TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ምስጋና ! የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ፦ " የአፋር ክልላዊ መንግሥት በሰመራ እና አጋቲና መጠለያ ጣቢያዎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች በኢሰመኮ ምክረ ሃሳቦች መሰረት እንዲለቀቁና በፍላጎታቸው መሰረት ወደመጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ በማድረጉ ኢሰመኮ እውቅና ይሰጠል። በተለይ በዚህ ሥራ ላይ በዋናነት የተሳተፉትን የአፋር የክልል አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ቢሮ፣ የክልሉ የጤና…
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ፦

- ኢሰመኮ ሰኔ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. ላይ ባወጣው መግለጫ በአፋር ክልል ፤ ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሰመራ እና አጋቲና ካምፖች በመባል በሚታወቁ ቦታዎች ከትግራይ ክልል አዋሳኝ ከሆኑ 3 የአፋር ክልል ወረዳዎች በታኅሣሥ ወር 2014 ተይዘው የቆዩና በሁለቱ ካምፖች የሚገኙ ወደ 9 ሺህ የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች ያሉበትን አሳሳቢ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ በመግለጽ በአፋጣኝና ያለቅድመ ሁኔታ እንደለቀቁ አሳስቦ ነበር።

- በሁለቱ ካምፖች ውስጥ ተይዘው የሚገኙ ሰዎች ችግር በሚፈታበት ሁኔታ ላይ በሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. በሰመራ ከተማ ከክልሉ መንግሥት ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ምክክር የክልሉ የመንግሥት ኃላፊዎች ችግሩን ለመፍታት አስፈላጊውን እርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀው ነበር። በዚሁ መሰረት በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመተባበር የምግብ፣ ሕክምና እና መጠለያ አቅርቦትን ለማሻሻል እንዲሁም የመንቀሳቀስ ነፃነቶቻቸውን በተሻለ ሁኔታ ለማረጋገጥ ጥረቶች ተደርገዋል፤ እንዲሁም ምዝገባ እና በሁለቱም ካምፖች የሚገኙ ሰዎች ወደየትኛው አካባቢዎች መመለስ እንደሚፈልጉ ለማወቅ የፍላጎት ዳሰሳዎች ተከናውናዋል።

- ኢሰመኮ ነሐሴ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ላይ ባወጣው መግለጫ በእነዚህ ካምፖች የሚገኙ የትግራይ ተወላጆችን ወደ መኖሪያ ቀዬአቸው የመመለሱን ሂደት በበጎ የሚመለከተው እና ክትትል ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን አሳውቆ ነበር።

- በሰመራ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በዋናነት በአፋር ክልል አብአላ አካባቢ ወደሚገኙ የቀድሞ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው የመመለስ ፍላጎት በማሳየታቸው ከነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በተከናወነ የመመለስ ሥራ ወደ መኖሪያ አካባቢዎቻቸው እንዲመለሱ ተደርጎ የሰመራ መጠለያ ጣቢያ #እንዲዘጋ ሆኗል።

- በአጋቲና የመጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ወደ 600 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጆች በተከናወነው የፍላጎት ዳሰሳ ወደ ትግራይ ክልል መሄድ የሚፈልጉ መሆኑን የገለጹ ቢሆንም በአፋር ክልል መንግሥት እና በትግራይ ክልል አስተዳደር መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት ባለመኖሩ በዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል ለማስፈጸም ጥረቶች በመደረግ ላይ ባሉበት ወቅት ጦርነቱ በድጋሚ በመቀስቀሱ ለማስፈጸም አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል።

- ኢሰመኮ የአፋር ክልላዊ መንግሥት በሰመራ እና አጋቲና መጠለያ ጣቢያዎች ተይዘው የነበሩ ሰዎች በኢሰመኮ ምክረ ሃሳቦች መሰረት እንዲለቀቁና በፍላጎታቸው መሰረት ወደመጡባቸው አካባቢዎች እንዲመለሱ በማድረጉ ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopia