ኤጄንሲው ማህበረሰቡንና ተማሪውን ለውጤቱ መዘግየት ይቅርታ ጠይቋል!
የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ በውጤቱ መዘግየት ተማሪዎችን እንዲሁም መላውን ማህበረሰብ ይቅርታ ጠይቋል። ፈተናው ቀደም ብሎ ታርሞ የተጠናቀቀ ቢሆንም በታየው የውጤት ግሽበት ምክንያት እስከዛሬዋ ቀን ድረስ መያዙ ነው የተገለፀው፡፡ በተካሄደው የማጣራት ሂደት 68 የሚሆኑ ተፈታኝ ተማሪዎች በተጨባጭ የፈተና ደንብ ጥሰት ያካሄዱ መሆናቸው በመረጋገጡ ሙሉ በሙሉ ውጤታቸው የተሰረዘባቸው ሲሆን በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብ/ብ/ህ፣ በአማራ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚገኙ የተወሰኑ ት/ቤቶች 846 ተፈታኞች በተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ያገኟቸው ውጤቶች ማጣራት #የሚጠይቁ ሆነው በመገኘታቸው እንዲያዝ መደረጉን ኤጀንሲው አስታውቋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia

" የወረዳ አመራሮቹ 50 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ይዤያቸዋለሁ " - ፖሊስ
በአዲስ አበባ ከተማ የወረዳ አስፈፃሚ እና ምክትላቸው " ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ያዝኳቸው " ሲል ፖሊስ ገለፀ።
የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አያናው አስራት ፤ ምክትላቸው የስራ ኢንተርፕራዝና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ እዮብ አፈወርቅ በ " መስሪያ ቦታ " አሰጣጥ ተደራድረው የሙስና ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዙን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሳውቀው።
ፖሊስ ፤ በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ከስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ብሎክን መሰረት በማድረግ የተፈጠረ የስራ እድል ላይ ከተጠቃሚ ወላጅ ጋር የተሻለ " የመስሪያ ቦታ እናሰጣለን " በማለት የተጠቃሚዋን ወላጅ አባት " ብር ካልሰጠኸን ልጅህን ከስልጠና እናወጣታለን፣ የስራ እድልም አይፈጠርላትም " በማለት ወላጅ አባቷን በማስፈራራት 6 ኪሎ አከባቢ ልዩ አዲስ ሆቴል 50,000 ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን ገልጿል።
ግለሰቦቹ እጅ ከፍንጅ የተያዙት ዛሬ ከቀኑ 10:30 ሰዓት ላይ መሆኑን ያሳወቀው ፖሊስ አሁን ላይ ፖሊስ ጣቢያ ገብተው ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብሏል።
ፖሊስ የከተማው ነዋሪዎች በየትኛውም የመንግስት ተቋም ሙስና #የሚጠይቁ እና #የሚቀበሉ ማናቸውም አካላትን ለፖሊስ እንዲጠቁሙ ጥሪ አቅርቧል።
@tikvahethiopia