TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አብን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዶ/ር በለጠ ሞላን በድጋሚ የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መረጠ። አቶ መልካሙ ሹምዬ ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል። የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ፤ ፓርቲው ለ3 ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን ሲያካሂድ እንደቆየና የሥራ አስፈፃሚ አባላቱን በአዲስ በማደራጀት ማጠናቀቁን ገልጸዋል። በዚህም መሠረት፦ 👉 ዶ/ር…
" አብን በጠቅላላ ጉባዔው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደመረጠ ተደርጎ የሚሰራጭ መረጃ ሐሰት ነው " - አቶ ጣሂር መሐመድ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባለፉት ሁለት ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን አካሂዷል።

ዛሬ ደግሞ ሦስተኛ ድርጅታዊ ጠቅላላ ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ጣሂር መሐመድ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሰጡት ቃል ፤ ትናንት በነበረው #የማዕከላዊ_ኮሚቴ_ስብሰባ በተወሰነ መልኩ የአመራር ሽግሽግ ለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች እልባት መሰጠቱን ገልፀዋል።

" ነገር ግን የፓርቲውን መመሪያ እና ደንብ በውል ካለመረዳት #በጠቅላላ_ጉባዔው የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደተመረጠ የሚናፈሰው ወሬ ትክክል አይደለም " ሲሉ አብራርተዋል።

አቶ ጣሂር ጠቅላላ ጉባዔው የሚመርጠው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን ነው ያሉ ሲሆን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ዘመን የሚጠናቀቅበት ጊዜ ደግሞ አልደረሰም ብለዋል።

በዚህም በማዕከላዊ ኮሚቴ የተላለፈ ውሳኔ በጠቅላላ ጉባዔ እንደተሻረ ተደርጎ በተለይ በማኅበራዊ የመገናኛ አውታር የሚንሸራሸረው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ጣሂር መሐመድ በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ በጠቅላላ ጉባዔው ምንም አይነት የምርጫ ሂደት እየተደረገ እንዳልሆነ ከሰዓታት በፊት ገልፀዋል።

" ትላንት በተጠናቀቀው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባችን የአመራር መተካካቶችን አድርገናል። " ያሉት አቶ ጣሂር " አሁን ላይ የጠቅላላ ጉባዔያችን በተሳካ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል " ብለዋል።

@tikvahethiopia