TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ በትምህርት ሚኒስቴር አስተባባሪነት እየተካሄደ ባለው "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር የደብተር ማምረት ሥራ ላይ በመገኘት በጎ ፈቃደኞችን አብረው በመስራት አበረታተዋል፡፡

በሀገራችን በተለያዩ #ክልሎች በተከሰቱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ትምህርታቸውን በአግባቡ ላልተከታተሉ እና ላቋረጡ ተማሪዎች የክረምት የማካካሻ ትምህርት እና ለመጪው የትምህርት ዘመን ለመስጠት በታቀደው የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶች ውስጥ ከትራኮን ትሬዲንግ ያገኘውን ወረቀት ተጠቅሞ በሦስት ቀን ውስጥ ወደ 80,000ሺ ደብተሮችን ማምረት መቻሉንና ይህም ስራ ለቀጣይ ሁለት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ካስተባባሪቹ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

በጥቂት ቀናት ውስጥም ቀደም ተብሎ የተሰበሰቡትን መማሪያ ቁሳቁስ ጨምሮ ወደ የክልሉ እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ለበለጠ መረጃ 📞 0911485705

via ከትምህርት ሚኒስቴር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
@tsegabwolde @tikvahethiopia