TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE #ይፋዊ ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ እጩ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 03/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ #በይፋ አሳውቋል። ሚኒስቴሩ የዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች መውጫ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የመፈተኛ ማዕከላት ይሰጣል ብሏል። የ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የተመዘገቡ በግልና በመንግስት ተቋማት የሚገኙ እጩ ምሩቃን…
#Update #የመውጫ_ፈተና

ዘንድሮ 240 ሺህ ሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ይወስዳሉ ተብሏል።

በ2015 በመንግስትና በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተሰበሰበው መረጀ መሠረት 240 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመስጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡

ሚኒስቴሩ ይህ ያስታወቀው የ9 ወራት የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት እያቀረበ በመገኝበት በአሁን ሰዓት ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፤ በ2015 በመጀመሪያ ዲግሪ ኘሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ብሉ -ኘሪንት የተዘጋጀ መሆኑና የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱን ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል፡፡

የመውጫ ፈተናን ለመተግበር የሚያስችል መመሪያ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም የገለፁት ሚኒስትሩ፤ የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሃ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም አብራርተዋል፡፡

በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች (ኮርሶች) ተለይተው፤ በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮት የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱንም አስረድተዋል፡፡

መረጃው የህ/ተ/ም/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የ2015 የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤታቸውን ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ " - ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና መጠናቀቅን አስመልክቶ መግለጫ ልኮልናል። ለመውጫ ፈተና ሊቀመጡ ይችላሉ ተብሎ ተገምቶ የነበረው 240 ሺህ ተማሪዎች ሲሆኑ የመውጫ ፈተናን…
ቁጥሮች . . . #የመውጫ_ፈተና

- የመውጫ ፈተና ለመውሰድ ብቁ ሆነው የተመዘገቡት ከ48 የመንግስት ተቋማት 84,627 ተማሪዎች እና ከ171 የግል ተቋማት 109,612 ተማሪዎች ፤ አጠቃላይ በድምሩ 194,239 ተማሪዎች ናቸው።

- ለፈተናው ከተመዘገቡት ከመንግስት ተቋማት 77,981 ተማሪዎች / 92.15 በመቶ ከግል ተቋማት 72,203 ተማሪዎች / 65.87 ከመቶ ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

- አጠቅላይ ፈተናውን የወሰዱ 150,184 ተማሪዎች ናቸው። (ከመንግሥት 77,981 ከግል 72,203)

- በመንግስት ተቋማት ለፈተናው ከተቀመጡት 77,981 ተማሪዎች ውስጥ 48,632 ተማሪዎች ወይም 62.37 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል።

- በግል ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት 72,203 ተማሪዎች ውስጥ 12,422 ተማሪዎች ወይም 17.2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ አስመዝግበዋል።

- በድምሩ ከአጠቃላይ 150,184 የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን ያለፉት 61,054 ብቻ ናቸው ይህም ማለት 40.65 ነው።

ተፈታኞች ውጤታቸውን #ከእሁድ ማታ ጀምሮ ለፈተናው የተሰጣቸውን User Name በመጠቀም በዚህ ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/ ገብተው ማወቅ ይችላሉ።

(ከትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ)

@tikvahethiopia