TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ለተመራቂም ሆነ ለነባር እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ አልተደረገም " - ወልድያ ዩኒቨርሲቲ

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለየትኛውም የተቋሙ ተማሪ ጥሪ እንዳላደረገ ገልጸ።

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከተቋሙ ጥሪ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ጥያቄ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አድርሰዋል።

አንዳንድ የተቋሙ ተማሪዎች ፤ ከሶስት ቀን በፊት በዲፓርትመንት ኃላፊዎች በኩል ተመራቂ ተማሪዎችን ለመጥራት ስለመታሰቡ መስማታቸውን ፤ ትላንት ምሽት ደግሞ በክፍል ተወካዮች በኩል " ተመራቂዎች ከ19/03/2016 ዓ.ም ጀምሮ እንዲገቡ መወሰኑንና በሰዓቱ መጥተው ሪፖርት እንዲያደርጉ " የሚል አጭር የፅሁፍ መልዕክት እንደደረሳቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያም ይህ ጥሪ ምን ያህል እውነተኛ ነው ? የሚለውን ለማረጋገጥ ወልድያ ዩኒቨርሲቲን አነጋግሯል።

በተማሪዎች ጥሪና ቅበላ ዙሪያ ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርሀን ደጀን ፤ ዩኒቨርሲቲው የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ለየትኛውም የተቋሙ ተማሪ ጥሪ #አለመደረጉን አረጋግጠዋል።

ለተመራቂም ሆነ ለነባር እንዲሁም ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ አለመደረጉን ኃላፊው ገልጸዋል።

የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ተሻሽሎ ተማሪዎች ለመጥራት የሚቻልበት ሁኔታ ሲፈጠር ወደፊት ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል ነው የጠቆሙት።

በአማራ ክልል ባለው የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቻቸው እስካሁን ጥሪ ያላደረጉ ሲሆን ተማሪዎችም ያለ ትምህርት ለወራት በቤታቸው መቀመጣቸውንና በዚህም ከፍተኛ የስነልቦና ጫና እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለፅ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተደጋጋሚ መጠየቃቸው አይዘነጋም።

Via @tikvahuniversity