TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Singapore

የዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም ሲንጋፖር ውስጥ በተፈጸመ ውስብስብ የፈተና ማጭበርበር እጇ አለበት የተባለችው ሴት እንድትያዝ ጥሪ ማቅረቡ ተሰማ።

የ57 ዓመቷ ፖህ ዩዋን ኒይ ስልክ እና ኢርፎን በመጠቀም ተማሪዎች የፈተና ውጤት እንዲያጭበረብሩ የሚያደርግ መዋቅር ዘርግታ እንደነበር ተገልጿል።

የእሷ ሦስት ተባባሪዎቿ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ተብሏል።

ግለሰቧ ቀደም ሲል የአስጠኚዎች ማዕከል ኃላፊት ላይ የነበረች ሲሆን የተፈረደባትን የአራት ዓመት እስራት ካለፈው መስከረም ትጀምራለች ተብሎ ቢጠበቅም አስካሁን እጇን አልሰጠችም።

ግለሰቧ ከሴንጋፖር ኮብልላለች ተብሎ ይታሰባል።

የአገሪቱ ፖሊስ የእስር ማዘዣ ያወጣ ሲሆን ለኢንተርፖል ጥቆማ ካደረጉም በኋላ ኢንተርፖል  " ቀይ ማስጠንቀቂያ " አውጥቷል። ያለችበትን የሚያውቁ እንዲያሳውቁ ጠይቋል።

‘ፖኒ’ በሚል ስም የምትጠራው ግለሰብ የወጣባት " ቀይ ማስጠንቀቂያ " በመላው ዓለም ያሉ የሕግ አካላት ያለችበትን እንዲፈልጉና እንዲይዟት ይሁንታ ይሰጣል።

እ.አ.አ. በ2016 በሲንጋፖር የተካሄዱ ሦስት ብሔራዊ ፈተናዎች ላይ ነው ማጭበርበር የተፈጸመው።

ተማሪዎች #ከቆዳቸው ጋር የሚመሳሰል ኢርፎን አድርገው በተለያዩ የፈተና ማዕከሎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን ተንቀሳቃሽ ስልክ እና ብሉቱዝ #ሰውነታቸው ላይ ተለጥፎ በልብስ እንዲሸፈን ተደርጎ ፈተና ወስደው ነበር።

ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-01-28-3

Credit : BBC

@tikvahethiopia