TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.8K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአጭርና በረጅም ጊዜ በሰላም ዙሪያ ለሚሰሩ ስራዎች አስር አባላት ያሉት የምርምር ቡድን ማቋቋሙን አስታወቀ። ለዚህ የሚሆን በጀት መመደቡንም ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሃና እንደገለጹት ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት በሰላም ዙሪያ ለሚደረጉ የምርምር ስራዎች በየዓመቱ አንድ ሚሊዮን ብር ተመድቧል። በዚህ አመትም እስከ ሰኔ 30 ለሚሰሩ ስራዎች አንድ ሚሊዮን ብር ተመድቧልብልዋል። ከዚህ በተጨማሪም የምርምር ቡድኑ በድህረ ግጭት እና በአስተዳደር ዙሪያ ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ይሰጣል ብለዋል።

via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ‼️

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትክክል የዩኒቨርሲቲውን መስፈርት አሟልተዋል ላላቸው 6 ዶክተሮች የሙሉ ሊቀ -ጠበብትነት ወይም የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል። ከተቋሙ ሴኔት የቀረበለትን መረጃ መነሻ በማድረግ ማዕረጉን እንደሰጠ ያስታወቀው ዩኒቨርሲቲው ጥር 26 ቀን 2011 ዓ.ም ነው። ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ዶክተር ኂሩት ወልደ ማርያም፣ ለዶክተር ምሩጽ ግደይ፣ ለዶክተር ሃጎስ አሸናፊ፣ ለዶክተር ተፈሪ ገድፍ፣ ለዶክተር ጌታቸው አሸናፊ እና ለዶክተር መረራ ጉዲና ማእረጉን የሰጠው።

ግለሰቦቹ በ4 ዋና ዋና መስፈርቶች የተመዘኑ ሲሆን፤ ያበረከቱት በጎ የመማር ማስተማር ሥራ፤ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያበረከቱት የማኅበረሰብ አገልልግሎት፤ ምርምር እና ኅትመት ዋናዎቹ ናቸው ብለዋል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና።

ዩኒቨርሲቲው በዓመት ኹለት ጊዜ #የፕሮፌሰርነት ማዕረግ እንደሚሰጥ እና ሂደቱ ብዙ ማጣራቶችን የሚያልፍ በመሆኑ ከ2 እስከ 3 ዓመታት ድረስ እንደሚዘገይም አብራርተዋል።

በአጠቃላይ የማዕረግ አሰጣጡም ላይ ይሁን አሁን ማእረግ ባገኙት ላይ የተገቢነት ጥያቄ እየተነሳ ነው በሚል የጀርመን ራድዮ ጥያቄ ያነሳላቸው ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ሳይገባው እና መስፈርቱን *ሳያሟላ ማእረጉን ያገኘ ሰው የለም የሚነሳው ቅሬታም መሰረተ ቢስ ነው ሲሉ መልስ ሰጥተዋል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጭው ግንቦት አጋማሽም የሴኔቱን ስብሰባ ተከትሎ ተጨማሪ የሊቀ-ጠበብትነት ወይም የፕሮፌሰርነት ማእረግ እንደሚሰጥ ለዚህም በዛ ያሉ ጥያቄዎች እየተመረመሩ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር #ጣሰው_ወልደሃና ለጀርመን ራድዮ አሳውቀዋል።

ምንጭ፦ የጀርመን ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia