TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ወጣቶች አቅምና እውቀት እያላችሁ አገርና ፍቅርን ገንቡ" የወላይታ የአገር ሽማግሌዎች
.
.
ወጣቶች አቅምና እውቀት እያላችሁ ሀገርንና ፍቅርን መገንባት እንደሚገባቸው የወላይታ ዞን የአገር ሽማገሌዎቸ አሳሰቡ። የአገር ሽማግሌዎቹ ይህን ያሉት የወላይታ የዘመን መለወጫ የጊፋታን በማስመልከት የተዘጋጀውን የቋንቋና የባህል ሲምፖዝየም መርቀው በከፈቱበት ወቅት ነው።

“ጊፋታ ማለት #ታላቅነት ማለት ነው ያሉት ሽማግሌዎቹ የዘንድሮ የ ጊፋታ በዓል የእርቅና የሰላም በዓል ነው" ብለዋል የአገር ሽማግሌዎቹ። የአገር ሽማገሌዎቹ አክለውም በመካከላችን ያለውን ልዩነት አጥፍተን ከሁሉም የአገሪቱ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር እርቅና ሰላምን በመፍጠር ኢትዮጵያን ማልማት እንደሚገባ ለወጣቶች አሳስበዋል።

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia