TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#KonssoZone📍

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን ሰገን ዙሪያ ወረዳ ባለፈው ቅዳሜ የወረዳው የገቢዎች ኃላፊ ምግብ ቤት ውስጥ በጥይት መገደሉ ከተገለጸ በኋላ በተከታታይ 4 ሰዎች መሞታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የደረሰው መረጃ ያሳያል።

ህይወታቸው ያለፈው የ ' ሰገን ገነት ቀበሌ ' ሊቀመንበር አቶ ኩሴ ጦኔ እንዲሁም አንድ የሚሊሻ አባል እና 2 ነዋሪዎች ናቸው።

የወረዳው የመንግስት ተጠሪ አቶ ገመይዳ ጉዴኖ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለጹት መጋቢት 18 ቀን 2014 የአከባቢው ሚሊሻ ከደራሼ ልዩ ወረዳ ሀይቤና ቀበሌ በኩል የመጡ ታጣቂዎች ጥቃት ፈጽመውበት መገደሉን ገልጸዋል። አቶ ገመይዳ ፥ " ጥቃቱ ሲፈጸምም ሽፋን የሰጠ አካል የለም " ሲሉ ነው የገለጹት።

በመቀጠልም ፤ መጋቢት 22 በግምት ከቀኑ 8:30 አከባቢ የሰገን ገነት ቀበሌ ሊቀመንበር ኩሴ ጦኔ በታጣቂዎቹ ታፍኖ መሳሪያውን ተቀምቶ ተገድሏል ብለዋል። ''ትላንት ማታ ነው ሬሳ ያወጣነው'' ሲሉም ተናግረዋል።

በዚያው ቀን 5:30 አከባቢም በመጓዝ ላይ በነበሩ 3 ሰዎች ላይ በተከፈተ ጥቃት ሁለቱ ህይወታቸው ሲያልፍ አንደኛው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ የህክምና ክትትል እየተደረገለት እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት መረጃ ይድረስንልን ያሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ፤ ጥቃቱን የሚፈጽሙት " በትጥቅ የተደራጁና መሳሪያ የታጠቁ አካላት " መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከአካካቢው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ያሰባሰብነው መረጃ እንደሚያሳየው ደግሞ የክልሉ ልዩ ኃይል ከነበረበት ካንፕ ለቆ በወጣበት ቅጽበት የቀበሌው ሊቀመንበር አቶ ኮሴ ጡኔ በታጣቂዎቹ መገደላቸውን ይጠቁማል።

አቶ ገመይዳ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንዳሉት የጸጥታ መዋቅሩ ከየቀጠናው ተሰብስቦ በመውጣቱ ጥቃቱን ሚሊሻ ብቻውን መከላከል እንዳልቻለ ጠቁመዋል።

የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በርሻ ኦላታ ፤ " ፅንፈኛው " ሲሉ የጠሩት ኃይል እየፈጠረ ባለው ሁከትና ብጥብጥ ህዝቡ ዳግም መፈናቀሉንና ለእንግልት መዳረጉን ገልፀዋል።

አቶ በርሻ ፤ የመለጋ እና ዱጋያ ቀበሌ ህብረተሰብ መንግስት የሰጣቸውን ጊዜያዊ መጠለያ ሸራ ቤት በመወጠር ቤት ንብረቱ በተቃጠለበት ቦታ ቀልሰው መኖር በጀመሩበት ወቅት ጥቃት መፈጸሙን አንስተዋል። በዱጋያ ትም/ት ቤት እና ለሰራዊት ማረፊያ የተገነባው ሁለት ካምፕ ላይም ጥቃት ደርሷል ሲሉ ነው የገለፁት።

በተመሳሳይ ከትላንትና መጋቢት 22 ቀን 2014 ማታ ጀምሮ " ጋርጨ " በሚባል ቀበሌ ከዚህ ቀደም በነበሩ ግጭቶች ተፈናቅለው ሸራ ወጥረው በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት መከፈቱን የቲክቫህ ቤተሰቦቻችን መልዕክት ጠቁመዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ሸራውን ሙሉ ለሙሉ ማቃጠላቸውን እና ለመቋቋሚያ የተሰጣቸውን ቆርቆሮም መዘረፉ ተጠቅሷል።

በአጠቃላይ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች በ7ቱ ላይ ጥቃት የተፈጸመ ሲሆን አምስቱ ሙሉ ለሙሉ መቃጠላቸውን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡ ከፍተኛ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ እንደሚገኝ የገለጹት የአካባቢው ቤተሰቦቻችን ሶስት አመት ሙሉ በተመሳሳይ ችግር ውስጥ መሰቃየታቸውን ይናገራሉ።

ችግሩ እንዲፈታ በተደጋጋሚ የክልልና የፌደራል መንግስት አካላት እንዲያውቁት ቢደረግም እዚህ ግባ የሚባል ምላሽ እንዳላገኙና ይበልጡኑ ይህ ችግር ባለበት ሁኔታ ያሉትን የጸጥታ ኃይሎች ማንቀሳቀስ ለችግሩ መስፋፋት አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia