰባ ዛሬ ጀምሯል። ዛሬ እየተካሄደ በሚገኘው የሁለቱ ሀገራት የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ላይም ቀደም ሲል በማዕድ እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመስራት የተስሟሙባቸውን ነጥቦች ጨምሮ አብሮ መስራት የሚችሉባቸው ሌሎች ጉዳዮች…
#Update : ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ በፖለቲካ ፣መከላከያ፣ በባህልና በቱሪዝም፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የተፈረመው ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ በቆየው 3ኛው የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ነው።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ ኩል በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻዉል እና በናይጄሪያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሁመር ዘናባ ፈርመውታል።

ሀገራቱ በመገናኛ ብዙሃን አስተዳደር እና አመራር በተለይም ፣የወጣቶች ተሳትፎ በማሳደግ እና የፖን-አፍሪካዊነትን የሚዘክሩ ይዘቶችን ለማበልፀግ በሚቻሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ያለውን ፀጋ በመጠቀም ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚነት እንዲዉል ያስችላል ተብሏል።

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በአፍሪካ ያለዉን እምቅ የሰዉ ሀብት እና ገበያ በጋራ ማልማት እና መጠቀም በስምምነቱ ዉስጥ የተካተቱ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የ4ተኛ የሁለቱ አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እ.ኤ.አ.2024 አቡጃ ከተማ- ናይጄሪያ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot
#Hawassa 📍

ከነገ ማለትም ሰኔ 8/2014 ጀምሮ በሐዋሳ ከተማ ለባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች የተከለከሉ መንገዶችን ይፋ ማድረጉን በአስተዳደሩ የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ አስታወቀ

የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊ አቶ አበራ አዴላ እንዳስታወቁት ከጨርቃጨርቅ በአላቲዮን ሆስፒታል አድርጎ በአቶቴ እስከ ትሩፋት እና በሎጊታ መስመር አድርጎ ሲዳማ ሱመዳ ድረስ ያለው ለባጃጅ የተከለከለ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም መሰረት የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ለህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በሚከተሉት መስመሮች ብቻ አቋራጭ መንገድን መጠቀም እንደሚችሉም ነው አቶ አበራ የገለፁት።

እንደ ሀላፊው አቋራጭ መንገዶቹ፦

* የጨርቃ ጨርቅ መንገድ ይዞ ባለው የሲዳማ ክልል ፀረ ሙስና ኮምሽን ጎን መስቀለኛ አካባቢን በመጠቀም፣

* ሀዮሌ ትምህርት ቤት አጥር ጎን ያለው መስቀለኛ የትራፊክ መብራትን ይዞ ወደ ስታዲየም መሄጃ መንገድን በመጠቀም፣

* ታቦር መካነየሱስ አጥር ጎን ባለው ወደ አሊቶ ሄዋኖ ትምህርት ቤት መሄጃ መስቀለኛ መንገድን በመጠቀም፣

* የትሩፋት መንገድ ማቋረጫ ሆኖ ባለው የትራፊክ መብራት በሁለቱም አቅጣጫ ያለውን አካባቢ በመጠቀም፣

* ከሎጊታ ካፌና ሬስቶራንት ፊት ለፊት ያለውን እና የቲቲሲ መሄጃ መስቀለኛ መንገድን ይዞ ወደ ኮምቦኒ ትምህርት ቤት ባለው ኮብል ስቶን አካባቢን ያለውን አቅጣጫ በመጠቀም እና

* በናኦል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አድርጎ የዊነር ባርና ሬስቶራንት መሄጃ መንገድን እንደ አቋራጭ በመጠቀም አገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ አቶ አበራ አስረድተዋል።

ከነገ ጀምሮ ይህንን በማያከብሩ የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ ተገቢው የእርምት እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል።

@tikvahethmagazine
ትላንት ጥዋት አንድ የአዲስ አበባ ቤተሰባችን አባል ያጋጠመውን አጋርቶናል።

ከ24 ወጥቶ ወደ ኢምፔሪያል በሚወስደው መንገድ አንድ እግረኛ ላይ በ " ኮድ 2 AA 16429 " ታርጋ የነበሩ 4 ሰዎች አንቀውት መሬት አስተኝተው ሲፈትሹት መመልከቱን ገልጿል።

በወቅቱ ይኸው እግረኛ ላይ ይህ ድርጊት ከፈፀሙ ግለሰቦች አንዱ አካባቢውን ሲቃኝ የነበረ ሲሆን መሳሪያ አውጥቶ እንዳሳየውና በኃላ ሊከተላቸው ቢሞክርም በፍጥነት በመንዳታቸው እንዲሁም አካባቢውም የሚመች ስላልሆነ መጨረሻቸውን ሳያይ ቀርቷል።

በአራቱ ሰዎች ተይዞ የነበረው ግለሰብ ነቅቶ ሲንቀሳቀስ በስፖኪዮ መመልከቱን የገለፀልን ይኸው ቤተሰባችን ምናልባት ታርጋውን ካላገኘው ኮድ 2 AA 16429 መሆኑን ጠቁሟል።

ጉዳዩን ለፖሊስም እንዲያውቀው አድርጓል።

ይህ የተፈፀመው ጥዋት ላይ ነውና ጥንቃቄም ማድረግ አይለያችሁ ብሏል።

ለቤተሰባችን ይጠቅማሉ የምትሉትን ጥቆማ፣ አስተያየትና የጥንቃቄ መልዕክት @tikvahmagbot ላይ ይጻፉልን።

@tikvahethmagazine
#የዛሬ ( ሠኔ 7/2014 )

💥 ዛሬ በጋምቤላ ክልል የተፈጠረው የተኩስ ልውውጥና የወጡ መረጃዎች በአጭሩ፦

- በጋምቤላ ክልል ዋና ከተማ " ጋምቤላ " ዛሬ መንግስት አሸባሪ ያለው የሸኔ ወታደሮች (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው) እና የጋምቤላ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው የነበር ሲሆን የመንግስት ኃይሎች ወስደውታል በተባለው እርምጃ ለሰዓታት የዘለቀው የተኩስ ልውውጥ ጋብ ብሏል።

- ከጠዋቱ 12:30 ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ያለማቋረጥ እስከ ረፋዱ 4 ሰዓት ከ20 ሲካሄድ ቆይቶ መጠነኛ መረጋጋት በከተማው ተፈጥሯል ነው የተባለው።

- የክልሉ መንግስት ቀየት ብሎ በሰጠው መግለጫ ''በተወሰደዉ እርምጃ በታጣቂ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ሰበአዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሷል" ሲል አመልክቷል። እስካሉን የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ የተጣራ መረጃ አልተገለጸም።

💥 ተመሳሳይ የተኩስ ልውውጥ በጊምቢና በደምቢዶሎ፦

- በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ከተማ ከማለዳ 12:30 ጀምሮ በጣም የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር የቲክቫህ ቤተሰቦች ገልጸውልናል።

- በሌላ ደምቢዶሎ ከተማ ከማለዳዉ 12:00 ጀምሮ ከባድ የተባለ ተኩስ ልውውጥ እንደነበር የቲክቫህ ደምቢ ዶሎ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

- የተኩስ ልውውጡ መንግስት ሽብርተኛ ብሎ በህ/ተ/ም/ቤት የፈረጀው ሸኔ (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ ነው የሚጠራው) እና በመንግስት ሀይል መካከል ነውም ብለዋል።

- በተኩስ ልውውጡ ጉዳት ስለ መድረሱ እንደሰሙ ያመለከቱት የቤተሰብ አባሎቻችን ከቤት መውጣት እንዳልቻሉና የኤሌክትሪክ አገልግሎትም እንደተቋረጠባቸውም ጠቁመዋል። በጉዳዩ ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ያለው ነገር የለም።

👉 የጠ/ሚ/ሩ ምላሾች

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ከህ/ተ/ም/ቤት አባላት እየተነሳላቸው ላለው ጥያቄ ማብራሪያ እና ምላሽ ሰጥተዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ያነሷቸውን ጉዳዮች እና ተጠይቀው ማብራሪያ የሰጡባቸውን በዚህ ተያይዟል : https://telegra.ph/የጠሚሩምላሾች-06-14

ችሎት

- በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአራዳ ምድብ ቻሎት ዛሬ ጠዋት 3:00 ሰዓት ላይ የቀረበው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ አቃቤ ህግ ቀርቦ ተጨማሪ 15 የክስ መመሥረቻ ቀን ጠይቆ ተፈቅዶለታል ስለሆነም ለሰኔ 22/2014ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ተቀጥሯል።

- በተመሳሳይ ጋዜጠኛ መዓዛ እንዲሁም ጋዜጠኛ ሰለሞን ላይ የተጠየቀው 14 ቀን ቀጠሮ ውድቅ አድርጎ 5ቀን ተቀጥረዋል።