#update ሙሉ በሙሉ በመንግስት ስር የነበሩ የመንግስት የልማት ድርጅቶችን በከፊል ወይም በአጠቃላይ ወደ ግል ለማዛወር በተወሰነው መሰረት በየተቋማቱ ላይ ጥናት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡ ከነዚሁም የልማት ድርጅቶች ውስጥ በስኳር ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ 13 የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል ለማዛወር ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴርና የስኳር ኮርፖሬሽን በጋራ መጠይቅ አዘጋጅተዋል ተብሏል፡፡ ፋብሪካዎቹ ወደ ግል የሚዛወሩት በከፊል ይሁን በሙሉ እስካሁን አልታወቀም፤ ግን ሂደቱ ተጀምሯል፡፡
Via #Sheger_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #Sheger_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አንዳንድ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች የብጥብጥ መነሻ እየሆኑ ነው፤ ይህንን ችግር ለማስቀረት ህብረተሰቡ ይተባበረኝ አለ፡፡
Via #Sheger_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #Sheger_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባለፉት 6 አመታት ውስጥ ለሴቶች ኢንተፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጄክት 3 ቢሊየን ብር መለቀቁ ተሰማ፡፡
የአለም ባንክ እና ሌሎች የውጭ ለጋሽ ድርጅቶች ለፌደራል ከተሞች ስራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ስር ለሚገኘው የሴቶች ኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ፕሮጄክት ዌዴፕ ነው ብሩ የተለቀቀው፡፡
እርዳታው ከአለም ባንክ፣ ከጃፓን፣ ከጣሊያን እና ከሌሎች የአውሮፓ ሀገሮች እንደፈሰሰ ሰምተናል፡፡ በዚህ ፕሮጀክትም ሴቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታት፣ የበዛ ችግሮችንም ለመፍታት ረድቷል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ ከተጀመረም አንስቶ እስካሁን ከ30 ሺህ በላይ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ተመዝግበው የስራ ማስኬጃና ለኢንቨስትመንት እጃቸው ላጠረባቸው 3 ቢሊዮን ብር ብድር ተለቋል ተብሏል፡፡
ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ መንግስት ከአለም ባንክ ባገኘው ብድር በስድስት የክልል ከተሞች ወደ ስራ መግባቱን ከኤጀንሲው ተሰምቷል፡፡
Via #Sheger

#SHEGER
በቻይና መንግሥት ድጋፍ የሚገነባው የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ አረንጓዴ ልማት ፕሮጀክት ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት ላይም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና የቻይና መንግስት ተወካዮች ተገኝተው ነበር።