TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EthiopianOrthodoxTewahedo

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በዓመቱ ውስጥ ከሚጾሙ አጽዋማት መካከል  ' ጾመ ሐዋርያት ' (በተለምዶ የሰኔ ጾም) በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

ይህ ጾም የሚፈሰከው ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ/ም ነው።

ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት መካከል አንዱ የሆነው ጾመ ሐዋርያት በየትኛውም አመት ላይ ቢውል ሰኞ ቀን ከሚጀምሩት አፅዋማት አንዱ ነው፡፡

ይህ ጾም የሚፈሰክበት ከሐምሌ 5 አይበልጥም ፤ የሚጀመርበት ቀን ደግሞ በዓለ ጰራቅሊጦስ እንደ ገባ ባለው የመጀመሪያው ሰኞ ነው።

እንደ ቤተክርስቲያኗ አስተምሮ ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰማያዊ ተልእኮ ስለተሰማቸው ከ5ዐ ቀን በኋላ በበዓለ ጰራቅሊጦስ ማግስት የጀመሩት ጾም ነው።

ጾሙ ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ከተቀበሉ በኋላ ለስብከተ ወንጌል ከመሰማራታቸው በፊት የጾሙት ነው።

ቤተክርስቲያኗም ትንሳኤ ከዋለ ከበዓለ 50 በኃላ የፆሙን አዋጅ ለልጆቿ አውጃለች።

ይህ ጾም እንደ ሌሎቹ አጽዋማት ሁሉ እያንዳንዱ ምእመን ሊጾመው የሚገባ እንደሆነ ቤተክርስቲያን ታዛለች።

ከዚህ ጾም በኃላ ከሰባቱ አጽዋማት መካከል የሆነው ጾመ ድኅነት (ረቡዕ እና ዓርብ) የሚጀምር ይሆናል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia