TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኛው‼️

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጄር ጀኔራል #ክንፈ_ዳኘውን ጉዳይ በመመልከት ላይ ይገኛል።

ፍርድ ቤቱ ሜጄር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው መንግስት የመደበላቸውን መከላከያ ጠበቃ በማንሳት በራሳቸው ጠበቃ እንዲያቆሙ ባለፈው አርብ ብይን መስጠቱ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ሜጄር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው በራሳቸው የግል ጠበቃ አቁመዋል።

ሆኖም ተጠርጣሪው ከግል ጠበቃቸው ጋር መገናኘት እንዳልቻሉ እና መርማሪ ባለበት የተገናኘን በመሆኑ ሚስጥር ማውራት አልቻልንምና ለመወያየት ጊዜ ይሰጠኝ ብለው በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ ሌሎች ጉዳዮች እስከሚታዩ ድረስ ብሎ እንዲወያዩ ፈቅዷል።

የኢትዮ ቴሌኮም የሴኪዩሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ የነበሩት ኮለኔል #ጉደታ_ኦላናም ዛሬ በዚሁ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ያልታወቀ ሀብት በማካበት እና በተጠረጠሩበት በዚህ ወንጀል እና በሌሎች የሙስና ወንጀሎች ላይ የሚደረግ ምርመራን በማደናቀፍ ወንጀል ተጠርጥረው ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት።

ተጠርጣሪው ጠበቃ ለማቆም የገቢ አቅም የለኝም በማለታቸውም መንግስት ጠበቃ አቁሞላቸው ጉዳዩን ለማየት ፍርድ ቤቱ ለህዳር 13 ቀን 2011 ቀጠሮ ሰጥቷል።

በሌላ በኩል መርማሪ ፖሊስ የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ አቶ #ተስፋዬ_ኡርጌን በተጨማሪነት በሰብዓዊ መብት
ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

አቶ ተስፋዬ ኡርጌ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።

መርማሪ ፖሊስም የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደህንነት የስራ ባልደረባ በተጨማሪነት በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

አቶ ተስፋዬ የደህንነት መምሪያ ሀላፊ ሆነው ሲሰሩ ሰዎችን በሽብር ተጠርጥራችኋል በሚል በስውር እስር ቤት በማሰርና በማሰቃየት፥ እርቃናቸውን በካቴና አስረው ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ በማቆየት፣ ግለሰቦችን ባልተገባ መልኩ ለሽብር መልምለው ወደ ኤርትራ በመላክ እንደጠረጠራቸው ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በሽብር ከተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ገንዘብ በመቀበል እና በሀዋላ ከተጠርጣሪዎች ላይ ህገ ወጥ ገንዘብ በመቀበል በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁም ብሏል መርማሪ ፖሊስ።

ቀሪ ስራዎችን ለማጠናቀቅም 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

አቶ ተስፋዬ በሰጡት ምላሽ እርሳቸው የተጠረጠሩበት ጉዳይ በግልጽና በተናጠል እንዳልቀረበ በመግለጽ፥ እርሳቸውን ለመያዝ በቂና ዝርዝር ጉዳይ አለመኖሩን አስረድተዋል።

በተጨማሪም ሀብት የመፍጠር ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ሃብት ማፍራታቸውንና ለአራት ወራት ፍርድ ቤት እየተመላለሱ መሆኑን በመጥቀስ፥ ሃብት ከማፍራት ጋር ተያይዞ ሀምሌ 5 ቀን 2010 ዓ.ም ቤታቸው መበርበሩንና ምርመራው በወቅቱ ማለቅ ነበረበት ብለዋል።

አሁን ላይ መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው ተጨማሪ ጊዜም ሊሰጥ አይገባም በማለት ተቃውመዋል።

ችሎቱም አቶ ተስፋዬ በተጨማሪነት የተጠረጠሩበት ወንጀል በተብራራ መልኩ እንዲቀርብና ፖሊስ የጠየቀውን 14 ቀን #በመፍቀድ ለህዳር 24 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ:- ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia