TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Omo

የኦሞ ወንዝ ሙላት ከቁጥጥር ውጭ መሆኑን ተከትሎ የአካባቢው አርሶአደር በ4ቱም አቅጣጫ ንብረቱን ጥሎ መሸሽ ላይ ነው።

ችግሩ እንደሚከሰት ታውቆ በርካታ ስራ ሲሰራ ቢቆይም የኦሞ ወንዝ መጠን ከተለመደውና ከታሰበው ውጭ መሆኑን ተከትሎ ግን ለዞኑ መንግስትም ሆነ ለግብረሰናይ ድርጅቶች ሁኔታው ከባድ ሆኖባቸዋል።

የወንዙ ሙላት ከባድ መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ አርብቶ አደሩን በአራት ጊዜያዊ መጠለያ እንዳስቀመጡትና ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚያሻዉ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማልኮ ገልጸው " በአሁኑ ወቅት የውሃው መጠን ከተለመደው ውጪ እየጨመረና ሰፊ ቦታ እየያዘ ከመምጣቱ የተነሳ ለኦሞራቴ ከተማ ማህበረሰብ እንደሚያሰጋ " ተናግረዋል ።

ችግሩ እየባሰ የመጣው የውሃውን አቅጣጫ የማስቀየርና የማፍሰስ ስራዎች በኢንቨስተሮች እርሻ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያስከተለ ነው በሚል በጅምር በመቆሙ መሆኑን የሚያነሱት የአካባቢዉ ነዋሪዎች በበኩላቸው ችግሩ በየአመቱ የሚፈጠር በመሆኑ ኑሯቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገዉ ይገልጻሉ።

በመሆኑም አሁን ላይ ማህበረሰቡ ቤቱ እየተዋጠበት ከብቱ እየሞተበትና የሚቀምሰውም በመጥፋቱ ተስፋ በመቁረጥ አካባቢውን ጥሎ መሸሽ መጀመሩ ተሰምቷል።

ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኦሞ ወንዝ ሙላት ጋር ተያይዞ በአከባቢው በተደጋጋሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሲከሰት እንደነበር የገለጹት የዳሰነች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደለ ሀቴ በበኩላቸው አምና ከ79 ሺህ በላይ አርብቶ አደሮች በወንዙ ሙላት መጥለቅለቅ ከመኖሪያ ቀዬአቸው መፈናቀላቸውን ይናገራሉ።

እነዚህ አርብቶ አደሮች እስከ ዛሬ በጊዜያዊ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ የተደረገ መሆኑን የሚገልጹት አቶ ታደለ ለእርሻ ስራ በሚል ወደ ቀድሞ ቀያቸው በተመለሱት ላይ አሁንም ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል ።

አሁን ላይ ወንዙ መደበኛ የፍሰት አቅጣጫውን በመልቀቅ የጉዳት መጠኑን አስፍቶና አርብቶ አደሩን አፈናቅሎ ለማህበራዊ ችግር እየዳረገ ሲሆን በኢፌዴሪ ውሃና ኢነሪጂ ሚኒስቴር አማካኝነት ችግሩን ለመቅረፍ የተጀመረው የመከላከያ ፕሮጀክት መፍትሄ ያመጣል ቢባልም ሊጠናቀቅ አልቻለም።

በዚህ ምክኒያትም አሁን ላይ በ33 ቀበሌዎች የነበሩ መሠረተ ልማቶች ትምህርት ቤቶች ጤና ኬላዎችና መኖሪያ ቤቶች በውሃ ሊከበቡና ነዋሪው ለከፋ ችግር ይጋለጥ ዘንድ ምክኒያት ሆኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia