TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
እንግጫ ነቀላ በዓል!

ባህላዊ እሴቶቻችንን በማልማት ዘላቂ ሰላማችንን እናረጋግጥ!


#የእንግጫ_ነቀላ በዓል ነሃሴ 29 እና 30 እንደሚከበር የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ አስታውቋል። የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህል ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወ/ሮ ዉዳለም አልማዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እየደበዘዘ የነበረዉን የእንግጫ ነቀላ በዓል ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ ዞናዊ በሆነ መልኩ ማክበር መጀመሩን ገልጸዉ እንግጫ ነቀላን ህዝባዊ በዓል በማደረግ የጎጃም ህዝብ መገለጫ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ መምሪያ ሃላፊዋ አያይዘዉም በዓሉን በማልማት የዞኑ አንዱ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነና ይህም ለዞኑ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉ አክለዋል፡፡ እንግጫ ነቀላ በጎጃም ማህበረሰብ ዘንድ በየዓመቱ በዘመን መለወጫ ወቅት በልጃገገረዶችና ወጣት ወንዶች የሚከበር በዓል ሲሆን በዚህ ዓመትም "ባህላዊ እሴቶቻችንን በማልማት ዘላቂ ሰላማችንን እናረጋግጥ" በሚል መሪ ቃል ይከበራል።

Via East gojjam zone culture-tourism department
@tsegabwolde @tikvahethiopia